የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 32

32
ኤር​ም​ያስ የእ​ርሻ መሬት እንደ ገዛ
1በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ በዐ​ሥ​ረ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት፥ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው ቃል ይህ ነው። 2በዚያ ጊዜም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት በነ​በ​ረው በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ታስሮ ነበር። 3የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብሎ አስ​ጠ​ብ​ቆት ነበ​ርና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይቺን ከተማ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እር​ሱም ይይ​ዛ​ታል ብለህ ስለ​ምን ትን​ቢት ትና​ገ​ራ​ለህ? 4የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ በእ​ው​ነት በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰ​ጣል፤ አፍ ለአ​ፍም ይና​ገ​ረ​ዋል፤ ዐይን ለዐ​ይ​ንም ይተ​ያ​ያሉ እንጂ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅ አያ​መ​ል​ጥም፤ 5ሴዴ​ቅ​ያ​ስም ወደ ባቢ​ሎን ይገ​ባል፤ እኔም እስ​ክ​ጐ​በ​ኘው ድረስ በዚያ ይኖ​ራል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ጋር ብቷጉ ምንም አይ​ቀ​ና​ች​ሁም።”#“እስ​ክ​ጐ​በ​ኘ​ውም ድረስ በዚያ ይኖ​ራል ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ጋር ብቷጉ አይ​ቀ​ና​ች​ሁም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
6የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 7“እነሆ የአ​ጎ​ትህ የሰ​ሎም ልጅ አና​ም​ኤል ወደ አንተ መጥቶ፦ ትገ​ዛው ዘንድ የመ​ቤ​ዠቱ መብት የአ​ንተ ነውና በዓ​ና​ቶት ያለ​ውን እር​ሻ​ዬን ግዛ” ይል​ሃል። 8እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የአ​ጎቴ ልጅ አና​ም​ኤል እኔ ወደ አለ​ሁ​በት ወደ ግዞቱ ቤት አደ​ባ​ባይ መጥቶ፥ “በብ​ን​ያም ሀገር በዓ​ና​ቶት ያለ​ውን እር​ሻ​ዬን ግዛ፤ የመ​ግ​ዛ​ትና የመ​ው​ረስ#“የመ​ው​ረስ” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ። መብቱ የአ​ንተ ነውና፥ አንተ ታላ​ቃ​ችን ነህና፤ ለአ​ንተ ግዛው” አለኝ። ይህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ። 9በዐ​ና​ቶ​ትም ያለ​ውን እርሻ ከአ​ጎቴ ልጅ ከአ​ና​ም​ኤል ገዛሁ፤ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘ​ን​ሁ​ለት። 10የው​ሉ​ንም ወረ​ቀት ጻፍሁ፤ አተ​ም​ሁ​ትም፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም ጠርቼ ብሩን በሚ​ዛን መዘ​ን​ሁ​ለት። 11የታ​ተ​መ​ው​ንም የውል ወረ​ቀት ወሰ​ድሁ፤ 12የአ​ጎ​ቴም ልጅ አና​ም​ኤል፥ የው​ሉ​ንም ወረ​ቀት የፈ​ረሙ ምስ​ክ​ሮች፥ በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ የተ​ቀ​መጡ አይ​ሁ​ድም ሁሉ እያዩ የው​ሉን ወረ​ቀት ለማ​ሴው ልጅ ለኔ​ርያ ልጅ ለባ​ሮክ ሰጠ​ሁት። 13በፊ​ታ​ቸ​ውም እን​ዲህ ብዬ ባሮ​ክን አዘ​ዝ​ሁት፦ 14“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ብዙ ቀን ይጠ​በቅ ዘንድ የታ​ተ​መ​ውን ይህን የውል ወረ​ቀት ወስ​ደህ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ አኑ​ረው። 15የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት​ንና እር​ሻን የወ​ይን ቦታ​ንም እንደ ገና ይገ​ዛሉ።”
የኤ​ር​ም​ያስ ጸሎት
16ለኔ​ርያ ልጅ ለባ​ሮ​ክም የው​ሉን ወረ​ቀት ከሰ​ጠ​ሁት በኋላ፥ እን​ዲህ ብዬ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለ​ይሁ፦ 17“ወዮ! አቤቱ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እነሆ አንተ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በታ​ላቅ ኀይ​ል​ህና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክን​ድህ ፈጥ​ረ​ሃል፤ ከአ​ን​ተም የሚ​ሳን ምንም ነገር የለም። 18ታላ​ቅና ኀያል አም​ላክ ሆይ! ለብዙ ሺህ ምሕ​ረ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የአ​ባ​ቶ​ች​ንም በደል ከእ​ነ​ርሱ በኋላ በል​ጆ​ቻ​ቸው ብብት ትመ​ል​ሳ​ለህ። 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ክር ታላቅ በሥ​ራም ብርቱ ነህ፤ ስምህ ታላቅ የሆነ፥ ኀያል፥ ሁሉን ቻይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሁ​ሉም እንደ መን​ገ​ዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዐይ​ኖ​ችህ በሰው ልጆች መን​ገድ ሁሉ ተገ​ል​ጠ​ዋል። 20እስከ ዛሬም ድረስ ምል​ክ​ት​ንና ድን​ቅን ነገር በግ​ብፅ ምድር፥ ደግ​ሞም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በሌ​ሎች ሰዎች መካ​ከል አድ​ር​ገ​ሃል፤ እንደ ዛሬም ለአ​ንተ ስም አድ​ር​ገ​ሃል። 21በም​ል​ክ​ትና በድ​ንቅ ነገር፥ በብ​ርቱ እጅና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ግርማ ሕዝ​ብ​ህን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣህ። 22ትሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ል​ህ​ላ​ቸ​ውን ምድር፥ ወተ​ትና ማርም የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ሰጠ​ሃ​ቸው፤ 23እነ​ር​ሱም ገብ​ተው ወረ​ሱ​አት፤ ነገር ግን ቃል​ህን አል​ሰ​ሙም፤ በሕ​ግ​ህም አል​ሄ​ዱም፤ ያደ​ር​ጉም ዘንድ ካዘ​ዝ​ሃ​ቸው ሁሉ ምንም አላ​ደ​ረ​ጉም፤ ስለ​ዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ህ​ባ​ቸው። 24አሕ​ዛ​ብም መጥ​ተው ይህ​ችን ሀገር ያዟት፤ ይህ​ችም ከተማ ከረ​ኃ​ቡና ከጦሩ የተ​ነሣ በወ​ጓት በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሰዎች እጅ ወደ​ቀች፤ እንደ ተና​ገ​ር​ኸ​ውም ሆነ።#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል። 25አን​ተም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እር​ሻ​ውን በብር ግዛ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም ጥራ አል​ኸኝ፤ እኔም ውሉን ጽፌ አተ​ምሁ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም አቆ​ምሁ፤#“እኔም ውሉን ጽፌ አተ​ምሁ ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም አቆ​ምሁ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ከተ​ማ​ዪቱ ግን ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅ ተሰ​ጥ​ታ​ለች።”
26የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 27“እነሆ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ በውኑ ከእኔ የሚ​ሰ​ወር ነገር አለን? 28ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይችን ከተማ ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅና ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እር​ሱም ይይ​ዛ​ታል። 29ይችን ከተማ የሚ​ወጉ ከለ​ዳ​ው​ያን ይመ​ጣሉ፤ ከተ​ማ​ዋ​ንም በእ​ሳት ያነ​ድ​ዱ​አ​ታል፤ ያስ​ቈ​ጡ​ኝም ዘንድ በሰ​ገ​ነ​ታ​ቸው ላይ ለበ​ዓል ያጠ​ኑ​ባ​ቸ​ውን፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠ​ጥን ቍር​ባን ያፈ​ሰ​ሱ​ባ​ቸ​ውን ቤቶች ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል። 30የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የይ​ሁዳ ልጆች ከታ​ና​ሽ​ነ​ታ​ቸው ጀምሮ በፊቴ ክፉ ነገ​ርን ብቻ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እኔን በእ​ጃ​ቸው ሥራ ከማ​ስ​ቈ​ጣት በቀር ሌላ ሥራ አላ​ደ​ረ​ጉ​ምና፥#“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እኔን በእ​ጃ​ቸው ሥራ ከማ​ስ​ቈ​ጣት በቀር ሌላ ሥራ አላ​ደ​ር​ጉ​ምና” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 31ከፊቴ አስ​ወ​ግ​ዳት ዘንድ ይህች ከተማ ከሠ​ሩ​አት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በቁ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ ውስጥ ናትና፤#ዕብ. “ቍጣ​ዬ​ንና መዓ​ቴን ለማ​ነ​ሣ​ሣት ሆና​ለ​ችና” ይላል። 32ይህም እኔን ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸው፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖሩ ስለ አደ​ረ​ጉት ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና ስለ ይሁዳ ልጆች ክፋት ሁሉ ነው። 33ፊታ​ቸ​ው​ንም ሳይ​ሆን ጀር​ባ​ቸ​ውን ወደ እኔ መለሱ፤ እኔም በማ​ለዳ ተነ​ሥቼ ሳስ​ተ​ም​ራ​ቸው ተግ​ሣ​ጽን ይቀ​በሉ ዘንድ አል​ሰ​ሙም። 34ያረ​ክ​ሱ​ትም ዘንድ ስሜ በተ​ጠ​ራ​በት ቤት ውስጥ ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን አኖሩ። 35ይሁ​ዳን ወደ ኀጢ​አት እን​ዲ​ያ​ገ​ቡት፥ ይህን ርኵ​ሰት ያደ​ርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ት​ንና በልቤ ያላ​ሰ​ብ​ሁ​ትን ነገር፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለሞ​ሎክ በእ​ሳት ያሳ​ልፉ ዘንድ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ለበ​ዓል ሠሩ።”
አስ​ተ​ማ​ማኝ ተስፋ
36አሁን እን​ግ​ዲህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ስለ እር​ስዋ፥ “በሰ​ይ​ፍና በራብ በቸ​ነ​ፈ​ርም ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ትሰ​ጣ​ለች ስለ​ም​ት​ላት ከተማ እን​ዲህ ይላል፦ 37እነሆ በቍ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ፥ በታ​ላ​ቅም መቅ​ሠ​ፍቴ እነ​ር​ሱን ካሳ​ደ​ድ​ሁ​ባት ሀገር ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ህም ስፍራ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ውም እን​ዲ​ኖሩ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ 38እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ። 39ለእ​ነ​ር​ሱም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ቸው መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ቸው ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ፈ​ሩኝ ሌላ #ዕብ. “አንድ” ይላል። መን​ገ​ድና ሌላ#ዕብ. “አንድ” ይላል። ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ። 40ከእ​ነ​ር​ሱም እን​ዳ​ል​መ​ለስ፥ ከእ​ነ​ርሱ ጋር የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን እገ​ባ​ለሁ፤ ከእ​ኔም ዘንድ ፈቀቅ እን​ዳ​ይሉ መፈ​ራ​ቴን በል​ባ​ቸው ውስጥ አኖ​ራ​ለሁ። 41ለእ​ነ​ር​ሱም መል​ካ​ምን በማ​ድ​ረግ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ው​ነ​ትም በፍ​ጹም ልቤና በፍ​ጹም ነፍሴ በዚ​ህች ምድር እተ​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ። 42እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እን​ዳ​መ​ጣሁ፥ እን​ዲሁ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ላ​ቸ​ውን በጎ​ነት ሁሉ አመ​ጣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ። 43እና​ን​ተም፦ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ያለች ባድማ ናት፤ ለከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም እጅ ተሰ​ጥ​ታ​ለች በም​ት​ሉ​አት ምድር እር​ሻን እንደ ገና ይገ​ዛሉ። 44ምር​ኮ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና በብ​ን​ያም ሀገር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ባሉ ስፍ​ራ​ዎች፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች በደ​ጋ​ውም ባሉ ከተ​ሞች፥ በቆ​ላ​ውም ባሉ ከተ​ሞች፥ በደ​ቡ​ብም ባሉ ከተ​ሞች፥ ሰዎች እር​ሻ​ውን በብር ይገ​ዛሉ፤ በው​ሉም ወረ​ቀት ፈር​መው ያት​ማሉ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም ያቆ​ማሉ፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።#ምዕ. 32 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 39 ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ