የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 29

29
ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ክህ​ነ​ትን ለመ​ስ​ጠት የተ​ሰጠ ሕግ
(ዘሌ. 8፥1-36)
1“እኔ​ንም በክ​ህ​ነት እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉኝ ትቀ​ድ​ሳ​ቸው ዘንድ የም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ነገር ይህ ነው፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ወይ​ፈ​ንና ሁለት አውራ በጎች ትወ​ስ​ዳ​ለህ። 2ቂጣ እን​ጀራ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወሰ የቂጣ እን​ጎቻ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ቀባ ስስ ቂጣ ከመ​ል​ካም ስንዴ ታደ​ር​ጋ​ለህ። 3በአ​ንድ መሶ​ብም ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከወ​ይ​ፈ​ኑና ከሁ​ለቱ አውራ በጎች ጋር በመ​ሶብ ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ። 4አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በው​ኃም ታጥ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ። 5ልብ​ሶ​ችን ወስ​ደህ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን የነጭ ሐር እጀ ጠባብ ቀሚስ፥ ልብሰ መት​ከ​ፍና ልብሰ እን​ግ​ድዓ ታለ​ብ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ለእ​ር​ሱም ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ከል​ብሰ መት​ከፉ ጋር አያ​ይ​ዝ​ለት። 6አክ​ሊ​ል​ንም በራሱ ላይ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የወ​ር​ቁ​ንም ቀጸላ በአ​ክ​ሊሉ ላይ ታኖ​ራ​ለህ። 7የቅ​ብ​ዐ​ት​ንም ዘይት ወስ​ደህ በራሱ ላይ ታፈ​ስ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ባ​ው​ማ​ለህ። 8ልጆ​ቹ​ንም ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቀሚ​ሶ​ች​ንም ታለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ 9#ዕብ. “አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን” ይላል።በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም ታስ​ታ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቆብ​ንም ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐ​ትም ክህ​ነት ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም የአ​ሮ​ን​ንና የል​ጆ​ቹን እጆች ትቀ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።
10“ወይ​ፈ​ኑ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን በር ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጆ​ቻ​ቸ​ውን በወ​ይ​ፈኑ ራስ ላይ ይጭ​ናሉ። 11ወይ​ፈ​ኑ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በር አጠ​ገብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታር​ደ​ዋ​ለህ። 12ከወ​ይ​ፈ​ኑም ደም ወስ​ደህ በመ​ሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ላይ በጣ​ትህ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም ደም ሁሉ ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች ታፈ​ስ​ሰ​ዋ​ለህ። 13የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ ሁሉ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ያለ​ውን ስብ ወስ​ደህ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ታስ​ቀ​ም​ጣ​ለህ። 14የወ​ይ​ፈ​ኑን ሥጋ ግን፥ ቍር​በ​ቱ​ንም፥ ፈር​ሱ​ንም ከሰ​ፈር ውጭ በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።
15“አን​ደ​ኛ​ው​ንም አውራ በግ ትወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በአ​ው​ራው በግ ራስ ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ይጭ​ናሉ። 16አው​ራ​ው​ንም በግ ታር​ደ​ዋ​ለህ፤ ደሙ​ንም ወስ​ደህ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ትረ​ጨ​ዋ​ለህ። 17አው​ራ​ው​ንም በግ በየ​ብ​ልቱ ትቈ​ር​ጠ​ዋ​ለህ፤ የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹ​ንም በውኃ ታጥ​ባ​ለህ፤ ከብ​ል​ቱና ከራ​ሱም ጋር ታኖ​ረ​ዋ​ለህ። 18አው​ራ​ንም በግ በሞ​ላው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ስለ ጣፋጭ ሽታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ረበ የእ​ሳት ቍር​ባን ነው።
19“ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም አውራ በግ ትወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም እጆ​ቻ​ቸ​ውን በአ​ው​ራው በግ ራስ ላይ ይጭ​ናሉ። 20አው​ራ​ው​ንም በግ ታር​ደ​ዋ​ለህ፤ ደሙ​ንም ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የአ​ሮ​ን​ንም የቀኝ ጆሮ ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንና የቀኝ እግ​ሩን አውራ ጣት ጫፍ፥ የል​ጆ​ቹ​ንም የቀኝ ጆሮ​አ​ቸ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃ​ቸ​ው​ንና የቀኝ እግ​ራ​ቸ​ውን አውራ ጣት ታስ​ነ​ካ​ለህ፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ትረ​ጨ​ዋ​ለህ። 21በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ካለው ደም ከቅ​ብ​ዐት ዘይ​ትም ወስ​ደህ በአ​ሮ​ንና በል​ብሱ ላይ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ባሉት በል​ጆ​ቹና በል​ብ​ሶ​ቻ​ቸው ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም ልብ​ሶ​ቹም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆቹ፥ ልብ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ይቀ​ደ​ሳሉ። 22የበ​ጉ​ንም ስብ፥ የሆድ ዕቃ​ውን የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ፥ የቀ​ኙ​ንም ወርች ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የሚ​ቀ​ደ​ሱ​በት ነውና። 23በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ሶብ ካለው አንድ የዘ​ይት እን​ጀ​ራና አንድ የቂጣ እን​ጐቻ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤#ዕብ. “አንድ እን​ጀራ፥ አን​ድም የዘ​ይት እን​ጀራ፥ አን​ድም ስስ ቂጣ” ይላል። 24ሁሉ​ንም በአ​ሮን እጆ​ችና በል​ጆቹ እጆች ታኖ​ረ​ዋ​ለህ፤ ለሚ​ለይ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትለ​የ​ዋ​ለህ። 25ከእ​ጃ​ቸ​ውም ትቀ​በ​ለ​ዋ​ለህ፤ በመ​ሥ​ዊ​ያ​ውም ላይ ከሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ታቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ፤ እርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት ነው።
26“ለአ​ሮ​ንም ክህ​ነት የታ​ረ​ደ​ውን የአ​ው​ራ​ውን በግ ፍር​ምባ ወስ​ደህ ለሚ​ለይ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትለ​የ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም የአ​ንተ ወግ ይሆ​ናል። 27ከሚ​ካ​ኑ​በ​ትም አውራ በግ የተ​ወ​ሰደ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ወግ የሚ​ሆን ለመ​ሥ​ዋ​ዕት የተ​ለ​የ​ውን ፍር​ም​ባና የተ​ነ​ሣ​ውን ወርች ትቀ​ድ​ሳ​ለህ። 28ይህም የተ​ለየ ቍር​ባን ነውና ከእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ል​ጆች ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የአ​ሮ​ንና የል​ጆቹ ሕግ ይሁን፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው የተ​ለየ ቍር​ባን ይሆ​ናል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ቍር​ባን ይሆ​ናል።
29“የአ​ሮ​ንም የቅ​ድ​ስ​ናው ልብስ ይቀ​ቡ​በ​ትና እጆ​ቻ​ቸው ይቀ​ደ​ሱ​በት ዘንድ ከእ​ርሱ በኋላ ለል​ጆቹ ይሁን። 30ከል​ጆ​ቹም በእ​ርሱ ፋንታ ካህን የሚ​ሆ​ነው በመ​ቅ​ደስ ለማ​ገ​ል​ገል ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ሲገባ ሰባት ቀን ይል​በ​ሰው።
31“የቅ​ድ​ስ​ና​ው​ንም#ዕብ. “የሚ​ካ​ን​በ​ትን” ይላል። በግ ወስ​ደህ ሥጋ​ውን በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ትቀ​ቅ​ለ​ዋ​ለህ። 32አሮ​ንና ልጆ​ቹም የአ​ው​ራ​ውን በግ ሥጋ፥ በመ​ሶ​ብም ያለ​ውን እን​ጀራ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በር ይበ​ሉ​ታል። 33ለመ​ክ​በ​ራ​ቸው እጆ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ድሱ ዘንድ በተ​ቀ​ደ​ሱ​በት በዚያ ቦታ ይብ​ሉት፤ የባ​ዕድ ልጅ ግን አይ​ብ​ላው፤ የተ​ቀ​ደሰ ነውና። 34ከቅ​ድ​ስ​ናው መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ ወይም እን​ጀራ እስከ ነገ ቢተ​ርፍ፥ የቀ​ረ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ፤ የተ​ቀ​ደሰ ነውና አይ​በ​ላም።
35“እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁ​ህም ሁሉ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ እን​ዲህ አድ​ርግ፤ ሰባት ቀን እጆ​ቻ​ቸ​ውን ትቀ​ድ​ሳ​ለህ። 36ዕለት ዕለ​ትም ስለ ማስ​ተ​ስ​ረይ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ኑን ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ማስ​ተ​ስ​ረ​ያም ባደ​ረ​ግህ ጊዜ መሠ​ዊ​ያ​ውን ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ቅዱ​ስም ይሆን ዘንድ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ። 37ሰባት ቀን መሠ​ዊ​ያ​ውን ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሰ​ው​ማ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናል፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።
የዘ​ወ​ትር መሥ​ዋ​ዕት
(ዘኍ​. 28፥1-8)
38“በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የም​ታ​ቀ​ር​በው ይህ ነው፤ በቀን በቀን ዘወ​ትር በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ሁለት ንጹ​ሓን የዓ​መት ጠቦ​ቶች ታቀ​ር​ባ​ለህ። 39አን​ዱን ጠቦት በነ​ግህ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ጠቦት በሠ​ርክ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ። 40ከአ​ንዱ ጠቦ​ትም ጋር የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ በሆነ ተወ​ቅጦ በተ​ጠ​ለለ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመ​ጠጥ ቍር​ባን የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ታቀ​ር​ባ​ለህ። 41ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ጠቦት በሠ​ርክ ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ፤ እንደ ነግ​ሁም የእ​ህ​ልና የመ​ጠጥ ቍር​ባን ታደ​ር​ግ​በ​ታ​ለህ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የእ​ሳት ቍር​ባን ይሆ​ናል። 42በዚያ እና​ገ​ርህ ዘንድ ለአ​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ወ​ትር መሥ​ዋ​ዕት ይሆ​ናል። 43በዚ​ያም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አዝ​ዛ​ለሁ፤ በክ​ብ​ሬም እቀ​ደ​ሳ​ለሁ። 44የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም እቀ​ድ​ሳ​ለሁ፤#ዕብ. “ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ጋር በዚያ እገ​ኛ​ለሁ፤ ድን​ኳ​ኑም በክ​ብሬ ይቀ​ደ​ሳል” ይላል። በክ​ህ​ነ​ትም ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን እቀ​ድ​ሳ​ለሁ። 45በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል እኖ​ራ​ለሁ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ። 46በእ​ነ​ርሱ እጠራ ዘንድ፥ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸው ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ቸው አም​ላ​ካ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ