የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 3

3
የጳ​ው​ሎስ መታ​ሰር
1ስለ​ዚህ አሕ​ዛብ ሆይ ስለ እና​ንተ እኔ ጳው​ሎስ የክ​ር​ስ​ቶስ እስ​ረ​ኛው ነኝ። 2ስለ እና​ንተ የሰ​ጠ​ኝን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጸ​ጋ​ውን ስጦታ#ግሪኩ “መጋ​ቢ​ነት” ይላል። ሰም​ታ​ች​ኋል። 3አስ​ቀ​ድሞ በጥ​ቂቱ እንደ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ ይህን ምሥ​ጢር ገልጦ አሳ​ይ​ቶ​ኛ​ልና። 4ይህ​ንም በም​ታ​ነ​ቡ​በት ጊዜ፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ምሥ​ጢር ማስ​ተ​ዋ​ሌን ለማ​ወቅ ትች​ላ​ላ​ችሁ። 5በሌላ ዘመን ለሰው ልጆች ያል​ተ​ገ​ለጠ ዛሬ ለቅ​ዱ​ሳን ሐዋ​ር​ያ​ቱና ለነ​ቢ​ያቱ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ እንደ ተገ​ለጠ፥ 6#ቈላ​. 1፥26-27። አሕ​ዛ​ብን ወራ​ሾ​ቹና አካሉ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ፥ በወ​ን​ጌ​ልም ትም​ህ​ርት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሆ​ነው ተስፋ አንድ ይሆኑ ዘንድ። 7በኀ​ይሉ አጋ​ዥ​ነት እንደ ሰጠኝ እንደ ጸጋው ስጦታ መጠን እኔ መል​እ​ክ​ተ​ኛና አዋጅ ነጋሪ የሆ​ን​ሁ​ለት፥ 8ከቅ​ዱ​ሳን ሁሉ ለማ​ንስ ለእኔ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ባለ​ጸ​ግ​ነት ለአ​ሕ​ዛብ አስ​ተ​ምር ዘንድ ይህን ጸጋ ሰጠኝ። 9ሁሉን በፈ​ጠረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​ሰ​ወረ የዚህ ምሥ​ጢር ሥር​ዐ​ት​ንም ለሁሉ እገ​ልጥ ዘንድ፤ 10ብዙ ልዩ ልዩ የሆ​ነች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኩል በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለ​ቆ​ችና ሥል​ጣ​ናት ትታ​ወቅ ዘንድ፤ 11ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር የወ​ሰ​ናት፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም የፈ​ጸ​ማት፥ 12እኛ ጸጋ​ንና ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ያገ​ኘ​ን​በት፥ በሃ​ይ​ማ​ኖት ወደ​ሚ​ገ​ኘው ተስ​ፋም ያደ​ረ​ሰ​በት፤ 13ስለ​ዚ​ህም ስለ እና​ንተ ለክ​ብ​ራ​ችሁ የም​ታ​ገ​ኘ​ኝን መከ​ራ​ዬን ቸል እን​ዳ​ይ​ላት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እማ​ል​ደ​ዋ​ለሁ።#ምዕ. 3 ቍ. 13 “... ስለ እና​ንተ ስላለ መከ​ራዬ እን​ዳ​ት​ታ​ክቱ እለ​ም​ና​ች​ኋ​ለሁ ክብ​ራ​ችሁ ነውና” ይላል።
የጳ​ው​ሎስ ጸሎት
14ስለ​ዚ​ህም በል​ቡ​ናዬ ተን​በ​ር​ክኬ ለአብ እሰ​ግ​ዳ​ለሁ። 15በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያሉ ነገ​ዶች ሁሉ ለሚ​ጠ​ሩት ለእ​ርሱ፤ 16እንደ ጌት​ነቱ ምላት ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ኀይል ያጸ​ና​ችሁ ዘንድ። 17በል​ባ​ችሁ ውስጥ በፍ​ቅር ሥር መሠ​ረ​ታ​ችሁ የጸና ሲሆን ክር​ስ​ቶስ በሃ​ይ​ማ​ኖት በሰው ውስጥ ያድ​ራ​ልና። 18ስፋ​ቱና ርዝ​መቱ፥ ምጥ​ቀ​ቱና ጥል​ቀቱ ምን ያህል እንደ ሆነ ከቅ​ዱ​ሳን ሁሉ ጋር ለማ​ስ​ተ​ዋል ትችሉ ዘንድ፥ 19የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ፍቅር ለመ​ረ​ዳት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍጹ​ም​ነት በሁሉ ፍጹ​ማን ትሆኑ ዘንድ።
20በከ​ሃ​ሊ​ነቱ እንደ ረዳን መጠን፥ የም​ና​ስ​በ​ው​ንና የም​ን​ለ​ም​ነ​ውን ሁሉ ትሠሩ ዘንድ፥ ታበ​ዙም ዘንድ ሊያ​ጸ​ና​ችሁ ለሚ​ችል፥ 21ለእ​ርሱ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ፥ በት​ው​ልድ ሁሉ ምስ​ጋና ይሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ አሜን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ