ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 11:20-31

ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 11:20-31 አማ2000

ያገ​ኙት ዘንድ ስለ አላ​ቸው ነገር ይስ​ሐቅ ያዕ​ቆ​ብ​ንና ኤሳ​ውን በእ​ም​ነት ባረ​ካ​ቸው። ያዕ​ቆ​ብም በሚ​ሞ​ት​በት ጊዜ የዮ​ሴ​ፍን ልጆች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውን በእ​ም​ነት ባረ​ካ​ቸው፤ በበ​ትሩ ጫፍም ሰገደ። ዮሴ​ፍም በሚ​ሞ​ት​በት ጊዜ፥ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ መው​ጣት በእ​ም​ነት ዐሰበ፤ ዐጽ​ሙ​ንም ትተው እን​ዳ​ይ​ወጡ አዘዘ። ሙሴ በተ​ወ​ለደ ጊዜ በእ​ም​ነት ሦስት ወር በአ​ባቱ ቤት ሸሸ​ጉት፤ ሕፃኑ መል​ካም እንደ ሆነ አይ​ተ​ው​ታ​ልና፤ የን​ጉ​ሥ​ንም ትእ​ዛዝ አል​ፈ​ሩም። ሙሴም በአ​ደገ ጊዜ የፈ​ር​ዖን የልጅ ልጅ እን​ዳ​ይ​ባል በእ​ም​ነት እንቢ አለ፤ ለጊ​ዜው በኀ​ጢ​አት ከሚ​ገኝ ደስታ ይልቅ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀ​በ​ልን መረጠ። የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ተግ​ዳ​ሮት ከግ​ብፅ ሀብት ሁሉ ይልቅ እጅግ የሚ​በ​ልጥ ባለ​ጠ​ግ​ነት እን​ደ​ሚ​ሆን ዐው​ቆ​አ​ልና፥ ዋጋ​ው​ንም ተመ​ል​ክ​ቶ​አ​ልና። የን​ጉ​ሡ​ንም ቍጣ ሳይ​ፈራ፥ የግ​ብ​ፅን ሀገር በእ​ም​ነት ተወ፤ ከሚ​ያ​የው ይልቅ የማ​ይ​ታ​የ​ውን ሊፈራ ወዶ​አ​ልና። ቸነ​ፈር በኵ​ራ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ባ​ቸው በእ​ም​ነት ፋሲ​ካን አደ​ረገ፤ ደሙ​ንም ረጨ። በደ​ረቅ ምድር እንደ መሄድ የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በእ​ም​ነት ተሻ​ገ​ሩ​አት፤ የግ​ብፅ ሰዎች ግን ሲሞ​ክሩ ሰጠሙ። ሰባት ቀን ከዞ​ሩ​አት በኋላ የኢ​ያ​ሪኮ ቅጽር በእ​ም​ነት ወደቀ። ዘማ ረአ​ብም በእ​ም​ነት ከከ​ሓ​ዲ​ዎች ጋር አል​ጠ​ፋ​ችም፤ ጕበ​ኞ​ችን በሰ​ላም ተቀ​ብላ ሰው​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ችና።