የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 37

37
ሕዝ​ቅ​ያስ የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስን ምክር እንደ ጠየቀ
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ንጉሡ ሕዝ​ቅ​ያስ ይህን በሰማ ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ፤ ማቅም ለበሰ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ገባ። 2የቤ​ቱ​ንም አዛዥ ኤል​ያ​ቄ​ምን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳም​ና​ስን፥ የካ​ህ​ና​ቱ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ማቅ ለብ​ሰው ወደ ነቢዩ ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ኢሳ​ይ​ያስ ይሄዱ ዘንድ ላካ​ቸው። 3እነ​ር​ሱም፥ “ሕዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመ​ከ​ራና የተ​ግ​ሣጽ፥ የዘ​ለ​ፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚ​ወ​ለ​ዱ​በት ጊዜ ደር​ሶ​አል፤ ለመ​ው​ለ​ድም ኀይል የለም። 4ምና​ል​ባት በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ጌታው የአ​ሦር ንጉሥ የላ​ከ​ውን የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስን ቃል አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰማ እንደ ሆነ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሰማው ቃል ይገ​ሥ​ጸው እንደ ሆነ፥ ስለ​ዚህ ለቀ​ረው ቅሬታ ጸልይ” አሉት።
5እን​ዲሁ የን​ጉሡ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ብላ​ቴ​ኖች ወደ ኢሳ​ይ​ያስ በመጡ ጊዜ፥ 6ኢሳ​ይ​ያስ፥ “ለጌ​ታ​ችሁ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ሦር ንጉሥ ባሪ​ያ​ዎች ስለ ሰደ​ቡኝ፥ ስለ ሰማ​ኸው ቃል አት​ፍራ። 7እነሆ፥ መን​ፈ​ስን በላዩ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ወሬ​ንም ይሰ​ማል፤ ወደ ምድ​ሩም ይመ​ለ​ሳል፤ በም​ድ​ሩም በሰ​ይፍ እን​ዲ​ወ​ድቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ በሉት” አላ​ቸው።
8የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከለ​ኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበ​ርና ራፋ​ስ​ቂስ ተመ​ልሶ በል​ብና ሲዋጋ አገ​ኘው። 9እር​ሱም፥ “የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንጉሥ ቲር​ሐቅ ሊዋ​ጋህ መጥ​ቶ​አል” የሚል ወሬ ሰማ። በሰ​ማም ጊዜ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እን​ዲህ ሲል፦ 10“ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በአ​ሦር ንጉሥ እጅ አት​ሰ​ጥም ብሎ የም​ት​ታ​መ​ን​በት አም​ላ​ክህ አያ​ታ​ል​ልህ። 11እነሆ፥ የአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት በም​ድር ሁሉ ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን እን​ዴ​ትስ እን​ዳ​ጠ​ፉ​አ​ቸው አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? አን​ተስ ትድ​ና​ለ​ህን? 12አባ​ቶች ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን በቴ​ማን ያሉ​ትን ጎዛ​ን​ንና ካራ​ንን፥ ራፌ​ስ​ንም የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን? 13የሔ​ማ​ትና የአ​ር​ፋድ፥ የሴ​ፈ​ር​ዋይ ከተማ፥ የሄ​ናና የዒዋ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አና​ጉ​ጋና” ይላል። ነገ​ሥ​ታት ወዴት አሉ?”
14ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ደብ​ዳ​ቤ​ውን ከመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞች እጅ ተቀ​ብሎ አነ​በ​በው፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጥቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘረ​ጋው። 15ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፦ 16“አቤቱ፥ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የም​ት​ቀ​መጥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሆይ፥ አንተ ብቻ​ህን የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ አም​ላክ ነህ፤ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ፈጥ​ረ​ሃል። 17አቤቱ፥ ጆሮ​ህን አዘ​ን​ብ​ልና ስማ፤ አቤቱ፥ ዐይ​ን​ህን ክፈ​ትና በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ የላ​ከ​ውን የሰ​ና​ክ​ሬ​ምን ቃል ተመ​ል​ከት። 18አቤቱ፥ በእ​ው​ነት የአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት ዓለ​ሙን ሁሉ ሀገ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋል፤ 19አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለ​ዋል፤ የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ የሰው እጅ ሥራም ነበሩ እንጂ አማ​ል​ክት አል​ነ​በ​ሩ​ምና ስለ​ዚህ አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ቸ​ዋል። 20እን​ግ​ዲህ አም​ላ​ካ​ችን አቤቱ፥ የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ አድ​ነን።”
የሰ​ና​ክ​ሬም ውድ​ቀት
21የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያ​ስም ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ተላከ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰና​ክ​ሬም ወደ እኔ የጸ​ለ​ይ​ኸ​ውን ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ። 22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እርሱ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው፦ ድን​ግ​ሊቱ የጽ​ዮን ልጅ ቀላል አድ​ር​ጋ​ሃ​ለች፤ በን​ቀ​ትም ሥቃ​ብ​ሃ​ለች፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ልጅ ራስ​ዋን ነቅ​ን​ቃ​ብ​ሃ​ለች። 23የተ​ገ​ዳ​ደ​ር​ኸው፥ የሰ​ደ​ብ​ኸ​ውስ ማንን ነው? ቃል​ህ​ንስ ከፍ ከፍ ያደ​ረ​ግ​ህ​በት፥ ዐይ​ን​ህ​ንስ ወደ ላይ ያነ​ሣ​ህ​በት ማን ነው? በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ላይ አይ​ደ​ለ​ምን? 24አን​ተም በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ በኩል እን​ዲህ ብለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተገ​ዳ​ደ​ር​ኸው፦ በሰ​ረ​ገ​ላዬ ብዛት ወደ ተራ​ሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባ​ኖስ ራስ ወጥ​ቻ​ለሁ፤ ረዣ​ዥ​ሞ​ቹ​ንም ዝግ​ባ​ዎች፥ የተ​መ​ረ​ጡ​ት​ንም ጥዶች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ ወደ ከፍ​ታ​ውም ዳርቻ ወደ ዱሩ እገ​ባ​ለሁ፤ 25ገድ​ቤም ውኃ​ው​ንና የው​ኃ​ውን ኩሬ አደ​ር​ቃ​ለሁ።
26“እኔ ጥንት የሠ​ራ​ሁ​ትን አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? እኔ በቀ​ድሞ ዘመን እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት፥ አሁ​ንም አሕ​ዛ​ብን በም​ሽ​ጎ​ቻ​ቸው፥ በጽኑ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ያጠፉ ዘንድ አዘ​ዝሁ። 27እጃ​ቸ​ው​ንም አዝ​ላ​ለሁ፤ ይደ​ር​ቃ​ሉም፤ በሰ​ገ​ነት ላይ እን​ዳለ ደረቅ ሣርም ሳያ​ሸት ዋግ እንደ መታው እህ​ልም ይሆ​ናሉ። 28አሁን ግን እኔ መቀ​መ​ጫ​ህ​ንና መው​ጫ​ህን፥ መግ​ቢ​ያ​ህ​ንም ዐው​ቄ​አ​ለሁ። 29የተ​ቈ​ጣ​ኸው ቍጣና ትዕ​ቢ​ትህ ወደ ጆሮዬ ደር​ሶ​አ​ልና ሰለ​ዚህ ስና​ጋ​ዬን በአ​ፍ​ን​ጫህ፥ ልጓ​ሜ​ንም በከ​ን​ፈ​ርህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በመ​ጣ​ህ​በ​ትም መን​ገድ እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ።
30“ይህም ምል​ክት ይሆ​ን​ሃል፤ በዚህ ዓመት የዘ​ራ​ኸ​ውን፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከገ​ቦው የበ​ቀ​ለ​ውን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ትዘ​ራ​ላ​ቸሁ፤ ታጭ​ዱ​ማ​ላ​ችሁ፤ ወይ​ን​ንም ትተ​ክ​ላ​ላ​ችሁ፤ ፍሬ​ው​ንም ትበ​ላ​ላ​ችሁ። 31ያመ​ለ​ጠው የይ​ሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰ​ድ​ዳል፤ ወደ ላይም ያፈ​ራል። 32ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅሬታ ከጽ​ዮ​ንም ተራራ ያመ​ለ​ጡት ይድ​ና​ሉና፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​አት ይህን ያደ​ር​ጋል። 33ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ ወደ​ዚች ከተማ አይ​መ​ጣም፤ ፍላ​ጻ​ንም አይ​ወ​ረ​ው​ር​ባ​ትም፤ በጋ​ሻም አይ​መ​ጣ​ባ​ትም፥ አያ​ጥ​ራ​ት​ምም። 34በመ​ጣ​በ​ትም መን​ገድ በዚያ ይመ​ለ​ሳል፤ ወደ​ዚ​ህም ከተማ አይ​መ​ጣም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ 35ስለ እኔም፥ ስለ ባሪ​ያ​ዬም ስለ ዳዊት ይህ​ችን ከተማ እረ​ዳ​ታ​ለሁ አድ​ና​ታ​ለ​ሁም።”
36የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወጣ፤ ከአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም ሰፈር መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ፤ ማለ​ዳም በተ​ነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድ​ኖች ሆነው አገ​ኙ​አ​ቸው። 37የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ተመ​ል​ሶም በነ​ነዌ ተቀ​መጠ። 38በአ​ም​ላ​ኩም በና​ሳ​ራክ ቤት ሲሰ​ግድ ልጆቹ አድ​ራ​ሜ​ሌ​ክና ሳራ​ሳር በሰ​ይፍ ገደ​ሉት፤ ወደ አራ​ራ​ትም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አር​ማ​ንያ” ይላል። ሀገር ኰበ​ለሉ። ልጁም አስ​ራ​ዶን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ