ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 44

44
በግ​ብፅ ለሚ​ኖሩ አይ​ሁድ የተ​ነ​ገረ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል
1በግ​ብፅ ምድር በሚ​ግ​ዶ​ልና በጣ​ፍ​ናስ፥ በሜ​ም​ፎ​ስም፥ በፋ​ቱ​ራም ሀገር ስለ ተቀ​መጡ አይ​ሁድ ሁሉ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ 2“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ያመ​ጣ​ሁ​ትን ክፉ ነገር ሁሉ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ከክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ እነሆ ዛሬ ባድማ ሆነ​ዋል፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸ​ውም የለም። 3ይህም የሆ​ነው ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ስላ​ደ​ረ​ጉት ክፋት፥ እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸው ለማ​ያ​ው​ቁ​አ​ቸው ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ያጥኑ ዘንድ፥ ያመ​ል​ኳ​ቸ​ውም ዘንድ ስለ​ሄዱ ነው። 4በማ​ለ​ዳም ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ላክ​ሁ​ባ​ቸው፤ የጠ​ላ​ሁ​ት​ንም ርኩስ ነገር አታ​ድ​ርጉ ብዬ ላክ​ሁ​ባ​ቸው። 5ነገር ግን አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ ከክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ተመ​ል​ሰው ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት እን​ዳ​ያ​ጥኑ ጆሮ​አ​ቸ​ውን አል​መ​ለ​ሱም። 6ስለ​ዚህ መዓ​ቴና መቅ​ሠ​ፍቴ ወረደ፤ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ነደደ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ጠፍና ባድማ ሆኑ።
7“አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከይ​ሁዳ ወገን መካ​ከል ቅሬታ እን​ዳ​ይ​ቀ​ር​ላ​ችሁ፥ ወን​ድ​ንና ሴትን፥ ብላ​ቴ​ና​ንና የሚ​ጠባ ሕፃ​ንን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ታጠፉ ዘንድ ይህን ታላቅ ክፋት በራ​ሳ​ችሁ ላይ ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? 8ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ታጠፉ ዘንድ፥ በም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል መረ​ገ​ሚ​ያና መሰ​ደ​ቢያ ትሆኑ ዘንድ፥ ለመ​ቀ​መጥ በገ​ባ​ች​ሁ​ባት በግ​ብፅ ምድር ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት በማ​ጠ​ና​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ለምን ታስ​ቈ​ጡ​ኛ​ላ​ችሁ? 9በውኑ በይ​ሁዳ ምድ​ርና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ያደ​ረ​ጉ​ትን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ክፋት፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ነገ​ሥ​ታት ክፋት፥ የአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ክፋት#“የአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ክፋት” የሚ​ለው በዕብ. የለም። “የሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ክፋት፥ የእ​ና​ን​ተ​ንም ክፋት” የሚል ዕብ. ይጨ​ም​ራል። የሚ​ስ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ክፋት ረስ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልን?። 10እስከ ዛሬም ድረስ አላ​ረ​ፉም፤ አል​ፈ​ሩ​ምም፤ በእ​ና​ን​ተና በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ፊት ባኖ​ር​ሁት ሕጌና ሥር​ዐቴ አል​ሄ​ዱም።
11“ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይሁ​ዳን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በግ​ብፅ ያሉ የአ​ይ​ሁ​ድን ቅሬታ” ይላል። ሁሉ አጠፋ ዘንድ፥ ፊቴን ለክ​ፋት በላ​ያ​ችሁ አደ​ር​ጋ​ለሁ። 12ወደ ግብ​ፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚ​ያም ይቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ቸ​ውን ያቀ​ኑ​ትን የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ሁሉም ይጠ​ፋሉ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ይወ​ድ​ቃሉ፤ በሰ​ይ​ፍና በራብ ይጠ​ፋሉ፤ ከታ​ና​ሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ ይሞ​ታሉ፤ ለጥ​ላ​ቻና ለጥ​ፋት፥ ለመ​ረ​ገ​ሚ​ያና ለመ​ሰ​ደ​ቢያ ይሆ​ናሉ። 13ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በመ​ዐት እንደ ጐበ​ኘሁ፥ እን​ዲሁ በግ​ብፅ ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በሰ​ይ​ፍና በራብ በቸ​ነ​ፈ​ርም እጐ​በ​ኛ​ለሁ። 14በዚያ ለመ​ቀ​መጥ በል​ባ​ቸው ተስፋ ወደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጓት ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ለሱ ዘንድ በግ​ብፅ ለመ​ኖር ከመጡ ከይ​ሁዳ ቅሬታ ወገን የሚ​ያ​መ​ል​ጥና የሚ​ቀር፥ ወደ​ዚ​ያም የሚ​መ​ለስ አይ​ኖ​ርም፤ ከሚ​ያ​መ​ል​ጥም በቀር ማንም አይ​መ​ለ​ስም።”
15ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ማጠ​ና​ቸ​ውን ያወቁ ሰዎች ሁሉ፥ በዚ​ያም የቆሙ ሴቶች ሁሉ፥ በግ​ብ​ፅም ምድር በጳ​ት​ሮስ የተ​ቀ​መጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ለኤ​ር​ም​ያስ መለ​ሱ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አሉ፦ 16“አንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የነ​ገ​ር​ኸ​ንን ቃል አን​ሰ​ማም። 17ነገር ግን እኛና አባ​ቶ​ቻ​ችን፥ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ እና​ደ​ር​ገው እንደ ነበረ፥ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እና​ጥን ዘንድ፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን እና​ፈ​ስ​ስ​ላት ዘንድ ከአ​ፋ​ችን የወ​ጣ​ውን ቃል ሁሉ በር​ግጥ እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ በዚያ ጊዜም እን​ጀ​ራን እን​ጠ​ግብ ነበር፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ልን ነበር፤ ክፉም አና​ይም ነበር። 18ለሰ​ማይ ንግ​ሥት ማጠ​ንን፥ ለእ​ር​ስ​ዋም የመ​ጠ​ጥን ቍር​ባን ማፍ​ሰ​ስን ከተ​ውን ወዲህ ግን፥ እኛ ሁላ​ችን አን​ሰ​ናል፤ በሰ​ይ​ፍና በራ​ብም አል​ቀ​ናል። 19እኛስ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት ባጠ​ን​ን​ላት፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን ባፈ​ሰ​ስ​ን​ላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎ​ቻ​ችን ምስ​ል​ዋን ለማ​በ​ጀት እን​ጎቻ አድ​ር​ገ​ን​ላት ኖሮ​አ​ልን? የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን አፍ​ስ​ሰ​ን​ላት ኖሮ​አ​ልን?”
20ኤር​ም​ያ​ስም ይህን ቃል ለመ​ለ​ሱ​ለት ሕዝብ ሁሉ፦ ለወ​ን​ዶ​ቹና ለሴ​ቶቹ፥ ለሕ​ዝ​ቡም ሁሉ መለ​ሰ​ላ​ቸው እን​ዲ​ህም አለ፦ 21“እና​ን​ተና አባ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ሁም የም​ድ​ርም ሕዝብ በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ያጠ​ና​ች​ሁ​ትን ዕጣን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሰ​በው፥ በል​ቡም ያኖ​ረው አይ​ደ​ለ​ምን? 22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የሥ​ራ​ች​ሁን ክፋ​ትና ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን ርኵ​ሰት ይታ​ገሥ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ስለ​ዚህ ምድ​ራ​ችሁ ባድማ፥ በረ​ሃና መረ​ገ​ሚያ ሆና​ለች፤ እስከ ዛሬም የሚ​ኖ​ር​ባት የለም። 23ስላ​ጠ​ና​ች​ሁት ዕጣን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ላይ ስለ በደ​ላ​ችሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ስላ​ል​ሰ​ማ​ችሁ፥ በሕ​ጉና በሥ​ር​ዐ​ቱም፥ በም​ስ​ክ​ሩም ስላ​ል​ሄ​ዳ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ ዛሬ እንደ ሆነ ይች ክፉ ነገር አግ​ኝ​ታ​ች​ኋ​ለች።”
24ኤር​ም​ያ​ስም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ ለሴ​ቶ​ቹም ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “በግ​ብፅ ምድር የም​ት​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። 25የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ን​ተና ሚስ​ቶ​ቻ​ችሁ በአ​ፋ​ችሁ፦ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እና​ጥን ዘንድ፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን እና​ፈ​ስ​ስ​ላት ዘንድ የተ​ሳ​ል​ነ​ውን ስእ​ለ​ታ​ች​ንን በር​ግጥ እን​ፈ​ጽ​ማ​ለን አላ​ችሁ፤ በእ​ጃ​ች​ሁም አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት፤ እን​ግ​ዲህ ስእ​ለ​ታ​ች​ሁን አጽኑ፤ ስእ​ለ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈጽሙ። 26ስለ​ዚህ እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር የም​ት​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ በሚ​ኖር በይ​ሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፦ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ተብሎ እን​ዳ​ይ​ጠራ፥ እነሆ በታ​ላቁ ስሜ ምያ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​እ​ብ​ሔር። 27እነሆ ለመ​ል​ካም ሳይ​ሆን ለክ​ፋት እተ​ጋ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ያሉት የይ​ሁዳ ሰዎች ሁሉ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ ያል​ቃሉ። 28ከሰ​ይ​ፍም የሚ​ያ​መ​ልጡ በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሰዎች ከግ​ብፅ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ለ​ሳሉ፤ ሊቀ​መ​ጡም ወደ ግብፅ ምድር የገ​ቡት የይ​ሁዳ ቅሬታ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእ​ነ​ርሱ የማ​ና​ችን ቃል እን​ዲ​ጸና ያው​ቃሉ።
29“ቃሌም በላ​ያ​ችሁ ለክ​ፋት እን​ዲ​ጸና ታውቁ ዘንድ በዚች ስፍራ በክፉ እን​ደ​ም​ጐ​በ​ኛ​ችሁ ምል​ክ​ታ​ችሁ ይህ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 30እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን ጠላቱ ለሆ​ነው፥ ነፍ​ሱ​ንም ለፈ​ለ​ገው ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፌ እንደ ሰጠ​ሁት፥ እን​ዲሁ እነሆ የግ​ብ​ፅን ንጉሥ ፈር​ዖን ሖፍ​ራን ለጠ​ላ​ቶቹ፥ ነፍ​ሱ​ንም ለሚ​ፈ​ልጉ እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።#ምዕ. 44 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 51 ከቍ. 1 እስከ 30 ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ