ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 27

27
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ሚ​ቀ​ር​በው መባእ የተ​ሰጠ ሕግ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 2“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ማና​ቸ​ውም ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ቢሳል አንተ እን​ደ​ም​ት​ገ​ም​ተው መጠን ስለ ሰው​ነቱ ዋጋ​ውን ይስጥ። 3ለወ​ንድ ከሃያ ዓመት ጀምሮ እስከ ስድሳ ዓመት ድረስ እንደ መቅ​ደሱ ሚዛን ግምቱ አምሳ የብር ዲድ​ር​ክም ይሁን። 4ሴትም ብት​ሆን ግምቷ ሠላሳ የብር ዲድ​ር​ክም ይሁን። 5ከአ​ም​ስት ዓመ​ትም ጀምሮ እስከ ሃያ ዓመት ድረስ ግምቱ ለወ​ንድ ሃያ የብር ዲድ​ር​ክም፥ ለሴ​ትም ዐሥር የብር ዲድ​ር​ክም ይሁን። 6ከአ​ንድ ወርም እስከ አም​ስት ዓመት ድረስ ለወ​ንድ ግምቱ አም​ስት የብር ዲድ​ር​ክም፥ ለሴ​ትም ግምቷ ሦስት የብር ዲድ​ር​ክም ይሁን። 7ከስ​ድሳ ዓመ​ትም ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ወንድ ቢሆን ግምቱ ዐሥራ አም​ስት ዲድ​ር​ክም፥ ለሴ​ትም ዐሥር ዲድ​ር​ክም ይሁን። 8ለግ​ምቱ የሚ​ከ​ፍ​ለ​ውን ቢያጣ ግን በካ​ህኑ ፊት ይቁም፤ ካህ​ኑም የተ​ሳ​ለ​ውን ሰው ከእጁ ባለው ገን​ዘብ መጠን ይገ​ም​ት​ለት፤ ካህ​ኑም የተ​ሳ​ለው ሰው እን​ደ​ሚ​ችል መጠን ይገ​ም​ት​ለት።
9“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ የሚ​ያ​ቀ​ር​በው እን​ስሳ ቢሆን፥ ሰው ከእ​ነ​ዚህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል። 10መል​ካ​ሙን በክፉ፥ ክፉ​ው​ንም በመ​ል​ካም አይ​ለ​ውጥ፤ እን​ስ​ሳ​ንም በእ​ን​ስሳ ቢለ​ውጥ እር​ሱና ልዋጩ የተ​ቀ​ደሱ ይሆ​ናሉ። 11እን​ስ​ሳው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት መሆን የማ​ይ​ገ​ባው ርኩስ ቢሆን፥ እን​ስ​ሳ​ውን በካ​ህኑ ፊት ያቁ​መው። 12መል​ካ​ምም ቢሆን ክፉም ቢሆን ካህኑ ይገ​ም​ተው፤ ካህ​ኑም እን​ደ​ሚ​ገ​ም​ተው መጠን እን​ዲሁ ይሁን። 13ይቤ​ዠው ዘንድ ቢወ​ድድ ግን ከግ​ምቱ በላይ አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​ምር።
14“ሰውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ይሆን ዘንድ ቤቱን ቢቀ​ድስ፥ ካህኑ መል​ካም ወይም ክፉ እንደ ሆነ ይገ​ም​ተ​ዋል፤ ካህ​ኑም እን​ደ​ሚ​ገ​ም​ተው መጠን እን​ዲሁ ይቆ​ማል። 15የተ​ሳ​ለ​ውም ሰው ቤቱን ይቤ​ዠው ዘንድ ቢወ​ድድ ከግ​ምቱ ገን​ዘብ በላይ አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​ምር፤ ቤቱም ለእ​ርሱ ይሆ​ናል።
16“ሰውም ከር​ስቱ እርሻ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢሳል፥ እንደ መዘ​ራቱ መጠን ይገ​መት፤ አንድ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ገብስ የሚ​ዘ​ራ​በት እርሻ አምሳ ወቄት ብር ይገ​መ​ታል። 17እር​ሻ​ው​ንም ከኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ጀምሮ ቢሳል፥ እንደ ግምቱ መጠን ይቆ​ማል። 18እር​ሻ​ው​ንም ከኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት በኋላ ቢሳል፥ ካህኑ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ እንደ ቀሩት ዓመ​ታት ገን​ዘ​ቡን ይቈ​ጥ​ር​ለ​ታል፤ ከግ​ም​ቱም ይጐ​ድ​ላል። 19እር​ሻ​ው​ንም የተ​ሳለ ሰው ይቤ​ዠው ዘንድ ቢወ​ድድ፥ ከግ​ምቱ ገን​ዘብ በላይ አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​ምር፤ ለእ​ር​ሱም ይሆ​ናል። 20እር​ሻ​ው​ንም ባይ​ቤ​ዠው፥ ወይም ለሌላ ሰው ቢሸጥ እንደ ገና ይቤ​ዠው ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ውም። 21እር​ሻው ግን በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ሲወጣ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ እርሻ ይሆ​ናል፤ ርስ​ቱም ለካ​ህኑ ይሆ​ናል። 22ከር​ስቱ እርሻ ያል​ሆ​ነ​ውን የገ​ዛ​ውን እርሻ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢሳል፥ 23ካህኑ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ የግ​ም​ቱን ዋጋ ይቈ​ጥ​ር​ለ​ታል፤ በዚ​ያም ቀን ግም​ቱን እንደ ተቀ​ደሰ ነገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ጣል። 24በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት እር​ሻው የም​ድ​ሪቱ ባለ ርስት ወደ ነበ​ረው ወደ ሸጠው ሰው ይመ​ለ​ሳል፤ የራሱ ወሰን ምድር ነውና።#በግ​እዙ “እስመ ደወለ ዚኣሁ ውእቱ ወም​ድሩ” የሚል ይገ​ኛል። 25ግም​ቱም ሁሉ እንደ መቅ​ደሱ ሚዛን ይሆ​ናል፤ አንዱ ዲድ​ር​ክም ሃያ አቦሊ ይሆ​ናል።
26“ከእ​ን​ስ​ሳህ የሚ​ወ​ለድ በኵር ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ማንም ይለ​ው​ጠው ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው። 27የረ​ከ​ሰም እን​ስሳ ቢሆን እንደ ግምቱ ይቤ​ዠው፤ በእ​ር​ሱም የዋ​ጋ​ውን አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​ም​ር​በ​ታል፤ ባይ​ቤ​ዥም እንደ ግምቱ ይሸ​ጣል።
28“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ለየ እርም የሆነ ነገር ሁሉ፥ ሰው ቢሆን ወይም እን​ስሳ ወይም የር​ስቱ እርሻ ቢሆን፥ አይ​ሸ​ጥም፤ አይ​ቤ​ዥም፤ እርም የሆነ ነገር ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው። 29ከሰ​ዎ​ችም መባ ሆኖ የቀ​ረበ ሁሉ እስ​ኪ​ሞት ድረስ አይ​ቤ​ዥም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አይ​ቤ​ዥም ፈጽሞ ይገ​ደል” የሚል ይጨ​ም​ራል።
30“የም​ድ​ርም ዐሥ​ራት፥ ወይም የም​ድር ዘር፥ ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ነው። 31ሰውም ዐሥ​ራ​ቱን ሊቤዥ ቢወ​ድድ፥ አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​መ​ር​በ​ታል። 32ከበ​ሬም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ፥ ከበ​ግም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ፥ ከእ​ረ​ኛ​ውም በትር በታች ከሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል። 33መል​ካ​ሙን በክፉ፥ ክፉ​ው​ንም በመ​ል​ካም አይ​ለ​ውጥ፤ ቢለ​ው​ጠ​ውም እር​ሱና ልዋጩ የተ​ቀ​ደሱ ይሆ​ናሉ፤ አይ​ቤ​ዠ​ውም።”
34እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ተራራ ላይ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ዘንድ ሙሴን ያዘ​ዘው ትእ​ዛ​ዛት እነ​ዚህ ናቸው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ