የኀጢአትንም መሥዋዕት ወይፈን አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በኀጢአቱ መሥዋዕት ወይፈን ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ። አረዱትም፤ ሙሴም ደሙን ወስዶ በጣቱ የመሠዊያውን ቀንዶች ዙሪያ ቀባ፤ መሠዊያውንም አነጻው፤ ደሙንም ከመሠዊያው በታች አፈሰሰው፤ ያስተሰርይለትም ዘንድ ቀደሰው። ሙሴም በሆድ ዕቃው ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ የጉበቱንም መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ ስባቸውንም ወሰደ፤ በመሠዊያውም ላይ ጨመረው። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ወይፈኑን፥ ቍርበቱንም፥ ሥጋውንም፥ ፈርሱንም ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለ። ሙሴም ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆን አውራ በግ አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ። ሙሴም ያን በግ አረደው፤ ደሙንም በመሠዊያው ዙሪያ ረጨው። አውራውንም በግ በየብልቱ ቈረጠ፤ ሙሴም ጭንቅላቱን፥ ብልቶቹንም፥ ስቡንም ጨመረ። የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠበ፤ ሙሴም አውራውን በግ ሁሉ በመሠዊያው ላይ ጨመረ፤ ይህ በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነበረ። ሙሴም ለቅድስና የሚሆነውን ሁለተኛውን አውራ በግ አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ፤ አረዱትም። ሙሴም ከደሙ ወስዶ የአሮንን የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግሩንም አውራ ጣት ቀባው። የአሮንንም ልጆች አቀረበ፤ ሙሴም የቀኝ ጆሮአቸውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃቸውንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግራቸውንም አውራ ጣት ከደሙ ቀባ፤ ሙሴም ደሙን በመሠዊያው ዙሪያ ረጨ።
ኦሪት ዘሌዋውያን 8 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘሌዋውያን 8:14-24
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች