የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 9

9
5፥ የእ​ን​ስ​ሳት ዕል​ቂት
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተህ እን​ዲህ በለው፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ። 2ሕዝ​ቤን ልት​ለ​ቃ​ቸው እንቢ ብትል፥ ብት​ይ​ዛ​ቸ​ውም፥ 3እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በሜዳ ውስጥ በአ​ሉት በከ​ብ​ቶ​ችህ፥ በፈ​ረ​ሶ​ችም፥ በአ​ህ​ዮ​ችም፥ በግ​መ​ሎ​ችም፥ በበ​ሬ​ዎ​ችም፥ በበ​ጎ​ችም ላይ ትሆ​ና​ለች፤ ይኸ​ውም እጅግ ጽኑዕ ሞት ነው፤ 4በዚያ ጊዜም በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ከብ​ቶ​ችና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብ​ቶች መካ​ከል ልዩ​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከብ​ቶች አን​ዳች አይ​ሞ​ትም።” 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ነገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር በም​ድር ላይ ያደ​ር​ጋል ብሎ ጊዜን ወሰነ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያን ነገር በነ​ጋው አደ​ረገ፤ 6የግ​ብ​ፅም ከብት ሁሉ ሞተ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብት ግን አንድ ስንኳ አል​ሞ​ተም። 7ፈር​ዖ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ እን​ዳ​ል​ሞተ በአየ ጊዜ ልቡ ደነ​ደነ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አል​ለ​ቀ​ቀም።
6፥ ሻህኝ
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን፥ “እጃ​ች​ሁን ሞል​ታ​ችሁ ከም​ድጃ አመድ ውሰዱ፤ ሙሴም በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ወደ ሰማይ ይበ​ት​ነው። 9እር​ሱም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ትቢያ ይሆ​ናል፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ ሻህኝ የሚ​ያ​መጣ ቍስል ይሆ​ናል” አላ​ቸው። 10ሙሴም አመ​ዱን በፈ​ር​ዖን ፊት ወስዶ ወደ ሰማይ በተ​ነው፤ በሰ​ውና በእ​ን​ስ​ሳም ላይ ሻህኝ የሚ​ያ​ወጣ ቍስል ሆነ። 11ጠን​ቋ​ዮ​ችም ቍስል ስለ ነበ​ረ​ባ​ቸው በሙሴ ፊት መቆም አል​ቻ​ሉም፤ ቍስል ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንና ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ሁሉ ይዞ​አ​ቸው ነበ​ርና። 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙ​ሴና ለአ​ሮን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለሙ​ሴና ለአ​ሮን” አይ​ልም ፤ ዕብ. “ሙሴን” ብቻ ይጽ​ፋል። እንደ ተና​ገ​ረው አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።
7፥ በረዶ
13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ማል​ደህ ተነሣ፤ በፈ​ር​ዖ​ንም ፊት ቆመህ እን​ዲህ በለው፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ኩኝ ሕዝ​ቤን ልቀቅ። 14በም​ድር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እን​ደ​ሌለ ታውቅ ዘንድ በሰ​ው​ነ​ትህ፥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ላይ መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ሁሉ በዚህ ጊዜ እል​ካ​ለሁ። 15አሁን እጄን ዘር​ግቼ አን​ተን እመ​ታ​ሃ​ለሁ፤ ሕዝ​ብ​ህ​ንም እገ​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ምድ​ራ​ች​ሁም ትመ​ታ​ለች። 16ነገር ግን ኀይ​ሌን እገ​ል​ጥ​ብህ ዘንድ፥ ስሜም በም​ድር ሁሉ ላይ ይነ​ገር ዘንድ ስለ​ዚህ ጠበ​ቅ​ሁህ። 17አንተ ግን እን​ዳ​ት​ለ​ቃ​ቸው ገና በሕ​ዝቤ ላይ ትታ​በ​ያ​ለህ፤ 18እነሆ፥ ከተ​መ​ሠ​ረ​ተች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ በግ​ብፅ ሆኖ የማ​ያ​ውቅ እጅግ ታላቅ በረዶ ነገ በዚህ ጊዜ አዘ​ን​ባ​ለሁ። 19አሁን እን​ግ​ዲህ ፥ ከብ​ቶ​ች​ህ​ንም በሜ​ዳም ያለ​ህን ሁሉ ፈጥ​ነህ ሰብ​ስብ። በሜዳ የተ​ገኘ ወደ ቤት ያል​ገባ ሰውና እን​ስሳ ሁሉ በረዶ ወር​ዶ​በት ይሞ​ታ​ልና።” 20ከፈ​ር​ዖን ሹሞች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የፈራ ከብ​ቶ​ቹን#ዕብ. “አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንና ከብ​ቶ​ቹን” ይላል። ወደ ቤቶቹ ሰበ​ሰበ። 21የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በልቡ ያላ​ሰበ ግን ከብ​ቶ​ቹን በሜዳ ተወ።#ዕብ. “አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንና ከብ​ቶ​ቹን” ይላል።
22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እጅ​ህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ በሰ​ውና በእ​ን​ስ​ሳም በም​ድ​ርም ቡቃያ ሁሉ ላይ በረዶ ይሆ​ናል።” 23ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነጐ​ድ​ጓ​ድና በረዶ ላከ፤ እሳ​ትም ወደ ምድር ወረደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ላይ በረዶ አዘ​ነበ። 24በረ​ዶም ነበረ፤ በበ​ረ​ዶ​ውም መካ​ከል እሳት ይቃ​ጠል ነበር፤ በረ​ዶ​ውም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ሕዝብ ከኖ​ረ​በት ጊዜ ጀምሮ እስ​ከ​ዚች ቀን እንደ እርሱ ያል​ሆነ እጅግ ብዙና ጠን​ካራ ነበረ። 25በረ​ዶ​ውም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ በሜዳ ያለ​ውን ሁሉ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን መታ፤ በረ​ዶ​ውም የእ​ር​ሻን ቡቃያ ሁሉ መታ። የጫ​ካ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ። 26የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተቀ​ም​ጠው በነ​በ​ሩ​ባት በጌ​ሤም ሀገር ብቻ በረዶ አል​ወ​ረ​ደም።
27ፈር​ዖ​ንም ልኮ ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠራ፤ “አሁ​ንም በደ​ልሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ኀጢ​አ​ተ​ኞች ነን። 28እን​ግ​ዲህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ የአ​ም​ላክ ነጐ​ድ​ጓድ፥ በረ​ዶ​ውም፥ እሳ​ቱም ጸጥ ይላል፤ እኔም እለ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ከዚህ አት​ቀ​መ​ጡም” አላ​ቸው። 29ሙሴም፥ “ለፈ​ር​ዖን ከከ​ተማ በወ​ጣሁ ጊዜ እጄን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነች ታውቅ ዘንድ ነጐ​ድ​ጓዱ ጸጥ ይላል፤ በረ​ዶ​ውም፥ ዝና​ቡም ደግሞ አይ​ወ​ር​ድም። 30ነገር ግን አን​ተና ሹሞ​ችህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክን ምን​ጊ​ዜም እን​ደ​ማ​ት​ፈሩ አው​ቃ​ለሁ” አለው። 31ተል​ባ​ውና ገብሱ ተመታ፤ ገብሱ አሽቶ፥ ተል​ባ​ውም አፍ​ርቶ ነበ​ርና። 32ስን​ዴ​ውና አጃው ግን አል​ተ​መ​ቱም፤ ገና ቡቃያ ነበ​ሩና። 33ሙሴም ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ከከ​ተማ ወጣ፤ እጁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘረጋ፤ ነጐ​ድ​ጓ​ዱም፥ በረ​ዶ​ውም ጸጥ አለ፤ ዝና​ቡም በም​ድር ላይ አላ​ካ​ፋም። 34ፈር​ዖ​ንም ዝናቡ፥ በረ​ዶ​ውም፥ ነጐ​ድ​ጓ​ዱም ጸጥ እንደ አለ በአየ ጊዜ በደ​ልን ጨመረ፤ እር​ሱና ሹሞ​ቹም ልባ​ቸ​ውን አደ​ነ​ደኑ። 35የፈ​ር​ዖ​ንም ልብ ጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ አፍ እንደ ተና​ገረ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አል​ለ​ቀ​ቀም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ