የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 8

8
2፥ ጓጕ​ን​ቸር
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈር​ዖን ግባ፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ። 2ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ብትል ግን እነሆ፥ ሀገ​ር​ህን ሁሉ በጓ​ጕ​ን​ቸ​ሮች እመ​ታ​ለሁ፤ 3ወን​ዙም ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችን ያፈ​ላል፤ ወጥ​ተ​ውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አል​ጋ​ህም፥ ወደ ሹሞ​ች​ህም ቤት፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ላይ፥ ወደ ቡሃ​ቃ​ዎ​ች​ህም፥ ወደ ምድ​ጃ​ዎ​ች​ህም ይገ​ባሉ፤ 4ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችም በአ​ንተ፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም፥ በሹ​ሞ​ች​ህም ሁሉ ላይ ይወ​ጣሉ።” 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን ይዘህ በወ​ን​ዞ​ቹና በመ​ስ​ኖ​ዎቹ፥ በውኃ ማከ​ማ​ቻ​ዎ​ቹም ላይ እጅ​ህን ዘርጋ፤ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ች​ንም አውጣ’ ” በለው። 6አሮ​ንም በግ​ብፅ ውኆች ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ወጡ፤ የግ​ብ​ፅ​ንም ሀገር ሸፈኑ። 7የግ​ብፅ ጠን​ቋ​ዮ​ችም በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ላይ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችን አወጡ።
8ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹን ከእኔ፥ ከሕ​ዝ​ቤም እን​ዲ​ያ​ርቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሠዋ ዘንድ ሕዝ​ቡን እለ​ቅ​ቃ​ለሁ” አላ​ቸው። 9ሙሴም ፈር​ዖ​ንን፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮቹ ከአ​ንተ፥ ከሕ​ዝ​ብ​ህም፥ ከቤ​ቶ​ች​ህም እን​ዲ​ጠፉ፥ በወ​ን​ዙም ብቻ እን​ዲ​ቀሩ፥ ለአ​ንተ፥ ለሹ​ሞ​ች​ህም፥ ለሕ​ዝ​ብ​ህም መቼ እን​ድ​ጸ​ልይ ቅጠ​ረኝ” አለው። ፈር​ዖ​ንም፥ “ነገ” አለው። 10ሙሴም፥ “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ታውቅ ዘንድ እሺ እንደ አልህ ይሁን። 11ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ከአ​ንተ፥ ከቤ​ቶ​ች​ህም፥ ከመ​ን​ደ​ሮ​ች​ህም፥ ከሹ​ሞ​ች​ህም፥ ከሕ​ዝ​ብ​ህም ይሄ​ዳሉ፤ በወ​ን​ዙም ብቻ ይቀ​ራሉ” አለው። 12ሙሴና አሮ​ንም ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጡ፤ ሙሴም ፈር​ዖን እንደ ቀጠ​ረው ሰለ ጓጕ​ን​ቸ​ሮቹ መራቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ። 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ እንደ አለ አደ​ረገ፤ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ከቤት፥ ከመ​ን​ደ​ርም፥ ከሜ​ዳም ሞቱ። 14እንደ ክም​ርም አድ​ር​ገው ሰበ​ሰ​ቡ​አ​ቸው፤ ምድ​ርም ገማች። 15ፈር​ዖ​ንም ጸጥታ እንደ ሆነ በአየ ጊዜ ልቡ ደነ​ደነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።
3፥ ቅማል
16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን በእ​ጅህ ዘርጋ፤ የም​ድ​ሩ​ንም ትቢያ ምታ’ በለው፤ ቅማ​ልም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ ይወ​ጣል።” 17አሮ​ንም እጁን ዘረጋ፤ በበ​ት​ሩም የም​ድ​ሩን ትቢያ መታው፤ በሰ​ውና በእ​ን​ስ​ሳም ላይ ቅማል ሆነ፤ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ የም​ድር ትቢያ ሁሉ ቅማል ሆነ። 18የግ​ብፅ ጠን​ቋ​ዮ​ችም በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው ቅማል ያወጡ ዘንድ እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ ነገር ግን አል​ቻ​ሉም፤ ቅማ​ሉም በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ ነበረ። 19ጠን​ቋ​ዮ​ችም ፈር​ዖ​ንን፥ “ይህስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት ነው” አሉት፤ የፈ​ር​ዖን ልብ ግን ጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።
4፥ ተና​ካሽ ዝንብ
20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ማል​ደህ ተነሣ፤ በፈ​ር​ዖ​ንም ፊት ቁም፤ እነሆ፥ እርሱ ወደ ውኃ ይወ​ር​ዳል፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በም​ድረ በዳ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ኩኝ ሕዝ​ቤን ልቀቅ። 21ሕዝ​ቤን ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ብትል ግን እነሆ፥ በአ​ንተ፥ በሹ​ሞ​ች​ህም፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም፥ በቤ​ቶ​ች​ህም ላይ የውሻ ዝንብ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያን ቤቶች፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ምድር ሁሉ በውሻ ዝንብ ይመ​ላሉ። 22በዚ​ያም ቀን የም​ድር ሁሉ አም​ላክ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ፥ በዚያ የውሻ ዝንብ እን​ዳ​ይ​ሆን ሕዝቤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትን የጌ​ሤ​ምን ምድር እለ​ያ​ለሁ። 23በሕ​ዝ​ቤና በሕ​ዝ​ብህ መካ​ከል እለ​ያ​ለሁ፤ ይህም ነገር ነገ በም​ድ​ሪቱ ላይ ይሆ​ናል።” 24እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አደ​ረገ፤ የው​ሻው ዝን​ብም በፈ​ር​ዖን ቤት፥ በሹ​ሞ​ቹም ቤቶች ውሰጥ፥ በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ መጣ፤ ምድ​ሪ​ቱም ከው​ሻው ዝንብ የተ​ነሣ ጠፋች።
25ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ በዚ​ያች ምድር ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ሠዉ” አላ​ቸው። 26ሙሴም፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ግብ​ፃ​ው​ያን እርም የሚ​ሉ​ትን እን​ሠ​ዋ​ለ​ንና እን​ዲሁ ይሆን ዘንድ አይ​ቻ​ልም፤ እነሆ፥ ግብ​ፃ​ው​ያን እርም የሚ​ሉ​ትን እኛ በፊ​ታ​ቸው ብን​ሠዋ በድ​ን​ጋይ ይወ​ግ​ሩ​ናል። 27እኛስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እን​ሠዋ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘን የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ እን​ሄ​ዳ​ለን” አለ። 28ፈር​ዖ​ንም፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በም​ድረ በዳ ትሠዉ ዘንድ እለ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነገር ግን በጣም ርቃ​ችሁ አት​ሂዱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸል​ዩ​ልኝ” አለ። 29ሙሴም፥ “እነሆ፥ ከአ​ንተ ዘንድ እወ​ጣ​ለሁ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ የውሻ ዝን​ቡም ከአ​ንተ፥ ከሹ​ሞ​ች​ህና ከሕ​ዝ​ብህ ነገ ይር​ቃል፤ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዉ ዘንድ ሕዝ​ቡን እን​ደ​ማ​ት​ለ​ቅቅ እን​ደ​ገና ማታ​ለ​ልን አት​ድ​ገም።” 30ሙሴም ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጣ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ። 31እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ እንደ አለ አደ​ረገ፤ የው​ሻ​ው​ንም ዝንብ ከፈ​ር​ዖን፥ ከሹ​ሞ​ቹም፥ ከሕ​ዝ​ቡም አራቀ፤ አንድ ስንኳ አል​ቀ​ረም። 32ፈር​ዖ​ንም በዚህ ጊዜ ደግሞ ልቡን አደ​ነ​ደነ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አል​ለ​ቀ​ቀም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ