የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 4:4-8

መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 4:4-8 አማ2000

እኔ ድካ​ምን ሁሉና የብ​ል​ሃት ሥራ​ውን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፥ ለሰ​ውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ቅን​አ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ነሣ አየሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው። ሰነፍ እጆ​ቹን ኰር​ትሞ ይቀ​መ​ጣል፥ የገዛ ሥጋ​ው​ንም ይበ​ላል። በድ​ካ​ምና ነፋ​ስን በመ​ከ​ተል ከሁ​ለት እጅ ሙሉ ይልቅ አንድ እጅ ሙሉ በዕ​ረ​ፍት ይሻ​ላል። እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ከንቱ ነገ​ርን አየሁ። አንድ ሰው ብቻ​ውን አለ፥ ሁለ​ተ​ኛም የለ​ውም፥ ልጅም ሆነ ወን​ድም የለ​ውም፤ ለድ​ካሙ ግን መጨ​ረሻ የለ​ውም፥ ዐይ​ኖ​ቹም ከባ​ለ​ጠ​ግ​ነት አይ​ጠ​ግ​ቡም። ለማን እደ​ክ​ማ​ለሁ? ሰው​ነ​ቴ​ንስ ከደ​ስታ ለምን እነ​ፍ​ጋ​ታ​ለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።