የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዕዝራ 7:6-10

መጽ​ሐፈ ዕዝራ 7:6-10 አማ2000

ይህም ዕዝራ ከባ​ቢ​ሎን ወጣ፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ የሰ​ጠ​ውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአ​ም​ላ​ኩም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና ንጉሡ ያሻ​ውን ሁሉ ሰጠው። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከካ​ህ​ና​ቱም፥ ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከመ​ዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከበ​ረ​ኞ​ቹም፥ ከና​ታ​ኒ​ምም በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ዐያ​ሌ​ዎች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጡ። በን​ጉ​ሡም በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ። በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በአ​ን​ደ​ኛው ቀን ከባ​ቢ​ሎን ሊወጡ ጀመሩ፤ መል​ካ​ሚ​ቱም የአ​ም​ላኩ እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ። ዕዝ​ራም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ይፈ​ል​ግና ያደ​ርግ ዘንድ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሥር​ዐ​ት​ንና ፍር​ድን ያስ​ተ​ምር ዘንድ ልቡን አዘ​ጋ​ጅቶ ነበር።

Free Reading Plans and Devotionals related to መጽ​ሐፈ ዕዝራ 7:6-10