ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 17:1-14

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 17:1-14 አማ2000

ከዚ​ህም በኋላ አብ​ራም የዘ​ጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው “በፊ​ትህ የሄ​ድሁ ፈጣ​ሪህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መል​ካም አድ​ርግ፤ ንጹ​ሕም ሁን፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል አጸ​ና​ለሁ፤ እጅ​ግም አበ​ዛ​ሃ​ለሁ።” አብ​ራ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን እን​ዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ቃል ኪዳ​ኔን በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል አጸ​ና​ለሁ፤ ለብዙ አሕ​ዛ​ብም አባት ትሆ​ና​ለህ። እን​ግ​ዲህ ስምህ አብ​ራም አይ​ባ​ልም ‘አብ​ር​ሃም’ ይባ​ላል እንጂ፤ ለብዙ አሕ​ዛብ አባት አድ​ር​ጌ​ሃ​ለ​ሁና። እጅ​ግም በጣም አበ​ዛ​ሃ​ለሁ፤ ሕዝ​ብም፥ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከአ​ንተ እን​ዲ​ወጡ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ። ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል በት​ው​ል​ዳ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን አቆ​ማ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተና ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ አም​ላክ እሆን ዘንድ። በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ር​ባ​ትን ይህ​ችን ምድር፥ የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ሁሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​አት ዘንድ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “አንተ ደግሞ ቃል ኪዳ​ኔን ትጠ​ብ​ቃ​ለህ፤ አንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ዘርህ በት​ው​ል​ዳ​ቸው። በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል የም​ት​ጠ​ብ​ቋት ቃል ኪዳኔ ይህች ናት፤ ከእ​ና​ንተ ወንድ ሁሉ ይገ​ረዝ። የሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁን ቍል​ፈት ትገ​ረ​ዛ​ላ​ችሁ፤ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ላለ​ውም ቃል ኪዳን ምል​ክት ይሆ​ናል። ሕፃ​ኑ​ንም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ትገ​ር​ዙ​ታ​ላ​ችሁ፤ በቤት የተ​ወ​ለደ ወይም ከዘ​ራ​ችሁ ያይ​ደለ፥ በብ​ርም ከእ​ን​ግዳ ሰው የተ​ገዛ ወንድ ሁሉ በት​ው​ል​ዳ​ችሁ ይገ​ረዝ። በቤ​ት​ህም የተ​ወ​ለደ፥ በብ​ርም የተ​ገዛ ፈጽሞ ይገ​ረዝ። ቃል ኪዳ​ኔም በሥ​ጋ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ይሆ​ናል። በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የሥ​ጋ​ውን ቍል​ፈት ያል​ተ​ገ​ረዘ፥ ያች ነፍስ ከወ​ገ​ንዋ ተለ​ይታ ትጥፋ፤ ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሳ​ለ​ችና።”

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}