የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 12:14-17

ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 12:14-17 አማ05

ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ማየት ስለማይችል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ፤ በቅድስናም ለመኖር ትጉ፤ ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት ተጠንቀቁ፤ እንዲሁም ምንም መራራ ፍሬ የሚያፈራ ሥር በመካከላችሁ እንዳይበቅልና እንዳያስቸግራችሁ ብዙዎችንም እንዳያረክስ ተጠንቀቁ። ሴሰኛ የሆነ ወይም ለአንድ ጊዜ ምግብ ብሎ ብኲርናውን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ነውረኛ የሆነ ሰው እንዳይገኝ ተጠንቀቁ። በኋላም ዔሳው በረከትን እንደገና ለመቀበል በፈለገ ጊዜ ይህን በረከት እንደ ተከለከለ ታውቃላችሁ፤ እያለቀሰ እንኳ ያንን በረከት ተግቶ ቢፈልግ ሊያገኘው አልቻለም። ለንስሓ ምንም ዕድል አላገኘም።