የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 38

38
የሕ​ዝ​ቅ​ያስ መታ​መ​ምና መዳን
1በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ ለሞት እስ​ኪ​ደ​ርስ ታመመ። ነቢ​ዩም የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ በሕ​ይ​ወት አት​ኖ​ር​ምና ቤት​ህን አስ​ተ​ካ​ክል” አለው። 2ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ፊቱን ወደ ግድ​ግ​ዳው መልሶ እን​ዲህ ሲል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ፦ 3“አቤቱ፥ በፊ​ትህ በእ​ው​ነ​ትና በቅን ልብ እንደ ሄድሁ፥ በፊ​ት​ህም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ አስብ።” ሕዝ​ቅ​ያ​ስም እጅግ ታላቅ ልቅ​ሶን አለ​ቀሰ። 4የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኢሳ​ይ​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፤ 5“ሂድ፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ በለው፦ የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እን​ባ​ህ​ንም አይ​ቻ​ለሁ፤ እነሆ፥ በዕ​ድ​ሜህ ላይ ዐሥራ አም​ስት ዓመት እጨ​ም​ራ​ለሁ፤ 6አን​ተ​ንና ይህ​ች​ንም ከተማ ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ አድ​ና​ለሁ፤ ለዚ​ችም ከተማ እቆ​ም​ላ​ታ​ለሁ። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ፈ​ጽ​መው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምል​ክቱ ይህ ይሆ​ን​ል​ሃል። 8እነሆ፥ በአ​ባ​ትህ የጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ ከፀ​ሐይ ጋራ የወ​ረ​ደ​ውን በደ​ረ​ጃ​ዎች ያለ​ውን ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እን​ዲ​መ​ለስ አደ​ር​ጋ​ለሁ።” ፀሐ​ይም በጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ የወ​ረ​ደ​በት ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመ​ለሰ።
የይ​ሁዳ ንጉሥ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ጸሎት
9የይ​ሁዳ ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያስ ታምሞ ከደ​ዌው በተ​ፈ​ወሰ ጊዜ የጸ​ለ​የው ጸሎት ይህ ነው፦
10እኔ እን​ዲህ አልሁ፥ “በሕ​ይ​ወት ዘመኔ መካ​ከል#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፍጻሜ” ይላል። ወደ ሲኦል በሮች እገ​ባ​ለሁ፤
የቀ​ረ​ው​ንም ዘመ​ኔን ተውሁ።
11ደግ​ሞም፦ በሕ​ያ​ዋን ምድር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን፤
የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም መዳን በም​ድር ላይ አላ​ይም፤
ከዘ​መ​ዶ​ችም ሰውን አላ​ይም።
12የቀ​ረ​ው​ንም ኑሬ​ዬን አጣሁ።
ከእ​ኔም ወጣች፥ ተለ​የ​ችም።
ድን​ኳ​ኑን ተክሎ እን​ደ​ሚ​ያ​ድ​ርና እን​ደ​ሚ​ሄድ፥
ሊቈ​ረጥ እንደ ተቃ​ረበ ሸማም እን​ዲሁ ነፍሴ በላዬ ሆነች።
13በዚያ ወራት እስ​ኪ​ነጋ ድረስ እንደ አን​በሳ ታወ​ክሁ፤
እን​ደ​ዚ​ሁም አጥ​ን​ቶች ተቀ​ጠ​ቀ​ጡ​ብኝ፤
ከማ​ለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ተጨ​ነ​ቅሁ።
14እንደ ሸመላ እን​ዲሁ ጮህሁ፤
እንደ ርግ​ብም አጕ​ረ​መ​ረ​ምሁ፤
15ዐይ​ኖች ደከሙ፤ ወደ ሰማ​ይም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማየት አል​ቻ​ል​ሁም።
ጌታ ሆይ፦ ይቅር በለኝ፤ የሰ​ው​ነ​ቴ​ንም መከራ አር​ቅ​ልኝ።
16ጌታ ሆይ፥ ስለ እር​ስዋ እን​ዲህ አል​ሁህ፤ ነፍ​ሴን አዳ​ን​ሃት፤
ደስ አለኝ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ኖርሁ።
17ሰው​ነ​ቴ​ንም እን​ዳ​ት​ጠፋ ይቅር አል​ሃት፤
ኀጢ​አ​ቴ​ንም ሁሉ ወደ ኋላዬ ጣልህ።
18በመ​ቃ​ብር የሚ​ኖሩ አያ​መ​ሰ​ግ​ኑ​ህ​ምና፤
ሙታ​ንም የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑህ አይ​ደ​ሉ​ምና፤
በሲ​ኦ​ልም የሚ​ኖሩ ይቅ​ር​ታ​ህን ተስፋ አያ​ደ​ር​ጉ​ምና።
19እኔ ዛሬ እን​ደ​ማ​ደ​ርግ ሕያ​ዋን ብቻ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤
ከዛሬ ጀምሮ ጽድ​ቅ​ህን የሚ​ና​ገሩ ልጆ​ችን እወ​ል​ዳ​ለሁ።#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ጌታ ሆይ ከዛሬ ጀምሮ ይህች ተግ​ሣፅ ትሥ​ራኝ፤ በሕ​ይ​ወቴ ጽድ​ቅ​ህን እና​ገ​ራ​ለሁ ዘወ​ትር አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ ለአ​ን​ተም እዘ​ም​ራ​ለሁ” ይላል።
20ጌታዬ ሆይ አንተ መድ​ኀ​ኒቴ ነህ፤
ስለ​ዚህ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አው​ታር ባለው ዕቃ አን​ተን ማመ​ስ​ገ​ንን አላ​ቋ​ር​ጥም።”
21ኢሳ​ይ​ያ​ስም ሕዝ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ አለው፥ “የበ​ለስ ጥፍ​ጥፍ አም​ጥ​ተህ በእ​ባጩ ላይ ለብ​ጠው፤ አን​ተም ትፈ​ወ​ሳ​ለህ።” 22ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እወጣ ዘንድ ምል​ክቱ ምን​ድን ነው?” ብሎ ነበር።#ይህ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ጸሎት በግ​እ​ዙና በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጡ መካ​ከል ልዩ​ነት አለው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ