የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ አሞጽ 2

2
ስለ ሞዓብ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ንጉሥ አጥ​ንት አመድ እስ​ኪ​ሆን ድረስ አቃ​ጥ​ሎ​ታ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የሞ​ዓብ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ#“መቅ​ሰ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም። 2በሞ​ዓብ ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የከ​ተ​ሞ​ች​ዋ​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች፤ ሞዓ​ብም በድ​ካ​ምና በው​ካታ፥ በመ​ለ​ከ​ትም ድምፅ ይሞ​ታል፤ 3ፈራ​ጅ​ንም ከመ​ካ​ከ​ልዋ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አለ​ቆ​ች​ዋን ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
ስለ ይሁዳ
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም አል​ጠ​በ​ቁ​ምና፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የተ​ከ​ተ​ሉት ከንቱ ነገር#ዕብ. “ጣዖት” ይላል። አስ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የይ​ሁዳ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ#“መቅ​ሰ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም። 5በይ​ሁዳ ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች።”
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ጻድ​ቁን በብር፥ ችጋ​ረ​ኛ​ው​ንም ምድ​ርን በሚ​ረ​ግ​ጡ​በት አንድ ጥንድ ጫማ ሸጠ​ው​ታ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የእ​ስ​ራ​ኤል ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ#“መቅ​ሰ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም። 7የድ​ሆ​ችን ራስ ይቀ​ጠ​ቅ​ጣሉ፤ የት​ሑ​ታ​ን​ንም ፍርድ ያጣ​ም​ማሉ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ስም ያረ​ክሱ ዘንድ አባ​ትና ልጁ ወደ አን​ዲት ሴት ይገ​ባሉ፤ 8ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አስ​ረው ለመ​ሥ​ዊ​ያው መጋ​ረጃ ያደ​ር​ጋሉ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም ቤት የቅ​ሚያ ወይን ጠጅ ይጠ​ጣሉ።#ዕብ. “በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ሁሉ አጠ​ገብ ለመ​ያ​ዣ​ነት በተ​ወ​ሰ​ደው ልብስ ላይ ይተ​ኛሉ” ይላል። 9እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብር​ታ​ቱም እንደ ወይራ ዛፍ የነ​በ​ረ​ውን አሞ​ራ​ዊ​ውን ከፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋሁ፤ ፍሬ​ው​ንም ከላዩ፥ ሥሩ​ንም ከታቹ አጠ​ፋሁ። 10የአ​ሞ​ራ​ዊ​ው​ንም ምድር ትወ​ርሱ ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ኋ​ችሁ፤ በም​ድረ በዳም አርባ ዓመት መራ​ኋ​ችሁ። 11ከወ​ንድ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ነቢ​ያ​ትን፥ ከጐ​በ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ለእኔ የተ​ለ​ዩ​ትን#ዕብ. “ናዝ​ራ​ው​ያ​ንን” ይላል። አስ​ነ​ሣሁ፤ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! ይህ እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለ​ምን?” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 12“እና​ንተ ግን ለእኔ የተ​ለ​ዩ​ትን#ዕብ. “ናዝ​ራ​ው​ያ​ንን” ይላል። የወ​ይን ጠጅ አጠ​ጣ​ች​ኋ​ቸው፤ ነቢ​ያ​ቱ​ንም፥ “ትን​ቢ​ትን አት​ና​ገሩ ብላ​ችሁ ከለ​ከ​ላ​ች​ኋ​ቸው።
13“ስለ​ዚህ ሠረ​ገላ ብር​ዑን እን​ዲ​ያ​ደቅ፥ በበ​ታ​ቻ​ችሁ ባለ መሬት እኔ አደ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ። 14የሚ​ሮጥ ሰው ማም​ለጥ አይ​ች​ልም፤ ኀይ​ለ​ኛ​ውም በብ​ር​ታቱ አይ​ዝም፤ አር​በ​ኛ​ውም ነፍ​ሱን አያ​ድ​ንም። 15ቀስ​ተ​ኛ​ውም አይ​ቆ​ምም፤ ፈጣ​ኑም አያ​መ​ል​ጥም፤ ፈረ​ሰ​ኛ​ውም ነፍ​ሱን አያ​ድ​ንም፤ 16ልበ ሙሉው ኀይ​ለ​ኛም በኀ​ይሉ አይ​ተ​ማ​መ​ንም፤ ነገር ግን በዚያ ቀን ዕራ​ቁ​ቱን ሆኖ ይሸ​ሻል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ