የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 22:21-27

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 22:21-27 አማ2000

“አሁ​ንም መታ​ገሥ ትችል እንደ ሆነ፥ ፍሬ​ህም ይበጅ እንደ ሆነ እስኪ ጽኑ ሁን። ከአ​ፉም ሕጉን ተቀ​በል፥ በል​ብ​ህም ቃሉን አኑር፤ ብት​መ​ለስ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ራስ​ህን ብታ​ዋ​ርድ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ከል​ብህ ብታ​ርቅ፥ በዓ​ለቱ ቋጥኝ ላይ ለራ​ስህ መዝ​ገ​ብን ታኖ​ራ​ለህ። የሶ​ፎ​ርም ወርቅ እንደ ጅረት ድን​ጋይ ይሆ​ን​ል​ሃል። ሁሉን የሚ​ችል አም​ላ​ክም ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ይረ​ዳ​ሃል። ንጽ​ሕ​ና​ንም በእ​ሳት እንደ ተፈ​ተነ ብር አድ​ርጎ ይመ​ል​ስ​ል​ሃል። በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞገ​ስን ታገ​ኛ​ለህ። ወደ ሰማ​ይም በደ​ስታ ትመ​ለ​ከ​ታ​ለህ። ወደ እር​ሱም ትጸ​ል​ያ​ለህ፥ እር​ሱም ይሰ​ማ​ሃል፤ ስእ​ለ​ት​ህ​ንም ይሰ​ጠ​ሃል።