የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 39:1-10

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 39:1-10 አማ2000

ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈ​ር​ዖን ጃን​ደ​ረባ የመ​ጋ​ቢ​ዎ​ቹም አለቃ የሚ​ሆን የግ​ብፅ ሰው ጲጥ​ፋራ ወደ ግብፅ ከአ​ወ​ረ​ዱት ከይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን እጅ ገዛው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዮ​ሴፍ ጋር ነበር፤ ሥራ​ውም የተ​ከ​ና​ወ​ነ​ለት ሰው ሆነ፤ በግ​ብ​ፃ​ዊው ጌታ​ውም ቤት ተሾመ። ጌታ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዮ​ሴፍ ጋር እን​ዳለ፥ እርሱ የሚ​ሠ​ራ​ው​ንም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ እን​ዲ​ያ​ከ​ና​ው​ን​ለት አየ። ዮሴ​ፍም በጌ​ታው ፊት ሞገ​ስን አገኘ፤ እር​ሱ​ንም ደስ ያሰ​ኘው ነበር፤ በቤ​ቱም ላይ ሾመው፤ ያለ​ው​ንም ሁሉ በእጁ ሰጠው። እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በቤቱ ባለ​ውም ሁሉ ላይ ከሾ​መው በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የግ​ብ​ፃ​ዊ​ውን ቤት በዮ​ሴፍ ምክ​ን​ያት ባረ​ከው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በረ​ከት በቤ​ቱም፥ በእ​ር​ሻ​ውም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ። ያለ​ው​ንም ሁሉ ለዮ​ሴፍ በእጁ አስ​ረ​ከ​በው፤ ከሚ​በ​ላ​ውም እን​ጀራ በቀር ምንም የሚ​ያ​ው​ቀው አል​ነ​በ​ረም። ዮሴ​ፍም መልኩ ያማረ፥ ፊቱም እጅግ የተ​ዋበ ነበር። ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የጌ​ታው ሚስት በዮ​ሴፍ ላይ ዐይ​ን​ዋን ጣለ​ች​በት፤ “ከእ​ኔም ጋር ተኛ” አለ​ችው። እር​ሱም እንቢ አለ፤ ለጌ​ታ​ውም ሚስት እን​ዲህ አላት፥ “እነሆ፥ ጌታዬ በቤቱ ያለ​ውን ሁሉ ለእኔ በእጄ አስ​ረ​ክ​ቦ​ኛል፤ በቤቱ ያለ​ው​ንም ምንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም፤ በዚህ ቤት ከእኔ የሚ​በ​ልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለ​ሆ​ንሽ ከአ​ንቺ በቀር ያል​ሰ​ጠኝ ነገር የለም፤ እን​ዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደ​ር​ጋ​ለሁ? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዴት ኀጢ​አ​ትን እሠ​ራ​ለሁ?” ይህ​ንም ነገር በየ​ዕ​ለቱ ለዮ​ሴፍ ትነ​ግ​ረው ነበር፤ እር​ሱም ከእ​ር​ስዋ ጋር ይተኛ ዘንድ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ይሆን ዘንድ አል​ሰ​ማ​ትም።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}