የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 17

17
ደም መብ​ላት ስለ መከ​ል​ከሉ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው- 2“ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲህ ብለህ ንገር፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ይህ ነው፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ 3ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው በሬ፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ቢያ​ርድ፥ በሰ​ፈሩ ውስጥ ወይም ከሰ​ፈሩ ውጭ ቢያ​ር​ደው፥ 4ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው የተ​መ​ረጠ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም የድ​ኅ​ነት መሥ​ዋ​ዕት ያደ​ር​ገው ዘንድ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ባያ​መ​ጣው፥ በሌ​ላም ቦታ ቢያ​ር​ደው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ፊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ያቀ​ርብ ዘንድ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ባያ​መ​ጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈ​ጠ​ር​በ​ታል፤ ደም አፍ​ስ​ሶ​አ​ልና፤ ያም ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ። 5ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሜዳ የሚ​ያ​ር​ዱ​ትን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ያመ​ጡ​ታል፤ ወደ ካህ​ኑም አም​ጥ​ተው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለድ​ኅ​ነት መሥ​ዋ​ዕት ይሠ​ዉ​ታል። 6ካህ​ኑም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ባለው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደሙን ይረ​ጨ​ዋል፤ ስቡ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ያቃ​ጥ​ለ​ዋል። 7መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ው​ንም ደግሞ ተከ​ት​ለው ላመ​ነ​ዘ​ሩ​ባ​ቸው ለሰ​ይ​ጣ​ናት አይ​ሠዉ። ይህ ለእ​ነ​ርሱ ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።”
8ለእ​ነ​ርሱ እን​ዲህ በላ​ቸው፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም ሌላ መሥ​ዋ​ዕት ቢያ​ቀ​ርብ፥ 9ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዋ ዘንድ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ባያ​መ​ጣው፥ ያ ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።
10“ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚ​በ​ላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከ​ብ​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ያንም ሰው ከሕ​ዝቡ ለይች አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ። 11የሥጋ ሁሉ ሕይ​ወት ደሙ ነው፤ ደሙም ከሕ​ይ​ወቱ የተ​ነሣ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ልና በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ማስ​ተ​ስ​ረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእ​ና​ንተ ሰጠ​ሁት። 12ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች፦ ‘ከእ​ና​ንተ ማንም ደምን አይ​በ​ላም፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ች​ሁም ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማንም ደምን አይ​በ​ላም’ አልሁ።
13“ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው የሚ​በላ እን​ስሳ ወይም ወፍ እያ​ደነ ቢይዝ፥ ደሙን ያፈ​ስ​ሳል፤ በአ​ፈ​ርም ይከ​ድ​ነ​ዋል። 14የሥጋ ሁሉ ሕይ​ወት ደሙ ነውና፤ ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፦ የሥጋ ሁሉ ሕይ​ወት ደሙ ነውና የሥ​ጋ​ውን ሁሉ ደም አት​ብሉ፤ የሚ​በ​ላ​ውም ሁሉ ተለ​ይቶ ይጥፋ አል​ኋ​ቸው። 15የሞ​ተ​ውን ወይም አውሬ የሰ​በ​ረ​ውን የሚ​በላ ሰው ሁሉ፥ የሀ​ገር ልጅ ወይም እን​ግዳ ቢሆን፥ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆ​ናል፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጹሕ ይሆ​ናል። 16ልብ​ሱ​ንና ገላ​ውን ባያ​ጥብ ግን ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ