የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 31:3-6

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 31:3-6 አማ2000

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሩቅ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “በዘ​ለ​ዓ​ለም ፍቅር ወድ​ጄ​ሃ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ በቸ​ር​ነት ሳብ​ሁህ። የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ሆይ እንደ ገና እሠ​ራ​ሻ​ለሁ፤ አን​ቺም ትሠ​ሪ​ያ​ለሽ፤ እንደ ገናም ከበ​ሮ​ሽን አን​ሥ​ተሽ ከዘ​ፋ​ኞች ጋር ትወ​ጫ​ለሽ። እንደ ገናም በሰ​ማ​ርያ ተራ​ሮች ላይ የወ​ይን ተክ​ሎ​ችን ትተ​ክ​ሊ​አ​ለሽ፤ የም​ት​ተ​ክሉ ትከሉ፤ አመ​ስ​ግ​ኑም፤ በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ሮች ላይ የሚ​ከ​ራ​ከሩ፦ ተነሡ፤ ወደ ጽዮን ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ውጣ ብለው የሚ​ጠ​ሩ​ባት ቀን ትመ​ጣ​ለ​ችና።”