የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 10:11-18

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 10:11-18 አማ2000

“ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍ​ሱን ይሰ​ጣል። ጠባቂ ያይ​ደለ፥ በጎ​ቹም ገን​ዘቡ ያይ​ደሉ ምን​ደኛ ግን፥ ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎ​ቹን ትቶ ይሸ​ሻል፤ ተኵ​ላም መጥቶ በጎ​ችን ይነ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋል፥ ይበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ልም። ምን​ደ​ኛስ ይሸ​ሻል፤ ስለ በጎ​ችም አያ​ዝ​ንም፤ ምን​ደኛ ነውና። ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆ​ኑ​ትን መን​ጋ​ዎ​ችን አው​ቃ​ለሁ፤ የእኔ የሆ​ኑ​ትም ያው​ቁ​ኛል። አብ እኔን እን​ደ​ሚ​ያ​ው​ቀኝ እኔም አብን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ለበ​ጎ​ችም ቤዛ አድ​ርጌ ሰው​ነ​ቴን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ። ከዚህ ቦታ ያይ​ደሉ ሌሎች በጎ​ችም አሉኝ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ወደ​ዚህ አመ​ጣ​ቸው ዘንድ ይገ​ባ​ኛል፤ ቃሌ​ንም ይሰ​ሙ​ኛል፤ ለአ​ንድ እረ​ኛም አንድ መንጋ ይሆ​ናሉ። ስለ​ዚ​ህም፤ አብ ይወ​ድ​ደ​ኛል፥ እንደ ገና አስ​ነ​ሣት ዘንድ እኔ ነፍ​ሴን እሰ​ጣ​ለ​ሁና። ከእኔ ማንም አይ​ወ​ስ​ዳ​ትም፤ ነገር ግን እኔ በፈ​ቃዴ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ እኔ ላኖ​ራት ሥል​ጣን አለኝ፤ መልሼ እወ​ስ​ዳት ዘንድ ሥል​ጣን አለ​ኝና፤ ይህ​ንም ትእ​ዛዝ ከአ​ባቴ ተቀ​በ​ልሁ።”