ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2
2
1እናንተም በኀጢአታችሁ#ግሪኩ “በበደላችሁና በኃጢአታችሁ” ይላል። ምውታን ሆናችሁ ነበር። 2ይኸውም ቀድሞ በዚህ ዓለም ሥርዐት፥ አሁን በከሓድያን ልጆች የሚበረታታባቸውና፥ በነፋስ አምሳል የሚገዛቸው አለቃ እንደ ነበረው ፈቃድ ጸንታችሁ የነበራችሁበት ነው። 3እኛ ሁላችን ቀድሞ እንደ ሥጋችን ምኞት ኖርን፤ የሥጋችንንም ፈቃድና ያሰብነውን አደረግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥአንም ሁሉ#ግሪኩ “እንደ ሌሎችም” ይላል። የጥፋት ልጆች ሆንን። 4እግዚአብሔር ግን በምሕረቱ ባለጸግነትና በወደደን በፍቅሩ ብዛት፥ 5#ቈላ. 2፥14። በኃጢአታችን የሞትን ሳለን በክርስቶስ ሕይወትን ሰጠን፤ በጸጋውም ዳንን። 6በኢየሱስ ክርስቶስም አስነሥቶ በሰማያት ከእርሱ ጋር አኖረን። 7በኢየሱስ ክርስቶስ ይቅር ስላለን የጸጋውን ባለጠግነት ብዛት በሚመጣው ዓለም ይገልጥ ዘንድ፥ 8አምነን በጸጋው ድነናልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ የእናንተ ሥራ አይደለም። 9የሚመካም እንዳይኖር በምግባራችን አይደለም። 10እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ላዘጋጀው በጎ ሥራ በኢየሱስ ክርስቶስ የፈጠረን ፍጥረቱ ነንና።
ሁለቱን አንድ ያደረገ ሰላም
11እናንተ አሕዛብ አስቡ፤ ቀድሞ በሥጋ ሥርዐት ነበራችሁ፤ ያልተገዘሩም ይሉአችሁ ነበር፤ እንዲህ የሚሉአችሁም የተገዘሩ ሰዎች ናቸው፤ ግዝረት ግን በሥጋ ላይ የሚደረግ የሰው እጅ ሥራ ነው። 12ያንጊዜ ክርስቶስን አታውቁትም ነበር፤ ከእስራኤል ሕግ የተለያችሁ ነበራችሁ፤ ከተስፋው ሥርዐትም እንግዶች ነበራችሁ፤ ተስፋም አልነበራችሁም፤ በዚህም ዓለም እግዚአብሔርን አታውቁትም ነበር። 13አሁን ግን ቀድሞ ርቃችሁ የነበራችሁ እናንተ በኢየሱስ ክርስቶስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀረባችሁ። 14ሁለቱን አንድ ያደረገ ሰላማችን እርሱ ነውና፥ በሥጋውም በመካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ ጥልን ሻረ። 15ሁለቱንም አድሶ አንድ ያደርጋቸው ዘንድ በሥርዐቱ የትእዛዝን ሕግ አጠፋ፤ ዕርቅንም አደረገ። 16#ቈላ. 1፥20። በመስቀሉም በአንድ ሥጋው ሁለቱን ወደ እግዚአብሔር አቀረባቸው፤ በእርሱም ጥልን አጠፋ። 17#ኢሳ. 57፥19። መጥቶም፤ ቀርበን ለነበርነው ሰላምን፥ ርቃችሁ ለነበራችሁት ለእናንተም ሰላምን ሰጠን። 18እርሱ መርቶናልና፤ ሁለታችንንም በመንፈስ ቅዱስ ወደ አባቱ አቅርቦናልና።#ግሪኩ “በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና” ይላል። 19እንግዲህስ ወዲህ እናንተ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም። 20በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ታንጻችኋልና የሕንጻው የማዕዘን ራስ ድንጋይም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ 21እርሱም ሕንጻ ሁሉ የሚያያዝበት፥ የእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ ግንብ የሚያድግበት ነው። 22እናንተ በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ልትሆኑ በእርሱ ታነጻችሁ።
Currently Selected:
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ