የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 35

35
የዳኑ ሰዎች ደስታ
1የተ​ጠ​ማው ምድረ በዳ ደስ ይለ​ዋል፤ በረ​ሃ​ውም ሐሤት ያደ​ር​ጋል፤ እንደ ጽጌ​ረ​ዳም ያብ​ባል። 2የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ምድረ በዳ ያብ​ባል፤ ሐሤ​ት​ንም ያደ​ር​ጋል፤ የሊ​ባ​ኖስ ክብ​ርና የቀ​ር​ሜ​ሎስ ክብር ይሰ​ጠ​ዋል፤ ሕዝ​ቤም የጌ​ታን ክብር፥ የአ​ም​ላ​ክ​ንም ግርማ ያያሉ።
3ደካ​ሞች እጆ​ችና አን​ካ​ሶች ጕል​በ​ቶች፥ ጽኑ። 4እና​ንተ አእ​ምሮ የሌ​ላ​ችሁ፥ ልቡ​ና​ች​ሁን አረ​ጋጉ፤ ጽኑ፤ አት​ፍሩ፤ እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችን ፍር​ድን ይመ​ል​ሳል፤ ይበ​ቀ​ላ​ልም፤ እር​ሱም መጥቶ ያድ​ነ​ናል።
5በዚ​ያን ጊዜም የዕ​ው​ሮች ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ይገ​ለ​ጣሉ፤ የደ​ን​ቆ​ሮ​ዎ​ችም ጆሮ​ዎች ይሰ​ማሉ። 6በዚ​ያን ጊዜ አን​ካ​ሳ​ዎች እንደ ሚዳቋ ይዘ​ል​ላሉ፤ የዲ​ዳ​ዎ​ችም ምላስ ርቱዕ ይሆ​ናል፤ በም​ድረ በዳ ውኃ፥ በተ​ጠማ መሬ​ትም ፈሳሽ ይፈ​ል​ቃ​ልና። 7ደረ​ቂቱ ምድር ኩሬ፥ የተ​ጠ​ማች ምድ​ርም የውኃ ምንጭ ትሆ​ና​ለች፤ የዎ​ፎች መኖ​ሪ​ያም ሸን​በ​ቆና ደን​ገል ይሆ​ን​በ​ታል። 8በዚ​ያም ንጹሕ መን​ገድ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም የተ​ቀ​ደሰ መን​ገድ ይባ​ላል፤ በዚ​ያም ንጹ​ሓን ያል​ሆኑ አያ​ል​ፉ​በ​ትም፤ ርኩስ መን​ገ​ድም በዚያ አይ​ኖ​ርም፤ የተ​በ​ተ​ኑ​ትም በእ​ርሱ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ሳ​ሳ​ቱ​ምም። 9አን​በሳ አይ​ኖ​ር​በ​ትም፤ ክፉ አው​ሬም አይ​ወ​ጣ​በ​ትም፤ በዚ​ያም አይ​ገ​ኙም፤ የዳ​ኑት ግን በዚያ ይሄ​ዳሉ። 10በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ይመ​ለ​ሳሉ፤ በደ​ስ​ታም ተመ​ል​ሰው ወደ ጽዮን ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታም በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ሐሤ​ት​ንና ደስ​ታ​ንም ያገ​ኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘ​ንና ትካ​ዜም ይጠ​ፋሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ