ሉቃስ 13:31-35
ሉቃስ 13:31-35 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በዚያ ጊዜ ከፈሪሳውያን አንዳንዶች መጥተው፣ “ሄሮድስ ሊገድልህ ስለሚፈልግ ተነሥተህ ከዚህ ሂድ” አሉት። እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ሄዳችሁ ለዚያ ቀበሮ፣ እነሆ፤ ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ፤ ሕመምተኞችን እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን ከግቤ እደርሳለሁ ብሏል በሉት፤ ይሁን እንጂ ነቢይ ከኢየሩሳሌም ውጭ ይሞት ዘንድ አይገባምና ዛሬና ነገ፣ ከነገ ወዲያም ወደዚያው ጕዞዬን እቀጥላለሁ። “ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ነቢያትን የምትገድዪ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ! ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ፣ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈቀዳችሁም፤ እነሆ፤ ቤታችሁ ወና ሆኖ ቀርቷል። እላችኋለሁ፤ ‘በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው’ እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ አታዩኝም።”
ሉቃስ 13:31-35 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በዚያችም ቀን ከፈሪሳውያን ወገን ሰዎች መጥተው፥ “ከዚህ ውጣና ሂድ፤ ሄሮድስ ሊገድልህ ይሻልና” አሉት። እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “ሂዱና ያችን ቀበሮ እንዲህ በሉአት፤ እነሆ፥ ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ፤ ሕይወትንም አድላለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን እፈጽማለሁ። ዛሬና ነገስ አለሁ፤ በሦስተኛው ቀን ግን እሄዳለሁ፤ ነቢይ በኢየሩሳሌም እንጂ በውጭ ሊሞት አይገባውምና። “ነቢያትን የምትገድሊያቸው፥ ወደ አንቺ የተላኩትን ሐዋርያትንም የምትደበድቢያቸው ኢየሩሳሌም፥ ኢየሩሳሌም፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፍዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ልሰበስባቸው ምን ያህል ወደድሁ? ነገር ግን እንቢ አላችሁ። እነሆ፥ ቤታችሁ ምድረ በዳ ሆኖ ይቀርላችኋል፤ ከዛሬ ወዲያ ‘በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው’ እስክትሉ ድረስ እንደማታዩኝ እነግራችኋለሁ።”
ሉቃስ 13:31-35 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በዚያ ጊዜ ከፈሪሳውያን አንዳንዶች መጥተው፣ “ሄሮድስ ሊገድልህ ስለሚፈልግ ተነሥተህ ከዚህ ሂድ” አሉት። እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ሄዳችሁ ለዚያ ቀበሮ፣ እነሆ፤ ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ፤ ሕመምተኞችን እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን ከግቤ እደርሳለሁ ብሏል በሉት፤ ይሁን እንጂ ነቢይ ከኢየሩሳሌም ውጭ ይሞት ዘንድ አይገባምና ዛሬና ነገ፣ ከነገ ወዲያም ወደዚያው ጕዞዬን እቀጥላለሁ። “ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ነቢያትን የምትገድዪ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ! ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ፣ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈቀዳችሁም፤ እነሆ፤ ቤታችሁ ወና ሆኖ ቀርቷል። እላችኋለሁ፤ ‘በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው’ እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ አታዩኝም።”
ሉቃስ 13:31-35 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በዚያን ሰዓት ከፈሪሳውያን አንዳንዱ ቀርበው፦ ሄሮድስ ሊገድልህ ይወዳልና ከዚህ ውጣና ሂድ አሉት። እንዲህም አላቸው፦ ሄዳችሁ ለዚያች ቀበሮ፦ እነሆ፥ ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ በሽተኞችንም እፈውሳለሁ፥ በሦስተኛውም ቀን እፈጸማለሁ በሉአት። ዳሩ ግን ነቢይ ከኢየሩሳሌም ውጭ ይጠፋ ዘንድ አይገባውምና ዛሬና ነገ ከነገ በስቲያም ልሄድ ያስፈልገኛል። ኢየሩሳሌም፥ ኢየሩሳሌም፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ፥ እናንተም አልወደዳችሁም። እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል። እላችኋለሁም፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።
ሉቃስ 13:31-35 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በዚያን ጊዜ አንዳንድ ፈሪሳውያን ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ “ሄሮድስ ሊገድልህ ይፈልጋልና ከዚህ ወጥተህ ሂድ” አሉት። ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ሄዳችሁ ለዚያ ቀበሮ፦ ‘ዛሬና ነገ አጋንንትን አስወጣለሁ፤ በሽተኞችን እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛው ቀንም ሥራዬን እጨርሳለሁ’ ይላል በሉት። ይሁን እንጂ ዛሬና ነገ ከነገ ወዲያም መንገዴን ወደ ኢየሩሳሌም መቀጠል አለብኝ፤ ነቢይ ከኢየሩሳሌም በቀር በሌላ ቦታ መሞት አይገባውም። “ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም ሆይ! አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ፥ ወደ አንቺ የተላኩትንም መልእክተኞች በድንጋይ የምትወግሪ፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ ሥር እንደምትሰበስብ፥ እኔም ስንት ጊዜ ልጆችሽን መሰብሰብ ፈለግኹ! አንቺና ሕዝብሽ ግን እምቢ አላችሁ። ስለዚህ ቤታችሁ ወና ሆኖ ይቀራል፤ በእውነት እላችኋለሁ፤ ‘በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው’ እስክትሉ ድረስ ከቶ አታዩኝም።”
ሉቃስ 13:31-35 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በዚያን ሰዓት ከፈሪሳውያን አንዳንዶች ቀርበው “ሄሮድስ ሊገድልህ ይፈልጋልና ከዚህ ውጣና ሂድ፤” አሉት። እንዲህም አላቸው “ሄዳችሁ ለዚያች ቀበሮ ‘እነሆ፥ ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ፤ በሽተኞችንም እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን እፈጽማለሁ’ በሉአት። ዳሩ ግን ነቢይ ከኢየሩሳሌም ውጭ ሊጠፋ አይገባውምና ዛሬና ነገ ከነገ በስቲያም መሄድ ያስፈልገኛል። ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም! ነቢያትን የምትገድል፥ ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም። እነሆ፥ ቤታችሁ ወና ሆኖ ይቀርላችኋል። በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው” እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም እላችኋለሁ።