የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 12:14-17

ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 12:14-17 አማ2000

ከሁሉ ጋር ወደ ሰላም ሩጡ፤ ቅድ​ስ​ና​ች​ሁ​ንም አት​ተዉ፤ ያለ እርሱ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​የው የለም። አስ​ተ​ውሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጸጋ የሚ​ያ​ቃ​ልል አይ​ኑር፤ ሕማ​ምን የም​ታ​መጣ፥ ብዙ​ዎ​ች​ንም የም​ታ​ስ​ታ​ቸ​ውና የም​ታ​ረ​ክ​ሳ​ቸው መራራ ሥር የም​ት​ገ​ኝ​በ​ትም አይ​ኑር። ለጥ​ቂት መብል ብኵ​ር​ና​ውን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ሴሰ​ኛና ርኩስ የሚ​ሆን አይ​ኑር። ከዚያ በኋላ እንኳ በረ​ከ​ትን ሊወ​ርስ በወ​ደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና፤ በእ​ን​ባም ተግቶ ምንም ቢፈ​ል​ጋት ለን​ስሓ ስፍራ አላ​ገ​ኘ​ምና።