የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 13

13
በሐ​ሰ​ተ​ኞች ነቢ​ያት ላይ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት በሚ​ና​ገሩ በእ​ስ​ራ​ኤል ነቢ​ያት ላይ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ከገዛ ልባ​ቸ​ውም ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ በላ​ቸው፤ 3ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ፈጽሞ ሳያዩ ከገዛ ልባ​ቸው አን​ቅ​ተው ትን​ቢት ለሚ​ና​ገሩ ወዮ​ላ​ቸው! 4እስ​ራ​ኤል ሆይ! ነቢ​ያ​ትህ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​ኖሩ ቀበ​ሮ​ዎች ናቸው። 5ወደ ተሰ​በ​ረው ቅጥር አል​ወ​ጣ​ች​ሁም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀን በሰ​ልፍ ትቆሙ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ቅጥ​ርን አል​ሠ​ራ​ች​ሁም። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሳይ​ል​ካ​ቸው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይላል የሚሉ ሰዎች ሐሰ​ትን ያያሉ፤ ከን​ቱን ያም​ዋ​ር​ታሉ፤ ቃሉ​ንም ማጽ​ናት ይጀ​ም​ራሉ። 7እኔም ሳል​ና​ገር፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ​አል ስትሉ፥ ከንቱ ምዋ​ር​ትን የተ​ና​ገ​ራ​ችሁ፥ የሐ​ሰት ራእ​ይ​ንም ያያ​ችሁ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን?”
8ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከንቱ ነገ​ርን ስለ ተና​ገ​ራ​ችሁ፥ ሐሰ​ተኛ ራእ​ይ​ንም ስለ አያ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ እነሆ እኔ በእ​ና​ንተ ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 9እጄም ሐሰ​ተኛ ራእ​ይን በሚ​ያዩ፥ ሕዝ​ቤ​ንም ለማ​ታ​ለል በከ​ንቱ በሚ​ያ​ም​ዋ​ርቱ ነቢ​ያት ላይ ትሆ​ና​ለች። እነ​ር​ሱም በሕ​ዝቤ ማኅ​በር ውስጥ አይ​ኖ​ሩም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት መጽ​ሐፍ አይ​ጻ​ፉም፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ምድር አይ​ገ​ቡም፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። 10ሰላም ሳይ​ኖር፦ ሰላም እያሉ ሕዝ​ቤን አታ​ል​ለ​ዋ​ልና፤ አን​ዱም ሰው ቅጥር ሲሠራ እነ​ርሱ ያለ​ገ​ለባ ይመ​ር​ጉ​ታል፤ ይወ​ድ​ቃ​ልም፤ 11ያለ ገለ​ባም ለሚ​መ​ር​ጉት ሰዎች፦ ይወ​ድ​ቃል በላ​ቸው። የሚ​ያ​ሰ​ጥም ዝናብ ይዘ​ን​ባል፤ ታላ​ቅም የበ​ረዶ ድን​ጋይ በራ​ሳ​ቸው ላይ አወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ኀይ​ለኛ ዐውሎ ነፋ​ስም ይሰ​ነ​ጣ​ጥ​ቀ​ዋል። 12እነሆ ግንቡ በወ​ደቀ ጊዜ፦ የመ​ረ​ጋ​ች​ሁት ምርግ ወዴት አለ? አይ​ሉ​አ​ች​ሁ​ምን? 13ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በመ​ዓቴ በዐ​ውሎ ነፋስ እሰ​ነ​ጣ​ጥ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ያጠ​ፋ​ውም ዘንድ በቍ​ጣዬ የሚ​ያ​ሰ​ጥም ዝናብ፥ በመ​ዓ​ቴም ታላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ር​ዳ​ለሁ። 14ያለ ገለባ የመ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ት​ንም ቅጥር አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ይወ​ድ​ቃል፤ ወደ ምድ​ርም እጥ​ለ​ዋ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ቱም ይታ​ያል፤ እር​ሱም ይና​ዳል፤ በመ​ካ​ከ​ሉም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 15መዓ​ቴ​ንም በግ​ንቡ ላይና ያለ​ገ​ለባ በመ​ረ​ጉት ላይ እፈ​ጽ​ማ​ለሁ፤ ግን​ቡም ይወ​ድ​ቃል፤ እኔም፦ ግን​ቡና መራ​ጊ​ዎቹ የሉም እላ​ች​ኋ​ለሁ። 16እነ​ር​ሱም ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ትን​ቢት የሚ​ና​ገሩ፥ የሰ​ላ​ም​ንም ራእይ የሚ​ያ​ዩ​ላት የእ​ስ​ራ​ኤል ነቢ​ያት ናቸው፤ ሰላ​ምም የለም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
በሐ​ሰ​ተ​ኞች ሴቶች ነቢ​ያት ላይ የተ​ነ​ገረ ተግ​ሣጽ
17“አን​ተም፥ የሰው ልጅ ሆይ! ከል​ባ​ቸው አን​ቅ​ተው ትን​ቢት በሚ​ና​ገሩ በሕ​ዝ​ብህ ሴቶች ልጆች ላይ ፊት​ህን አድ​ርግ፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገ​ር​ባ​ቸው፤ 18እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ነፍ​ስን ለማ​ጥ​መድ ለእጅ ድጋፍ ሁሉ መከዳ ለሚ​ሰፉ፥ ለሰ​ውም ሁሉ ራስ እንደ እየ​ቁ​መቱ ሽፋን ለሚ​ሠሩ ሴቶች ወዮ​ላ​ቸው! የሕ​ዝ​ቤን ነፍስ ታጠ​ም​ዳ​ላ​ችሁ፤ በውኑ እና​ንተ ነፍ​ሳ​ች​ሁን ታድ​ና​ላ​ችሁ? 19ከንቱ ነገ​ርን ለሚ​ሰ​ሙት ሕዝቤ እየ​ዋ​ሻ​ችሁ ሞት የማ​ይ​ገ​ባ​ቸ​ውን ነፍ​ሳት ትገ​ድሉ ዘንድ፥ በሕ​ይ​ወ​ትም መኖር የማ​ይ​ገ​ባ​ቸ​ውን በሕ​ይ​ወት ታኖሩ ዘንድ ስለ ጭብጥ ገብ​ስና ስለ ቍራሽ እን​ጀራ ሕዝ​ቤን አር​ክ​ሳ​ች​ኋል።
20“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ነፍ​ሳ​ትን እንደ ወፍ በም​ታ​ጠ​ም​ዱ​ባት በመ​ከ​ዳ​ችሁ ላይ ነኝ፤ ከክ​ን​ዳ​ች​ሁም ወስጄ እቀ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ፤ እንደ ወፍም የም​ታ​ጠ​ም​ዱ​አ​ቸ​ውን ነፍ​ሳት እለ​ቅ​ቃ​ለሁ። 21ሽፋ​ኖ​ቻ​ች​ሁን ደግሞ እቀ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤ​ንም ከእ​ጃ​ችሁ አድ​ና​ለሁ፤ ከዚ​ያም ወዲያ በእ​ጃ​ችሁ ለመ​ታ​ደን አይ​ሆ​ኑም፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 22እኔም ያል​መ​ለ​ስ​ሁ​ትን የጻ​ድ​ቁን ልብ ወደ ዐመፃ መል​ሳ​ች​ኋ​ልና፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መን​ገድ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውን እጅ አበ​ር​ት​ታ​ች​ኋ​ልና፤ 23ስለ​ዚህ፥ ሐሰ​ትን አታ​ዩም፤ እን​ግ​ዲ​ህም ከንቱ ምዋ​ር​ትን አታ​ም​ዋ​ር​ቱም፤ ሕዝ​ቤ​ንም ከእ​ጃ​ችሁ አድ​ና​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ