የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 34

34
በሴ​ዴ​ቅ​ያስ ላይ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
1የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርና ሠራ​ዊቱ ሁሉ፥ ከእ​ጁም ግዛት በታች ያሉ የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ፥ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች ሁሉ ይወጉ በነ​በረ ጊዜ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ 2“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሂድ፤ ለይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ለሴ​ዴ​ቅ​ያስ ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይች ከተማ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ተላ​ልፋ ትሰ​ጣ​ለች፤ ይይ​ዛ​ታል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ላ​ታል። 3አን​ተም በር​ግጥ ትያ​ዛ​ለህ፤ በእ​ጁም አል​ፈህ ትሰ​ጣ​ለህ እንጂ ከእጁ አታ​መ​ል​ጥም፤ ዐይ​ን​ህም የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ዐይን ታያ​ለች፤ እር​ሱም ከአ​ንተ ጋር አፍ ለአፍ ይና​ገ​ራል፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ትገ​ባ​ለህ።
4“ነገር ግን የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አንተ እን​ዲህ ይላል፦ በሰ​ይፍ አት​ሞ​ትም፤ 5ነገር ግን በሰ​ላም ትሞ​ታ​ለህ፥ ከአ​ንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገ​ሥ​ታት አባ​ቶ​ችህ እሳት ይቃ​ጠ​ል​ላ​ቸው እንደ ነበር እን​ዲሁ ያቃ​ጥ​ሉ​ል​ሃ​ልና፦ ወየው! ጌታ ሆይ! እያሉ ያለ​ቅ​ሱ​ል​ሃል፤ እኔ ቃልን ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
6ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም ይህን ቃል ሁሉ ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሴ​ዴ​ቅ​ያስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነገ​ረው። 7የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ሠራ​ዊት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና የቀ​ሩ​ትን የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች ሁሉ፥ ለኪ​ሶ​ንና አዚ​ቃ​ንም ይወጋ ነበር። እነ​ዚህ የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች በይ​ሁዳ ከተ​ሞች መካ​ከል ቀር​ተው ነበ​ርና።
ስለ አገ​ል​ጋ​ዮች ነጻ​ነት
8ስለ አር​ነ​ታ​ቸው ዐዋጅ እን​ዲ​ነ​ግር ንጉሡ ሴዴ​ቅ​ያስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን ከአ​ደ​ረገ በኋላ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው ቃል ይህ ነው። 9ሰው ሁሉ ዕብ​ራዊ የሆነ ወንድ ባሪ​ያ​ው​ንና ዕብ​ራ​ዊት የሆ​ነች ሴት ባሪ​ያ​ውን አር​ነት እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ አይ​ሁ​ዳዊ ወን​ድ​ሙ​ንም ማንም እን​ዳ​ይ​ገዛ፤ 10ሰው ሁሉ ወንድ ባሪ​ያ​ው​ንና ሴት ባሪ​ያ​ውን አር​ነት እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ማንም እን​ዳ​ይ​ገ​ዛ​ቸው ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለ​ቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ፤ አር​ነ​ትም አወ​ጡ​አ​ቸው። 11ነገር ግን ከዚያ በኋላ ተመ​ል​ሰው አር​ነት ያወ​ጡ​አ​ቸ​ውን ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን አስ​መ​ለሱ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችም አድ​ር​ገው ገዙ​አ​ቸው።
12ስለ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 13“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ ሀገር በአ​ወ​ጣ​ኋ​ቸው ቀን ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዲህ ስል ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግሁ፦ 14ስድ​ስት#ዕብ. “ሰባት” ይላል። ዓመት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ የተ​ሸ​ጠ​ላ​ች​ሁን፥ ስድ​ስ​ትም ዓመት የተ​ገ​ዛ​ላ​ች​ሁን ዕብ​ራዊ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ አር​ነት ታወ​ጡ​ታ​ላ​ችሁ፤ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ግን አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም። 15እና​ን​ተም ዛሬ ተመ​ል​ሳ​ችሁ ሰው ሁሉ ባል​ን​ጀ​ራ​ውን አር​ነት ለማ​ው​ጣት ዓመተ ኅድ​ገ​ትን በማ​ድ​ረግ በዐ​ይኔ ፊት ቅን የሆ​ነ​ውን ነገር አድ​ር​ጋ​ችሁ ነበር፤ ስሜም በሚ​ጠ​ራ​በት ቤት ውስጥ በፊቴ ቃል ኪዳን አድ​ር​ጋ​ችሁ ነበር። 16ነገር ግን ተመ​ል​ሳ​ችሁ ስሜን አስ​ነ​ቀ​ፋ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም በፈ​ቃ​ዳ​ቸው እን​ዲ​ሄዱ አር​ነት ያወ​ጣ​ች​ኋ​ቸ​ውን ወን​ድና ሴት ባሪ​ያ​ዎ​ቻ​ች​ሁን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎች እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ መለ​ሳ​ች​ኋ​ቸው።”
17ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰው ሁሉ ለወ​ን​ድ​ሙና ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ዓመተ ኅድ​ገ​ትን ለማ​ድ​ረግ እኔን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እነሆ እኔ ለሰ​ይ​ፍና ለቸ​ነ​ፈር፥ ለራ​ብም ዓመተ ኅድ​ገ​ትን አው​ጅ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በም​ድ​ርም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ። 18ቃል ኪዳ​ኔን የተ​ላ​ለ​ፉ​ትን ሰዎች፥ በፊቴ ያደ​ረ​ጉ​ትን ቃል ኪዳን ያል​ፈ​ጸ​ሙ​ትን፥ እን​ቦ​ሳ​ው​ንም ቈር​ጠው በቍ​ራጩ መካ​ከል ያለ​ፉ​ትን#“ቈር​ጠው በቍ​ራጩ መካ​ከል ያለ​ፉ​ትን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ። 19የይ​ሁ​ዳን አለ​ቆ​ችና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን አለ​ቆች፥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ች​ንና#“የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አለ​ቆች ጃን​ደ​ረ​ቦ​ችን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ካህ​ና​ት​ንም፥ በእ​ን​ቦ​ሳም ቍራጭ#“በእ​ን​ቦ​ሳም ቁራጭ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። መካ​ከል ያለ​ፉ​ትን የሀ​ገ​ሩን ሕዝብ ሁሉ፥ 20ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ለሚ​ሹ​አት#“ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ለሚ​ሹ​አት” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ሬሳ​ቸ​ውም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናል። 21የይ​ሁ​ዳ​ንም ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና መኳ​ን​ን​ቱን ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ለሚ​ሹ​አት እጅ#“ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ለሚ​ሹ​አት እጅ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ከእ​ና​ን​ተም ለተ​መ​ለ​ሱት ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ። 22እነሆ እኔ አዝ​ዛ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ወደ​ዚ​ህ​ችም ሀገር እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይወ​ጋሉ፤ ይይ​ዙ​አ​ት​ማል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ታል፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ሰው የሌ​ለ​በት ባድማ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።”#ምዕ. 34 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 41 ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ