መጽሐፈ ኢዮብ 5
5
1“አሁንም የሚመልስልህ ካለ ጥራ፥
ከቅዱሳን መላእክትም የምታየው ካለ?
2ሰነፉን ሰው ቍጣ ይገድለዋልና፥
ቅንዓትም ሰነፉን ያጠፋዋል።
3ሰነፎችን ሥር ሰድደው አየኋቸው፥
በድንገትም መኖሪያቸው ጠፋች።
4ልጆቻቸው ከደኅንነት ርቀዋል፥
በበርም ውስጥ ይቀጠቅጡአቸዋል፤ መከራም ያጸኑባቸዋል፥
የሚታደጋቸውም የለም።
5እነርሱ የሰበሰቡትንም ጻድቃን ይበሉታል።
እነርሱን ግን ክፋት ቷጋቸዋለች፥
ኀይላቸውም ይደክማል።
6ችግር ከምድር አይወጣምና፥
መከራም ከተራሮች አይበቅልምና፤
7የአሞራ ግልገሎች ግን ወደ ላይ እየበረሩ ከፍ እንዲሉ፥
ሰው እንዲሁ ለድካም ተወልዶአል።
8“እኔ ግን እግዚአብሔርን እለምነው ነበር፥
የሁሉ ጌታ እግዚአብሔርንም እጠራው ነበር።
9እርሱ የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና
የማይቈጠረውን የከበረና ድንቅ ነገር ያደርጋል።
10በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥
ከሰማይም በታች ውኃን ይልካል።
11የተዋረዱትን ከፍ ያደርጋቸዋል፥
የወደቁትንም ያነሣቸዋል።
12የተንኰለኞችን ምክር ይለውጣል፥
እጆቻቸውም ቅን አይሠሩም።
13ጠቢባንንም በተንኰላቸው ይይዛቸዋል፤
ምክርን የሚጐነጉኑ ሰዎችን አሳብ ያጠፋል።
14በቀን ጨለማ ያገኛቸዋል፥
በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ።
15በጦርነት ይጠፋሉ፤
ደካማውም ከኀያሉ እጅ ያመልጣል።
16ለምስኪኑ ተስፋ አለውና፤
የዐመጸኛም አፍ ይዘጋልና።
17“ነገር ግን እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ብፁዕ ነው፤
ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን የአምላክን ተግሣጽ አትናቅ።
18እርሱ ይሰብራል፥ ዳግመኛም ይጠግናል፤
ይቀሥፋል፥ እጆቹም ይፈውሳሉ።
19ስድስት ጊዜ ከክፉ ነገር ያድንሃል፥
በሰባተኛውም ጊዜ ክፋት አትነካህም።
20በራብ ጊዜ ከሞት ያድንሃል፥
በጦርነትም ጊዜ ከሰይፍ እጅ ያድንሃል።
21ከምላስ ጅራፍ ይሰውርሃል፥
ከምትመጣብህም ክፋት አትፈራም።
22በኃጥኣንና በዐመጸኞች ላይ ትስቅባቸዋለህ፤
ከምድረ በዳ አራዊትም አትፈራም፤
23የምድረ በዳ አራዊትም ከአንተ ጋር ይስማማሉ።
24ያንጊዜ ቤትህ በሰላም እንዲሆን ታውቃለህ፤
ከንብረትህም አንዳች አይጐድልም።
25ዘርህም ብዙ እንዲሆን፥
ልጆችህም እንደ አማረ መስክ ሣር እንዲሆኑ ታውቃለህ።
26በወራቱ የደረሰ አዝመራ እንዲሰበሰብ፥
የእህሉ ነዶም በወቅቱ ወደ አውድማ እንዲገባ፥
በረዥም ዕድሜ ወደ መቃብር ትገባለህ።
27እነሆ፥ ይህን ዐውቀን መረመርን፥ የሰማነውም ይህ ነው፤
አንተ ግን አንዳች ሠርተህ እንደ ሆነ ለራስህ ዕወቅ።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 5: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ