የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 29

29
የኢ​ዮብ መጨ​ረሻ ንግ​ግር
1ኢዮ​ብም ምሳ​ሌ​ውን ይመ​ስል ዘንድ ደገመ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦
2“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቀኝ እንደ ነበ​ረው ጊዜ፥
ወደ ፊተ​ኛው ወራት ማን በመ​ለ​ሰኝ?
3በራ​ስ​ጌዬ ላይ መብ​ራቴ በበራ ጊዜ፥
እኔም ጨለ​ማ​ውን ዐልፌ በብ​ር​ሃኑ በሄ​ድሁ ጊዜ፥
4በበ​ረ​ከት ሁሉ በነ​በ​ርሁ ጊዜ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “መን​ገ​ዴን እከ​ተል በነ​በ​ርሁ ጊዜ” ይላል።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤቴን በጐ​በኘ ጊዜ፥
5ባለ ሀብት በነ​በ​ርሁ ጊዜ፥
ልጆ​ችም በዙ​ሪ​ያዬ በነ​በሩ ጊዜ፥
6ቅቤ በመ​ን​ገዴ ይፈ​ስስ በነ​በረ ጊዜ፥
ወተት በተ​ራ​ራዬ ይፈ​ስ​ስ​ልኝ በነ​በረ ጊዜ።
7ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገሥ​ግሼ በወ​ጣሁ ጊዜ፥
በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ወን​በ​ሬን ባኖ​ሩ​ልኝ ጊዜ፥
8ጐበ​ዛ​ዝት እኔን አይ​ተው ተሸ​ሸጉ፥
ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ቆሙ።
9ኀያ​ላ​ኑም ከመ​ና​ገር ዝም አሉ፥
እጃ​ቸ​ው​ንም በአ​ፋ​ቸው ላይ ጫኑ።
10የሰ​ሙ​ኝም ብፁዕ ይሉ​ኛል።
ምላ​ሳ​ቸ​ውም በት​ና​ጋ​ቸው ተጠጋ።
11የሰ​ማ​ች​ኝም ጆሮ ብፁዕ አለ​ችኝ፥
ያየ​ች​ኝም ዐይን ገለል አለች፤
12ድሃ​ውን ከሚ​ጨ​ቁ​ነው እጅ አድ​ኛ​ለ​ሁና።
ረዳት የሌ​ለ​ውን ደሃ​አ​ደ​ጉ​ንም ረድ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና።
13ለሞት የቀ​ረ​በው መረ​ቀኝ፤
የባ​ል​ቴ​ቲ​ቱም አፍ ባረ​ከኝ፤
14ጽድ​ቅን ለበ​ስሁ፥
ቅን​ነ​ት​ንም እንደ መጎ​ና​ጸ​ፊያ ተሸ​ለ​ምሁ፤
ፍር​ድ​ንም እንደ ኩፋር ተቀ​ዳ​ጀ​ኋት
15ለዕ​ው​ራን ዐይን፥
ለአ​ን​ካ​ሳ​ዎ​ችም እግር ነበ​ርሁ።
16ለድ​ሃ​ዎች አባት ነበ​ርሁ፥
የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ሰው ክር​ክር መረ​መ​ርሁ።
17የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችን መን​ጋጋ ሰበ​ርሁ፥
የነ​ጠ​ቁ​ት​ንም ከጥ​ር​ሳ​ቸው ውስጥ አስ​ጣ​ልሁ።
18እኔም እን​ደ​ም​ሸ​መ​ግ​ልና እን​ደ​ማ​ረጅ፥
እንደ ረዥም ዘን​ባ​ባም ረዥም ዘመን እን​ደ​ም​ኖር፥
እንደ አሸ​ዋም ዘመ​ኔን እን​ደ​ማ​በዛ ዐሰ​ብሁ።
19ውኃ በሥሬ ላይ ይፈ​ስ​ሳል፥
ጠልም በአ​ዝ​መ​ራዬ ላይ ይወ​ር​ዳል፤
20ክብሬ በእኔ ዘንድ ታድ​ሶ​አል፥
ቀስ​ቴም በእጄ ውስጥ ሳለ እሄ​ዳ​ለሁ።
21“ሰዎች እኔን ይሰ​ሙ​ኛል፥ ያዳ​ም​ጡ​ኝ​ማል፥
በም​ክ​ሬም ዝም ይላሉ።
22በነ​ገሬ ላይ ደግ​መው አይ​ና​ገ​ሩም፤
ባነ​ጋ​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውም ጊዜ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።
23የተ​ጠ​ማች ምድር ዝና​ምን ተስፋ እን​ደ​ም​ታ​ደ​ርግ፥
እን​ደ​ዚ​ሁም እነ​ርሱ ንግ​ግ​ሬን ይጠ​ባ​በ​ቃሉ።
24በእ​ነ​ርሱ ብስቅ አያ​ም​ኑም፤
የፊ​ቴም ብር​ሃን አል​ወ​ደ​ቀም።
25መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን መረ​መ​ርሁ፤
እንደ አለ​ቃም ሆኜ ተቀ​መ​ጥሁ፤
ንጉሥ በሠ​ራ​ዊቱ መካ​ከል እን​ደ​ሚ​ኖር ኖርሁ፤
በሚ​ያ​ዝ​ኑም ጊዜ በእኔ ይጽ​ናኑ ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ