“በመሠዊያውም ላይ የምታቀርበው ይህ ነው፤ በቀን በቀን ዘወትር በመሠዊያው ላይ ሁለት ንጹሓን የዓመት ጠቦቶች ታቀርባለህ። አንዱን ጠቦት በነግህ፥ ሁለተኛውንም ጠቦት በሠርክ መሥዋዕት አድርገህ ታቀርበዋለህ። ከአንዱ ጠቦትም ጋር የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመጠጥ ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ። ሁለተኛውንም ጠቦት በሠርክ ታቀርበዋለህ፤ እንደ ነግሁም የእህልና የመጠጥ ቍርባን ታደርግበታለህ፤ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን የእሳት ቍርባን ይሆናል። በዚያ እናገርህ ዘንድ ለአንተ በምገለጥበት በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ለልጅ ልጃችሁ የዘወትር መሥዋዕት ይሆናል። በዚያም የእስራኤልን ልጆች አዝዛለሁ፤ በክብሬም እቀደሳለሁ። የምስክሩንም ድንኳን መሠዊያውንም እቀድሳለሁ፤ በክህነትም ያገለግሉኝ ዘንድ አሮንንና ልጆቹን እቀድሳለሁ። በእስራኤልም ልጆች መካከል እኖራለሁ፤ አምላካቸውም እሆናቸዋለሁ። በእነርሱ እጠራ ዘንድ፥ አምላክም እሆናቸው ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው አምላካቸው እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
ኦሪት ዘፀአት 29 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፀአት 29:38-46
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች