ትንቢተ ኤርምያስ 43
43
ኤርምያስ ወደ ግብፅ እንደ ተወሰደ
1የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ፥ ለእነርሱ አምላካቸው እግዚአብሔር የላከውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ መናገርን በፈጸመ ጊዜ እንዲህ ሆነ፤ 2የኢዮስያስ#ዕብ. “ሆሻያ” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “ማሲያ” ይላል። ልጅ ኣዛርያስ፥ የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ ትዕቢተኞችም ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን፥ “ሐሰት ተናግረሃል፤ አምላካችን እግዚአብሔር፦ በዚያ ትቀመጡ ዘንድ ወደ ግብፅ አትግቡ ብሎ አልላከህም፤ 3ነገር ግን ከለዳውያን እንዲገድሉን ወደ ባቢሎንም እንዲያፈልሱን በእጃቸው አሳልፈህ ትሰጠን ዘንድ የኔርዩ ልጅ ባሮክ በላያችን ላይ አነሣሥቶሃል” አሉት።
4የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ የጭፍራ አለቆችም ሁሉ፥ ሕዝቡም ሁሉ በይሁዳ ምድር ይቀመጡ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም። 5የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ የጭፍራ አለቆችም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ ከተሰደዱባቸው ከአሕዛብ ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታ ሁሉ ወሰዱ። 6ወንዶችንና ሴቶችን፥ ሕፃናቱንም፥ የንጉሡንም ሴቶች ልጆች፥ የአዛዦችም አለቃ ናቡዛርዳን ከሳፋን ልጅ ከአኪቃም ልጅ ከጎዶልያስ ጋር የተዋቸውን ሰዎች ሁሉ፥ ነቢዩ ኤርምያስንና የኔርዩን ልጅ ባሮክንም ወሰዱ። 7የእግዚአብሔርንም ቃል አልሰሙምና ወደ ግብፅ ምድር ገቡ፤ እስከ ጣፍናስ ድረስም መጡ።
8በጣፍናስም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ 9“ታላላቆችን ድንጋዮች በእጅህ ውሰድ፥ የይሁዳም ሰዎች እያዩ በጣፍናስ ባለው በፈርዖን ቤት ደጅ መግቢያ ሸሽጋቸው። 10እንዲህም በላቸው፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባሪያዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን አመጣለሁ፤ ዙፋኑንም እኔ በሸሸግኋቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ አኖራለሁ፤ ጋሻዎቹንም በእነርሱ ላይ ያነሣል።#ዕብ. “እርሱም ማለፊያውን ድንኳኑን በላያቸው ይዘረጋል” ይላል። 11መጥቶም የግብፅን ምድር ይመታል፤ ለሞትም የሚሆነውን ለሞት፥ ለምርኮም የሚሆነውን ለምርኮ፥ ለሰይፍም የሚሆነውን ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል። 12በግብፅም አማልክት ቤቶች እሳትን ያነድዳል፤ ያቃጥላቸውማል፤ ይማርካቸውማል፤ እረኛም ልብሱን እንደሚቀምል እንዲሁ የግብፅን ሀገር ይቀምላታል፤#ዕብ. “እረኛ ደበሎውን እንደሚደርብ እንዲሁ የግብፅን አገር ይደርባል” ይላል። ከዚያም በሰላም ይወጣል። 13በግብፅ ምድርም ያለውን የፀሐይ ከተማ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኦን” ይላል። ምሰሶዎችን ይሰብራል፥ የግብፅንም አማልክት ቤቶች በእሳት ያቃጥላል።”#ምዕ. 43 በግሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 50 ነው።
Currently Selected:
ትንቢተ ኤርምያስ 43: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ