የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 12

12
ነቢዩ እንደ ስደ​ተኛ
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! በዐ​መ​ፀኛ ቤት መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ሃል፤ እነ​ርሱ ያዩ ዘንድ ዐይን አላ​ቸው ነገር ግን አያ​ዩም፤ ይሰ​ሙም ዘንድ ጆሮ አላ​ቸው፤ ነገር ግን አይ​ሰ​ሙም፤ እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና። 3አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የስ​ደ​ተኛ እክት አዘ​ጋጅ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ቀን ለቀን ተማ​ረክ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ከስ​ፍራ ወደ ሌላ ስፍራ ተማ​ር​ከህ ሂድ፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፀኛ ቤት እንደ ሆኑ ምን​አ​ል​ባት ያስ​ተ​ውሉ ይሆ​ናል። 4ቀን ለቀ​ንም በፊ​ታ​ቸው እክ​ት​ህን እንደ ስደ​ተኛ እክት አው​ጣው፤ በማ​ታም ጊዜ በዐ​ይ​ና​ቸው እያ​ዩህ ስደ​ተ​ኞች እን​ደ​ሚ​ወጡ እን​ዲሁ ውጣ። 5በፊ​ታ​ቸ​ውም ግን​ቡን ነድ​ለህ በዚያ ውጣ። 6ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ምል​ክት አድ​ር​ጌ​ሃ​ለ​ሁና በፊ​ታ​ቸው ዕቃ​ህን በት​ከ​ሻህ ላይ አን​ግ​ተው፤ በጨ​ለ​ማም ተሸ​ክ​መህ ውጣ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ዳ​ታይ ፊት​ህን ሸፍን።” 7እን​ዳ​ዘ​ዘ​ኝም አደ​ረ​ግሁ፤ ቀን ለቀ​ንም እክ​ቴን እንደ ስደ​ተኛ እክት አወ​ጣሁ፤ በማ​ታም ጊዜ ግን​ቡን በእጄ ነደ​ልሁ፤ በጨ​ለ​ማም አወ​ጣ​ሁት፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም በት​ከ​ሻዬ ላይ አን​ግቼ ተሸ​ከ​ም​ሁት።
8በነ​ጋ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 9“የሰው ልጅ ሆይ! ዐመ​ፀኛ ቤት የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት፦ የም​ታ​ደ​ር​ገው ምን​ድር ነው? አላ​ሉ​ህ​ምን? 10አን​ተም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ሸክም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖ​ረው አለቃ ላይ፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም በሚ​ኖ​ሩት በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ላይ ነው በላ​ቸው። 11ደግ​ሞም፦ እኔ ምል​ክ​ታ​ችሁ ነኝ፤ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​ባ​ቸ​ዋል፥ እነ​ር​ሱ​ንም ማር​ከው ይወ​ስ​ዷ​ቸ​ዋል በል። 12በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም የሚ​ኖ​ረው አለቃ በት​ከ​ሻው ላይ አን​ግቶ በጨ​ለማ ይወ​ጣል፤ በዚያ ያወጡ ዘንድ ግን​ቡን ይነ​ድ​ላሉ፤ በዐ​ይ​ኑም ምድ​ርን እን​ዳ​ያይ ፊቱን ይሸ​ፍ​ናል። 13መረ​ቤ​ንም በእ​ርሱ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ በወ​ጥ​መ​ዴም ይያ​ዛል፤ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር ወደ ባቢ​ሎን አመ​ጣ​ዋ​ለሁ፤ ሆኖም አያ​ያ​ትም፤ በዚ​ያም ይሞ​ታል። 14የሚ​ረ​ዱ​ት​ንም፥ በዙ​ሪ​ያው ያሉ​ትን ሁሉ፥ ጭፍ​ሮ​ቹ​ንም ሁሉ ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በኋ​ላ​ቸ​ውም ሰይ​ፍን እመ​ዝ​ዛ​ለሁ። 15በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል በም​በ​ት​ና​ቸው ጊዜ፥ በሀ​ገ​ሮ​ችም በም​ዘ​ራ​ቸው ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። 16በሚ​ሄ​ዱ​ባ​ቸ​ውም አሕ​ዛብ መካ​ከል ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይና​ገሩ ዘንድ ከሰ​ይ​ፍና ከራብ፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርም ጥቂ​ቶች ሰዎ​ችን ከእ​ነ​ርሱ አስ​ቀ​ራ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”
17የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 18“የሰው ልጅ ሆይ! እን​ጀ​ራ​ህን በመ​ታ​ወክ ብላ፤ ውኃ​ህ​ንም በፍ​ር​ሃ​ትና በድ​ን​ጋጤ ጠጣ፤ 19ለም​ድ​ሪ​ቱም ሕዝብ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ​ሚ​ኖሩ ስለ እስ​ራ​ኤል ምድ​ርም እን​ዲህ ይላል፦ የሚ​ኖ​ሩ​ባት ሁሉ በዐ​መፅ ይኖ​ራ​ሉና ምድ​ሪቱ በመ​ላዋ ትጠፋ ዘንድ እን​ጀ​ራ​ቸ​ውን በች​ግር ይበ​ላሉ፤ ውኃ​ቸ​ው​ንም በድ​ን​ጋጤ ይጠ​ጣሉ። 20ሰዎች የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ይጠ​ፋሉ፤ ምድ​ሪ​ቱም ውድማ ትሆ​ና​ለች፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።”
21የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 22“የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር፦ ዘመኑ ረዝ​ሞ​አል፤ ራእ​ዩም ሁሉ ጠፍ​ቶ​አል የም​ት​ሉት ምሳ​ሌው ምን​ድን ነው? 23ስለ​ዚህ እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህን ምሳሌ አስ​ቀ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ደግሞ ምሳሌ አድ​ር​ገው አይ​ና​ገ​ሩ​ትም፤ አንተ ግን፦ ዘመ​ኑና የራ​እዩ ሁሉ ነገር ቀር​ቦ​አል በላ​ቸው። 24ከዚ​ህም በኋላ በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት መካ​ከል ከንቱ ራእ​ይና ውሸ​ተኛ ምዋ​ርት አይ​ሆ​ንም። 25እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ የም​ና​ገ​ረ​ውም ቃል ይፈ​ጸ​ማል፤ ደግ​ሞም አይ​ዘ​ገ​ይም፤ እና​ንተ ዐመ​ፀኛ ቤት ሆይ! በዘ​መ​ና​ችሁ ቃሌን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እፈ​ጽ​መ​ው​ማ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
26የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 27“የሰው ልጅ ሆይ! ዐመ​ፀ​ኛው የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት፦ ይህቺ የሚ​ያ​ያት ራእይ ለብዙ ዘመን ናት፤ እር​ሱም ለሩቅ ወራት ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ራል” ይላሉ። 28ስለ​ዚህ በላ​ቸው፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የም​ና​ገ​ረው ቃል ይፈ​ጸ​ማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚ​ዘ​ገይ የለም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ