ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 23:9-40

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 23:9-40 አማ2000

ስለ ነቢ​ያት ልቤ በው​ስጤ ተሰ​ብ​ሮ​አል፤ አጥ​ን​ቶ​ችም ሁሉ ታው​ከ​ዋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ፤ ከጌ​ት​ነ​ቱም ክብር የተ​ነሣ እኔም በመ​ከራ እንደ ተቀ​ጠ​ቀጠ ሰው፥ የወ​ይን ጠጅ እን​ዳ​ሸ​ነ​ፈ​ውም እንደ ሰካ​ራም ሰው ሆኛ​ለሁ። ዝሙ​ታ​ቸው ምድ​ርን ሞል​ት​ዋ​ልና፥ ከመ​ር​ገም ፊት የተ​ነሣ ምድር አል​ቅ​ሳ​ለች፤ የም​ድረ በዳ ማሰ​ሪ​ያው ሁሉ ደር​ቆ​አል፤ ሥራ​ቸ​ውና ድካ​ማ​ቸው ከንቱ ሆነ። “ነቢ​ዩና ካህ​ኑም ረክ​ሰ​ዋ​ልና፥ በቤ​ቴም ውስጥ ክፋ​ታ​ቸ​ውን አግ​ኝ​ቻ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ስለ​ዚህ መን​ገ​ዳ​ቸው ድጥና ጨለማ ትሆ​ን​ባ​ቸ​ዋ​ለች፤ እነ​ር​ሱም ፍግ​ም​ግም ብለው ይወ​ድ​ቁ​ባ​ታል፤ እኔም በም​ጐ​በ​ኛ​ቸው ዓመት ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። በበ​ዓል ትን​ቢት የተ​ና​ገ​ሩ​በ​ትን የሰ​ማ​ር​ያን ነቢ​ያት ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን አይ​ቻ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አሳ​ት​ዋ​ቸው። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ነቢ​ያት ላይ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጥን ነገር አይ​ቻ​ለሁ፤ ያመ​ነ​ዝ​ራሉ፤ በሐ​ሰ​ትም ይሄ​ዳሉ፤ ማንም ከክ​ፋቱ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን እጅ ያበ​ረ​ታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም እንደ ገሞራ ሆኑ​ብኝ። ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነቢ​ያት ዘንድ ርኵ​ሰት በም​ድር ሁሉ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና ሕማ​ምን አበ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መራራ ውኃ​ንም አጠ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።” ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ትን ቃል አት​ስሙ፤ ከን​ቱ​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ሳይ​ሆን ከገዛ ልባ​ቸው የወ​ጣ​ውን ራእይ ይና​ገ​ራሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለሚ​ያ​ቃ​ልሉ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፥ በፍ​ላ​ጎ​ታ​ቸ​ውና በል​ቡ​ና​ቸው ክፋት ለሚ​ሄ​ዱም ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያ​ገ​ኛ​ች​ሁም” ይላሉ። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር የሚ​ቆም፥ ቃሉን የሚ​ያ​ይና የሚ​ሰማ ማን ነው? ቃሉ​ንስ ያዳ​መጠ፥ የሰ​ማስ ማን​ነው? እነሆ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ንው​ጽ​ው​ጽታ ይመ​ጣል፤ ኃጥ​ኣ​ንን ያነ​ዋ​ው​ጣ​ቸ​ውና ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸው ዘንድ መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋል፤ የዐ​መ​ፀ​ኞ​ችን ራስ ይገ​ለ​ባ​ብ​ጣል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ የል​ቡን ዐሳብ ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ አይ​መ​ለ​ስም፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን ያው​ቁ​ታል። “እኔ ሳል​ል​ካ​ቸው እነ​ዚህ ነቢ​ያት ሮጡ፤ እኔም ሳል​ነ​ግ​ራ​ቸው ትን​ቢ​ትን ተና​ገሩ። በቃሌ ቢቆ​ሙና ምክ​ሬን ቢሰሙ ኖሮ ግን ሕዝ​ቤን ከክፉ ሥራ​ቸው በመ​ለ​ሱ​አ​ቸው ነበር። “እኔ ቅርብ አም​ላክ ነኝ እንጂ ሩቅ አም​ላክ አይ​ደ​ለ​ሁም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ሰው በስ​ውር ቦታ ቢሸ​ሸግ፥ እኔ አላ​የ​ው​ምን? ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንስ የሞ​ላሁ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ሕል​ምን አለ​ምን እያሉ በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን የነ​ቢ​ያ​ትን ነገር ሰም​ቻ​ለሁ። ትን​ቢ​ትን በሐ​ሰት በሚ​ና​ገሩ፥ የል​ባ​ቸ​ው​ንም ሽን​ገላ በሚ​ና​ገሩ በነ​ቢ​ያት ልብ ይህ የሚ​ሆ​ነው እስከ መቼ ነው? አባ​ቶ​ቻ​ቸው ስለ በዓል ስሜን እንደ ረሱ፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው በሚ​ና​ገ​ራት ሕል​ማ​ቸው ሕዝ​ቤን ስሜን ለማ​ስ​ረ​ሳት ያስ​ባሉ። የሚ​ያ​ልም ነቢይ ሕል​ምን ይና​ገር፤ ቃሌም ያለ​በት ቃሌን በእ​ው​ነት ይና​ገር። ገለባ ከስ​ንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድን​ጋ​ዩ​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ቅቅ መዶሻ አይ​ደ​ለ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ስለ​ዚህ እነሆ እያ​ን​ዳ​ንዱ ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ቃሌን በሚ​ሰ​ርቁ ነቢ​ያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። እነሆ ከም​ላ​ሳ​ቸው ትን​ቢ​ትን አው​ጥ​ተው፦ እርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ነው በሚሉ ነቢ​ያት ላይ ነኝ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነሆ ሐሰ​ትን በሚ​ያ​ልሙ፥ በሚ​ና​ገ​ሩም፥ በሐ​ሰ​ታ​ቸ​ውና በድ​ፍ​ረ​ታ​ቸ​ውም ሕዝ​ቤን በሚ​ያ​ስቱ በነ​ቢ​ያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እኔም አል​ላ​ክ​ኋ​ቸ​ውም፤ አላ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ምም፤ ለእ​ነ​ዚህ ሕዝብ በማ​ና​ቸ​ውም አይ​ረ​ቡ​አ​ቸ​ውም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ምን​ድር ነው?” ብሎ ቢጠ​ይ​ቅህ፥ አንተ፥ “ሸክሙ እና​ንተ ናችሁ፤ እጥ​ላ​ች​ሁ​ማ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም የሚ​ለ​ውን ነቢ​ይ​ንና ካህ​ንን፥ ሕዝ​ብ​ንም ያን ሰውና ቤቱን እቀ​ጣ​ለሁ። አን​ዱም አንዱ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው፥ አን​ዱም አንዱ ለወ​ን​ድሙ እን​ዲህ ይበል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ለ​ሰው ምን​ድን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ምን ነገር ተና​ገረ?” ለሰው ሁሉ ቃሉ ሸክም ይሆ​ን​በ​ታ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ብላ​ችሁ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አት​ጥሩ፤ የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ያ​ውን አም​ላክ ቃል ለው​ጣ​ች​ኋ​ልና። ለነ​ቢዩ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን መለ​ሰ​ልህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ የተ​ና​ገ​ረው ምን​ድን ነው?” በሉ ምን ተና​ገረ? ነገር ግን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም” ብትሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም አት​በሉ ብዬ ልኬ​ባ​ች​ኋ​ለ​ሁና፥ እና​ን​ተም ይህን ቃል፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ብላ​ች​ኋ​ልና፥ ስለ​ዚህ፥ እነሆ- ፈጽሜ እረ​ሳ​ች​ኋ​ለሁ እና​ን​ተ​ንም፥ ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም የሰ​ጠ​ኋ​ትን ከተማ ከፊቴ አን​ሥቼ እጥ​ላ​ለሁ። የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንም ስድ​ብና ከቶ ተረ​ስቶ የማ​ይ​ጠ​ፋ​ውን የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ውር​ደት አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።”