የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 35

35
ኤር​ም​ያ​ስና ሬካ​ባ​ው​ያን
1በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፤ እን​ዲህ ሲል፦ 2“ወደ ሬካ​ባ​ው​ያን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አር​ካ​ባ​ያ​ው​ያን” ይላል። ቤት ሄደህ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አም​ጥ​ተህ ከክ​ፍ​ሎቹ ወደ አን​ዲቱ አግ​ባ​ቸው፤ የወ​ይን ጠጅም አጠ​ጣ​ቸው።” 3የከ​ባ​ስ​ንን ልጅ የኤ​ር​ም​ያ​ስን ልጅ ያእ​ዛ​ን​ያ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም፥ ልጆ​ቹ​ንም ሁሉ የሬ​ካ​ባ​ው​ያ​ንን ቤተ ሰብእ ሁሉ ወሰ​ድ​ኋ​ቸው፤ 4ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በበ​ረ​ኛው በሰ​ሎም ልጅ በማ​ሴው ጓዳ በላይ ባለው በአ​ለ​ቆቹ ጓዳ አጠ​ገብ ወደ አለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ጎዶ​ልያ ልጅ ወደ ሐና​ንያ ልጆች ጓዳ አገ​ባ​ኋ​ቸው። 5በሬ​ካ​ባ​ው​ያ​ንም ልጆች ፊት የወ​ይን ጠጅ የሞ​ላ​ባ​ቸ​ውን ማድ​ጋ​ዎ​ች​ንና ጽዋ​ዎ​ችን አኑሬ፥ “የወ​ይ​ኑን ጠጅ ጠጡ” አል​ኋ​ቸው።
6እነ​ርሱ ግን እን​ዲህ አሉ፥ “የወ​ይ​ኑን ጠጅ አን​ጠ​ጣም፤ አባ​ታ​ችን የሬ​ካብ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ እና​ን​ተና ልጆ​ቻ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የወ​ይን ጠጅ አት​ጠጡ ብሎ አዝ​ዞ​ና​ልና። 7በም​ት​ኖ​ሩ​ባት ምድር ላይ ብዙ ዘመን እን​ድ​ት​ኖሩ፥ በዕ​ድ​ሜ​አ​ችሁ ሙሉ በድ​ን​ኳን ውስጥ ተቀ​መጡ እንጂ ቤትን አት​ሥሩ፤ ዘር​ንም አት​ዝሩ፤ ወይ​ንም አት​ት​ከሉ፤ አን​ዳ​ችም አይ​ሁ​ን​ላ​ችሁ። 8እኛም የአ​ባ​ታ​ች​ንን የሬ​ካብ ልጅ የኢ​ዮ​ና​ዳ​ብን ቃል ባዘ​ዘን ነገር ሁሉ ታዝ​ዘ​ናል፤ እኛም ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ንም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ንም ዕድ​ሜ​አ​ች​ንን ሙሉ የወ​ይን ጠጅ አል​ጠ​ጣ​ንም፤ 9የም​ን​ቀ​መ​ጥ​በ​ት​ንም ቤት አል​ሠ​ራ​ንም፤ የወ​ይን ቦታና እርሻ፥ ዘርም የለ​ንም። 10በድ​ን​ኳን ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ናል፤ አባ​ታ​ች​ንም ኢዮ​ና​ዳብ ያዘ​ዘ​ንን ሁሉ ሰም​ተ​ናል፤ አድ​ር​ገ​ና​ልም። 11ነገር ግን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዚች ምድር ላይ በዘ​መተ ጊዜ፦ ኑ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሠራ​ዊ​ትና ከሶ​ርያ ሠራ​ዊት ፊት የተ​ነሣ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ሂድ፤ አልን፤ እን​ዲ​ሁም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መ​ጥን።”
12የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 13“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሂድና ለይ​ሁዳ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሚ​ቀ​መጡ ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ቃሌን ትሰሙ ዘንድ ተግ​ሣ​ጽን አት​ቀ​በ​ሉ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 14የሬ​ካብ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ ልጆቹ የወ​ይን ጠጅ እን​ዳ​ይ​ጠጡ ያዘ​ዛ​ቸው ቃል ተፈ​ጸመ፤ ለአ​ባ​ታ​ቸ​ውም ትእ​ዛዝ ታዝ​ዘ​ዋ​ልና እስከ ዛሬ ድረስ ወይን አይ​ጠ​ጡም፤ እኔም በማ​ለዳ ስለ እና​ንተ ተና​ገ​ርሁ፤ ሆኖም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም። 15ደግ​ሞም፦ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ሥራ​ች​ሁ​ንም አሳ​ምሩ፤ ታገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ከ​ተሉ፤ ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ሁት ምድር ትቀ​መ​ጣ​ላ​ችሁ እያ​ልሁ ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ልኬ​ባ​ችሁ ነበር፤ እና​ንተ ግን ጆሮ​አ​ች​ሁን አላ​ዘ​ነ​በ​ላ​ች​ሁም፤ እኔ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም። 16የሬ​ካብ ልጅ የኢ​ዮ​ና​ዳብ ልጆች አባ​ታ​ቸው ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ትእ​ዛዝ ፈጽ​መ​ዋል፤ ይህ ሕዝብ ግን አል​ሰ​ማ​ኝም፤ 17ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በተ​ና​ገ​ር​ኋ​ቸው ጊዜ አል​ሰ​ሙ​ምና፥ በጠ​ራ​ኋ​ቸ​ውም ጊዜ#“አል​ሰ​ሙ​ምና በጠ​ራ​ኋ​ቸ​ውም ጊዜ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። አል​መ​ለ​ሱ​ል​ኝ​ምና የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ባ​ቸ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ በይ​ሁዳ ላይ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በሚ​ቀ​መጡ ሁሉ ላይ አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።”
18ኤር​ም​ያ​ስም ሬካ​ባ​ው​ያ​ንን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ባ​ታ​ች​ሁን የኢ​ዮ​ና​ዳ​ብን ትእ​ዛዝ ሰም​ታ​ች​ኋ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ሁሉ ጠብ​ቃ​ች​ኋ​ልና፥ ያዘ​ዛ​ች​ሁ​ንም ሁሉ አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ 19ስለ​ዚህ በፊቴ የሚ​ቆም ሰው ከሬ​ካብ ልጅ ከኢ​ዮ​ና​ዳብ ወገን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ታ​ጣም፥” ይላል የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።#ምዕ. 35 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 42 ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ