የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ አሞጽ 1

1
1በቴ​ቁሔ በላም ጠባ​ቂ​ዎች መካ​ከል የነ​በረ አሞጽ በይ​ሁዳ ንጉሥ በዖ​ዝ​ያን ዘመን፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን፥ የም​ድር መና​ወጥ ከሆ​ነ​በት ከሁ​ለት ዓመት በፊት ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም#ዕብ. “እስ​ራ​ኤል” ይላል። ያየው ቃል ይህ ነው።
2እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ሆኖ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ይና​ገ​ራል፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆኖ ቃሉን ይሰ​ጣል፤ የእ​ረ​ኞ​ችም ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ የቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም ራስ ይደ​ር​ቃል።”
ስለ ቂር
3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የገ​ለ​ዓ​ድን ነፍሰ ጡሮች በብ​ረት መጋዝ ሰን​ጥ​ቀ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና#ዕብ. “በብ​ረት መን​ኰ​ራ​ኵር ረግ​ጠ​ዋ​ልና” ይላል። ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የደ​ማ​ስቆ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም። 4በአ​ዛ​ሄል ቤት ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የወ​ልደ አዴ​ር​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች። 5የደ​ማ​ስ​ቆ​ንም ቍል​ፎች እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ በአ​ዎን ሸለቆ የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ሰዎች አጠ​ፋ​ለሁ፤ የካ​ራን ሰዎች ወገ​ኖ​ች​ንም እቈ​ራ​ር​ጣ​ለሁ፤ የሶ​ርያ ሕዝ​ብም ወደ ቂር ይማ​ረ​ካሉ፤”#ዕብ. “በትር የያ​ዘ​ው​ንም ከዔ​ደን ቤት አጠ​ፋ​ለሁ” ይላል። ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
ስለ ፍል​ስ​ጥ​ኤም
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በኤ​ዶ​ም​ያስ ይዘ​ጉ​ባ​ቸው#ዕብ. “ለኤ​ዶ​ም​ያስ አሳ​ል​ፈው ይስ​ጧ​ቸው” ይላል። ዘንድ የሰ​ሎ​ሞ​ንን#“የሰ​ሎ​ሞ​ንን” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ምርኮ ማር​ከ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጋዛ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ#“መቅ​ሰ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ” በዕብ. ብቻ። አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም። 7በጋዛ ቅጥር ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋ​ንም#ዕብ. “አዳ​ራ​ሾ​ች​ዋን” ይላል። ትበ​ላ​ለች። 8የአ​ዛ​ጦን ነዋ​ሪ​ዎ​ችን አጠ​ፋ​ለሁ፤ የአ​ስ​ቀ​ሎ​ናም ሕዝብ ይጠ​ፋ​ለሁ፤#ዕብ. “በትረ መን​ግ​ሥት የያ​ዘ​ው​ንም ከእ​ስ​ቀ​ሎና” ይላል። እጄ​ንም በአ​ቃ​ሮን ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የቀ​ሩ​ትም ይጠ​ፋሉ” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
ስለ ጢሮስ
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የሰ​ሎ​ሞን ምር​ኮ​ኞ​ችን በኤ​ዶ​ም​ያስ ዘግ​ተ​ዋ​ልና፥#ዕብ. “ምር​ኮ​ኞ​ችን ሁሉ ለኤ​ዶ​ም​ያስ አሳ​ል​ፈው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና” ይላል። የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ንም ቃል ኪዳን አላ​ሰ​ቡ​ምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢ​ሮስ ኀጢ​አት አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።#ዕብ. “መቅ​ሰ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ” ይላል። 10በጢ​ሮስ ቅጥር ላይ እሳ​ትን አሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋ​ንም ትበ​ላ​ለች።”
ስለ ኤዶም
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦“ወን​ድ​ሙን በሰ​ይፍ አሳ​ድ​ዶ​ታ​ልና፥ በም​ድር ላይም ማኅ​ፀ​ንን አር​ክ​ሶ​አ​ልና፥ የሚ​ዘ​ል​ፈ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ውን#ዕብ. “ቍጣ​ው​ንም ሁል​ጊዜ አበ​ር​ት​ቶ​አ​ልና” ይላል። በር​ብ​ሮ​አ​ልና፥ መዓ​ቱ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጠብ​ቆ​አ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የኤ​ዶ​ም​ያስ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ#“መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም። 12በቴ​ማን ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የቅ​ጥ​ር​ዋ​ንም መሠ​ረ​ቶች#ዕብ. “የባ​ሶ​ራ​ንም አዳ​ራ​ሾች” ይላል። ትበ​ላ​ለች።”
ስለ አሞን
13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ዳር​ቻ​ቸ​ውን ያሰፉ ዘንድ የገ​ለ​ዓ​ድን ነፍሰ ጡሮች ቀድ​ደ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የአ​ሞን ልጆች ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስም። 14በራባ ቅጥር ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በጦ​ር​ነት ቀን በጩ​ኸት#ዕብ. “በአ​ውሎ ነፋስ” ይላል። መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋን ትበ​ላ​ለች፤ በፍ​ጻ​ሜ​ዋም ቀን ትና​ወ​ጣ​ለች። 15ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውን፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንና ካህ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን#“ካህ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን” የሚ​ለው በዕብ. የለም። በአ​ን​ድ​ነት ይማ​ር​ኳ​ቸ​ዋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ