የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 19:31-42

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 19:31-42 አማ2000

አይ​ሁድ ግን የመ​ዘ​ጋ​ጀት ቀን ነበ​ርና፥ የዚ​ያች ሰን​በ​ትም ቀን ታላቅ ናትና “ሥጋ​ቸው በሰ​ን​በት በመ​ስ​ቀል ላይ አይ​ደር” አሉ፤ ጭን ጭና​ቸ​ው​ንም ሰብ​ረው ያወ​ር​ዷ​ቸው ዘንድ ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ኑት። ጭፍ​ሮ​ችም መጥ​ተው ከእ​ርሱ ጋር የተ​ሰ​ቀ​ሉ​ትን የአ​ን​ደ​ኛ​ው​ንና የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውን ጭኖች ሰበሩ። ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሄደው ፈጽሞ እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ጭኑን አል​ሰ​በ​ሩም። ነገር ግን ከጭ​ፍ​ሮቹ አንዱ የቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ያን​ጊ​ዜም ከእ​ርሱ ደምና ውኃ ወጣ። ያየ​ውም መሰ​ከረ፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም እው​ነት ነው፤ እር​ሱም እና​ንተ ልታ​ምኑ እው​ነት እን​ደ​ሚ​ና​ገር ያው​ቃል። ይህ ሁሉ የሆ​ነው “ከእ​ርሱ ዐፅ​ሙን አት​ስ​በሩ” ያለው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው። ሌላ​ዉም መጽ​ሐፍ ደግሞ“ የወ​ጉ​ትን ያዩ​ታል” ይላል። ከዚ​ህም በኋላ አይ​ሁ​ድን ስለ​ፈራ በስ​ውር የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ደቀ መዝ​ሙር የነ​በ​ረው የአ​ር​ማ​ት​ያስ ሰው ዮሴፍ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ይወ​ስድ ዘንድ ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ነው፤ ጲላ​ጦ​ስም ፈቀ​ደ​ለት። እር​ሱም ሄዶ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ወሰደ። ቀድሞ በሌ​ሊት ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሄዶ የነ​በ​ረው ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም መጣ፤ ቀብ​ተ​ውም የሚ​ቀ​ብ​ሩ​በ​ትን መቶ ወቄት የከ​ር​ቤና የሬት ቅል​ቅል ሽቶ አመጣ። እንደ አይ​ሁድ አገ​ና​ነዝ ሥር​ዐ​ትም የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ወስ​ደው ከሽቱ ጋር በበ​ፍታ ገነ​ዙት። በዚ​ያም በተ​ሰ​ቀ​ለ​በት ቦታ የአ​ት​ክ​ልት ስፍራ ነበር፤ በዚያ የአ​ት​ክ​ልት ስፍራ ውስ​ጥም በው​ስጡ ሰው ያል​ተ​ቀ​በ​ረ​በት አዲስ መቃ​ብር ነበር። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም በዚያ ቀበ​ሩት፤ ለአ​ይ​ሁድ የመ​ሰ​ና​ዳት ቀን ነበ​ርና፤ መቃ​ብ​ሩም ለሰ​ቀ​ሉ​በት ቦታ ቅርብ ነበር።