የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 14

14
1“ከሴት የተ​ወ​ለደ ሟች ሰው
የሕ​ይ​ወቱ ዘመን ጥቂት ነው፥
የቍጣ መከ​ራ​ንም የተ​ሞላ ነው።
2እንደ አበባ ይወ​ጣል፥ ይረ​ግ​ፋ​ልም፤
እንደ ጥላም ያል​ፋል፥ እር​ሱም አይ​ኖ​ርም።
3እን​ደ​ዚ​ህስ ያለ​ውን ሰው አንተ የም​ት​መ​ረ​ም​ረው አይ​ደ​ለ​ምን?
በፊ​ት​ህስ እር​ሱን ወደ ፍርድ ታገ​ባ​ዋ​ለ​ህን?
4ከር​ኵ​ሰት የሚ​ነጻ ማን ነው?
አንድ ስንኳ የለም።
5በም​ድር ላይ አንድ ቀንም እንኳ ቢኖር፤
ወሮ​ቹም በአ​ንተ ዘንድ የተ​ቈ​ጠሩ ናቸው፤
ዘመ​ኑ​ንም ወስ​ነህ ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም ከዚያ አያ​ል​ፍም።
6“እንደ ምን​ደኛ ሕይ​ወ​ቱን እን​ዲ​ጠ​ባ​በ​ቃት፥
ያርፍ ዘንድ ከእ​ርሱ ዘወር በል።
7ዛፍ ቢቈ​ረጥ ደግሞ ያቈ​ጠ​ቍጥ ዘንድ፥ ተስፋ አለው፤
ቅር​ን​ጫ​ፉም አያ​ል​ቅም።
8ሥሩም በም​ድር ውስጥ ቢያ​ረጅ፥
ግን​ዱም በጭ​ንጫ ውስጥ ቢሞት፥
9ከውኃ ሽታ የተ​ነሣ ያቈ​ጠ​ቍ​ጣል፤
እንደ አዲስ ተክ​ልም ያፈ​ራል።
10ሰው ግን ከሞተ ፈጽሞ ይተ​ላል፤
ሟች ሰው ከሞተ በኋላ እን​ግ​ዲህ አይ​ኖ​ርም።
11ባሕር ይጐ​ድ​ላል፤
ወን​ዙም ይነ​ጥ​ፋል፤ ይደ​ር​ቅ​ማል።
12ሰውም ከተኛ በኋላ
ሰማይ እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ አይ​ነ​ቃም፤
ከእ​ን​ቅ​ል​ፉም አይ​ነ​ሣም።
13“በመ​ቃ​ብር ውስጥ ምነው በጠ​በ​ቅ​ኸኝ ኖሮ!
ቍጣህ እስ​ኪ​በ​ር​ድም ድረስ በሸ​ሸ​ግ​ኸኝ ኖሮ!
እስ​ከ​ም​ታ​ስ​በ​ኝም ምነው ቀጠሮ በሰ​ጠ​ኸኝ ኖሮ!
14ሰው የሕ​ይ​ወ​ቱን ዘመን ፈጽሞ ከሞተ በኋላ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖር ቢሆን
ዳግ​መኛ እስ​ክ​ወ​ለድ ድረስ፥
በት​ዕ​ግ​ሥት በተ​ጠ​ባ​በ​ቅሁ ነበር።
15በጠ​ራ​ኸ​ኝም ጊዜ በመ​ለ​ስ​ሁ​ልህ ነበር፤
የእ​ጅ​ህ​ንም ሥራ አት​ና​ቀኝ።
16አሁን ግን ኀጢ​አ​ቶ​ችን ቈጥ​ረ​ሃል፤
ከበ​ደ​ሌም እን​ዲ​ቱ​ንስ እንኳ አል​ረ​ሳ​ህም።
17መተ​ላ​ለ​ፌን በከ​ረ​ጢት ውስጥ አት​መ​ሃል፥
ኀጢ​አ​ቴ​ንም ለብ​ጠ​ህ​ባ​ታል።
18ተራራ ሲወ​ድቅ ይጠ​ፋል፥
ዓለ​ቱም ከስ​ፍ​ራው ይፈ​ል​ሳል፤
19“ውኆች ድን​ጋ​ዮ​ችን ይፍ​ቃሉ፤
ፈሳ​ሾ​ቹም የም​ድ​ሩን አፈር ይወ​ስ​ዳሉ፤
እን​ዲሁ አንተ የሰ​ውን ተስፋ ታጠ​ፋ​ዋ​ለህ።
20ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታስ​ወ​ግ​ደ​ዋ​ለህ፥ እር​ሱም ያል​ፋል፤
ፊት​ህን ትመ​ል​ስ​በ​ታ​ለህ፥ እር​ሱ​ንም ትሰ​ድ​ደ​ዋ​ለህ።
21ልጆቹ ቢበዙ አያ​ያ​ቸ​ውም
ቢያ​ን​ሱም አያ​ው​ቃ​ቸ​ውም።
22ነገር ግን የገዛ ሥጋው በሕ​ማም ይሠ​ቃ​ያል፥
ነፍ​ሱም ታለ​ቅ​ሳ​ለች።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ