እንዲህም ሆነ፤ ልብሱን ትቶ ወደ ውጭ እንደ ሸሸ በአየች ጊዜ፥ የቤቷን ሰዎች ወደ እርስዋ ጠርታ እንዲህ ብላ ነገረቻቸው፥ “እዩ፤ ይህ ዕብራዊ ባርያ በእኛ እንዲሣለቅ አመጣብን፤ እርሱ ወደ እኔ ገብቶ ከእኔ ጋር ተኚ አለኝ፤ እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽሁ፤ ድምፄንም ከፍ አድርጌ እንደ ጮኽሁ ቢሰማ፥ ልብሱን በእኔ ዘንድ ጥሎ ሸሸ፤ ወደ ውጭም ወጣ።” ጌታው ወደ ቤቱ እስኪገባ ድረስም ልብሱን ከእርስዋ ዘንድ አኖረች። ይህንም ነገር እንዲህ ብላ ነገረችው፥ “ያመጣኸው ዕብራዊው ባሪያ ሊሣለቅብኝ ወደ እኔ ገባ፤ ከአንቺም ጋር ልተኛ አለኝ። እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ልብሱን በእጄ ተወና ወደ ውጭ ሸሸ።” ጌታውም፥ “ባሪያህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ የነገረችውን የሚስቱን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ። ዮሴፍንም ወሰደው፤ የንጉሡ እስረኞች ወደሚታሰሩበት ስፍራ ወደ ግዞት ቤትም አገባው፤ ከዚያም በግዞት ነበረ። እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ፤ ምሕረትንም አበዛለት፤ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው። የግዞት ቤቱም አለቃ በግዞት ያሉትን እስረኞች ሁሉ በዮሴፍ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዚያም የሚደረገው ነገር ሁሉ እርሱ የሚያደርገው ነበረ። የግዞት ቤቱ ጠባቂዎች አለቃም በግዞት ቤት የሚደረገውን ሁሉ ምንም አያውቅም ነበር፤ ሁሉን ለዮሴፍ ትቶለት ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረና፤ የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ ያቀናለት ነበር።
ኦሪት ዘፍጥረት 39 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 39:13-23
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች