የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 11

11
በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ የተ​ላ​ለፈ ፍርድ
1መን​ፈ​ስም አነ​ሣኝ፤ ወደ ምሥ​ራ​ቅም አን​ጻር ወደ​ሚ​ያ​ሳ​የው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር ወሰ​ደኝ። እነ​ሆም በበሩ መግ​ቢያ ሃያ አም​ስት ሰዎች ነበሩ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም የሕ​ዝ​ቡን አለ​ቆች የዓ​ዙ​ርን ልጅ ያእ​ዛ​ን​ያ​ንና የበ​ና​ያስ ልጅ ፈላ​ጥ​ያን አየሁ። 2እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ ከን​ቱን የሚ​ያ​ስቡ፥ በዚ​ችም ከተማ ክፉን ምክር የሚ​መ​ክሩ ሰዎች ናቸው። 3እነ​ር​ሱም፦ በውኑ ቤቶች በድ​ን​ገት የሚ​ሠሩ አይ​ደ​ለ​ምን? ይህች ከተማ ድስት እኛም ሥጋ ነን ብለ​ዋል። 4ስለ​ዚህ የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገ​ር​ባ​ቸው፤ ትን​ቢት ተና​ገር።”
5የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በላዬ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል ብለህ ተና​ገር፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ይህን ነገር ተና​ግ​ራ​ች​ኋል፤ እኔም የሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁን በደል አው​ቃ​ለሁ። 6በዚ​ህች ከተማ ውስጥ ግዳ​ዮ​ቻ​ች​ሁን አብ​ዝ​ታ​ች​ኋል፤ በጎ​ዳ​ና​ዎ​ች​ዋም ሙታ​ና​ች​ሁን ሞል​ታ​ች​ኋል። 7ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በመ​ካ​ከ​ልዋ ያኖ​ራ​ች​ኋ​ቸው ግዳ​ዮ​ቻ​ችሁ እነ​ርሱ ሥጋ ናቸው፤ ይህ​ችም ከተማ ድስት ናት፤ እና​ን​ተን ግን ከመ​ካ​ከ​ልዋ አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ። 8ሰይ​ፍን ትፈ​ራ​ላ​ችሁ፤ እኔም ሰይ​ፍን አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 9ከመ​ካ​ከ​ል​ዋም አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በባ​ዕ​ዳ​ንም እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በላ​ያ​ች​ሁም ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ። 10በሰ​ይፍ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 11ይህች ከተማ ድስት አት​ሆ​ን​ላ​ች​ሁም፤ እና​ን​ተም በመ​ካ​ከ​ልዋ ሥጋ አት​ሆ​ኑም፤ እኔም በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 12በት​እ​ዛዜ አል​ሄ​ዳ​ች​ሁ​ምና፥ ፍር​ዴ​ንም አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምና፥ በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም እን​ደ​ሚ​ኖ​ሩት እንደ አሕ​ዛብ ሕግ አድ​ር​ጋ​ች​ኋል።”#ምዕ. 11 ቍ. 12 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
13ትን​ቢ​ትም በተ​ና​ገ​ርሁ ጊዜ የበ​ና​ያስ ልጅ ፈላ​ጥያ ሞተ፤ እኔም በግ​ን​ባሬ ተደ​ፍቼ፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ወዮ! ወዮ​ልኝ! በውኑ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅሬታ ፈጽ​መህ ታጠ​ፋ​ለ​ህን?” ብዬ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኽሁ።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለስ​ደ​ተ​ኞች የሰ​ጠው ተስፋ
14የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 15“የሰው ልጅ ሆይ! በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖሩ፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ራቁ፤ ይህች ምድር ርስት ሆና ለእኛ ተሰ​ጥ​ታ​ለች የሚ​ሉ​አ​ቸው ወን​ድ​ሞ​ች​ህና ዘመ​ዶ​ችህ፥ የም​ርኮ ሰዎ​ች​ህም ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ ያል​ቃሉ። 16ስለ​ዚህ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ወደ አሕ​ዛብ አር​ቄ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ሀገ​ሮ​ችም እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ይሁን እንጂ በመ​ጡ​ባ​ቸው ሀገ​ሮች በእ​ነ​ዚያ ትንሽ መቅ​ደስ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ በል። 17ስለ​ዚ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ እቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከበ​ተ​ን​ሁ​ባ​ቸ​ውም ሀገ​ሮች እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ምድር እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ። 18ወደ​ዚ​ያም ይመ​ጣሉ፤ በደ​ል​ንና ርኵ​ሰ​ት​ንም#ግእዝ “ጣዖ​ታት” ይላል። ሁሉ ከእ​ር​ስዋ ያስ​ወ​ግ​ዳሉ። 19ሌላ ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም አዲስ መን​ፈስ አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ ከሥ​ጋ​ቸ​ውም ውስጥ የድ​ን​ጋ​ዩን ልብ አወ​ጣ​ለሁ፤ የሥ​ጋ​ንም ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ 20በት​እ​ዛ​ዜም ይሄዱ ዘንድ፥ ፍር​ዴ​ንም ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ እነ​ርሱ ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል፥ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ። 21ጣዖት በሚ​ያ​መ​ል​ኩ​በት ልባ​ቸ​ውና በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው እንደ ልባ​ቸው ቢሄዱ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መነ​ሣት
22ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ዘረጉ፥ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ችም በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው ነበሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ክብር በላ​ያ​ቸው ነበረ። 23የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ከከ​ተ​ማ​ዪቱ መካ​ከል ተነ​ሥቶ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ምሥ​ራቅ#“ምሥ​ራቅ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። በኩል በአ​ለው ተራራ ላይ ቆመ። 24መን​ፈ​ስም አነ​ሣኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በራ​እይ ወደ ከላ​ው​ዴ​ዎን ምድር ወደ ምር​ኮ​ኞቹ አመ​ጣኝ። 25ያየ​ሁ​ትም ራእይ ከእኔ ወጣ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያሳ​የ​ኝን ነገር ሁሉ ለም​ር​ኮ​ኞች ተና​ገ​ርሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ