የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 33

33
ሁለ​ተ​ኛው አስ​ተ​ማ​ማኝ ተስፋ
1ኤር​ም​ያስ ገና በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ታስሮ ሳለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሁለ​ተኛ ጊዜ እን​ዲህ ሲል መጣ​ለት፦ 2“ስሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ፥ ምድ​ርን የፈ​ጠ​ራት፥ የሠ​ራ​ትና ያጸ​ናት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ 3ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም የማ​ታ​ው​ቀ​ውን ታላ​ቅና ኀይ​ለኛ ነገ​ርን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ። 4የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ሽ​ግና ለመ​ከ​ላ​ከያ ስለ ፈረ​ሱት ስለ​ዚ​ህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት ቤቶች እን​ዲህ ይላ​ልና፦ 5የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ተዋ​ጊ​ዎች ለመ​ዋ​ጋት መጥ​ተ​ዋል፤ ነገር ግን በቍ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ በገ​ደ​ል​ኋ​ቸው ሰዎች ሬሳ​ዎች እሞ​ላ​ታ​ለሁ፥ ስለ ክፋ​ታ​ቸው ሁሉ ፊቴን ከዚ​ህች ከተማ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከእ​ነ​ርሱ እመ​ለ​ሳ​ለሁ” ይላል። እመ​ል​ሳ​ለሁ። 6እነሆ ፈው​ስ​ንና መድ​ኀ​ኒ​ትን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ እፈ​ው​ሳ​ታ​ለ​ሁም፤ የሰ​ላ​ም​ንና የእ​ው​ነ​ት​ንም መን​ገድ እገ​ል​ጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ። 7የይ​ሁ​ዳን ምር​ኮ​ኞች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ምር​ኮ​ኞች እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ቀድ​ሞም እንደ ነበሩ አድ​ርጌ እሠ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ። 8እኔ​ንም ከበ​ደ​ሉ​በት ኀጢ​አት ሁሉ አነ​ጻ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔም የበ​ደ​ሉ​ኝ​ንና ያመ​ፁ​ብ​ኝን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይቅር እላ​ለሁ። 9ይህ​ችም ከተማ እኔ የም​ሠ​ራ​ላ​ቸ​ውን በጎ​ነት ሁሉ በሚ​ሰሙ፥ እኔም ስላ​መ​ጣ​ሁ​ላ​ቸው በጎ​ነ​ትና ሰላም ሁሉ በሚ​ፈ​ሩና በሚ​ደ​ነ​ግጡ አሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ለደ​ስታ፥ ለክ​ብ​ርና ለገ​ና​ን​ነት ትሆ​ና​ለች።”
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እና​ንተ፦ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ያለች ባድማ ናት በም​ት​ሉ​አት በዚች ስፍራ፥ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው በሌለ፥ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ባድማ በሆኑ በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ፥ 11የሐ​ሤት ድም​ፅና የደ​ስታ ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽራ ድም​ፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የም​ስ​ጋ​ናን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​መጡ ሰዎች ድምፅ እንደ ገና ይሰ​ማል። የዚ​ያ​ችን ምድር ምር​ኮ​ኞች ቀድሞ እንደ ነበረ አድ​ርጌ እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 12የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ባድማ ሆኖ፥ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ባለው በዚህ ስፍራ በከ​ተ​ሞ​ችም ሁሉ መን​ጎ​ቻ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ሳ​ር​ፉ​በት የእ​ረ​ኞች መኖ​ሪያ ይሆ​ናል። 13በደ​ጋው ላይ ባሉ ከተ​ሞች፥ በቆ​ላ​ውም ባሉ ከተ​ሞች፥ በደ​ቡ​ብም ባሉ ከተ​ሞች፥ በብ​ን​ያ​ምም ሀገር፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ባሉ ስፍ​ራ​ዎች፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች በጎቹ በተ​ቈ​ጣ​ጣ​ሪ​ያ​ቸው እጅ እንደ ገና ያል​ፋሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”
14“እነሆ ስለ እስ​ራ​ኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የሰ​ጠ​ሁ​ትን መል​ካም የተ​ስፋ ቃል የም​ፈ​ጽ​ም​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 15በዚ​ያም ዘመን በዚ​ያም ጊዜ ለዳ​ዊት የጽ​ድ​ቅን ቍጥ​ቋጥ አበ​ቅ​ል​ለ​ታ​ለሁ፤ እር​ሱም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን በም​ድር ያደ​ር​ጋል። 16በዚ​ያም ዘመን ይሁዳ ይድ​ናል፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተዘ​ልላ ትቀ​መ​ጣ​ለች፤ የም​ት​ጠ​ራ​በ​ትም ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቃ​ችን ተብሎ ነው። 17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መጥ ሰው ከዳ​ዊት ዘንድ አይ​ታ​ጣም። 18የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርብ፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን የሚ​ያ​ቃ​ጥል፥ ሁል​ጊ​ዜም የሚ​ሠዋ ሰው ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ዘንድ በእኔ ፊት አይ​ታ​ጣም።”
19የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 20“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ቀንና ሌሊት በወ​ራ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሆኑ የቀን ቃል ኪዳ​ኔ​ንና የሌ​ሊት ቃል ኪዳ​ኔን ማፍ​ረስ ብት​ችሉ፥ 21በዙ​ፋኑ ላይ የሚ​ነ​ግሥ ልጅ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ለት ከባ​ሪ​ያዬ ከዳ​ዊት ጋር፥ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈ​ር​ሳል። 22የሰ​ማ​ይን ሠራ​ዊት መቍ​ጠር፥ የባ​ሕ​ር​ንም አሸዋ መስ​ፈር እን​ደ​ማ​ይ​ቻል፥ እን​ዲሁ የባ​ሪ​ያ​ዬን የዳ​ዊ​ትን ዘርና የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ኝን ሌዋ​ው​ያ​ንን አበ​ዛ​ለሁ።”
23የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 24“ይህ ሕዝብ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ወገን ጥሎ​አ​ቸ​ዋል፥ እን​ዲሁ በፊ​ታ​ቸው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ሕዝብ እን​ዳ​ይ​ሆን ሕዝ​ቤን አቃ​ል​ለ​ዋል ያለ​ውን ነገር አት​መ​ለ​ከ​ት​ምን? 25እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የቀ​ንና የሌ​ሊት ቃል ኪዳ​ኔን የሰ​ማ​ይ​ንና የም​ድ​ር​ንም ሥር​ዐት ያላ​ጸ​ናሁ እንደ ሆነ፥ 26እኔም ደግሞ በአ​ብ​ር​ሃ​ምና በይ​ስ​ሐቅ በያ​ዕ​ቆ​ብም ዘር ላይ ገዢ​ዎች ይሆኑ ዘንድ ከዘሩ እን​ዳ​ላ​ስ​ነሣ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንና የባ​ሪ​ያ​ዬን የዳ​ዊ​ትን ዘር እጥ​ላ​ለሁ፤ ምር​ኮ​አ​ቸ​ውን እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና፥ እም​ራ​ቸ​ው​ማ​ለ​ሁና።”#ምዕ. 33 ከቍ. 1 እስከ 13 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 40 ከቍ. 1 እስከ 13 ነው ከ14 እስከ መጨ​ረ​ሻው በግ​ሪኩ የለም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ