ትንቢተ ሆሴዕ 14
14
እስራኤል ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ መጠራታቸው
1ሰማርያ በአምላክዋ ላይ ዐምፃለችና ፈጽማ ትጠፋለች፤ በሰይፍም ይወድቃሉ፤ ሕፃኖቻቸውንም ይጥሉአቸዋል፤ እርጉዞቻቸውንም ይሰነጥቋቸዋል። 2እስራኤል ሆይ! በኀጢአትህ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ። 3ከእናንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተመለሱ። እንዲህም በሉት፥ “ኀጢአትን ሁሉ አስወግድ፤ በቸርነትም ተቀበለን፤ በወይፈንም ፈንታ የከንፈራችንን ፍሬ ለአንተ እንሰጣለን። 4አሦር አያድነንም፤ በፈረስም ላይ አንቀመጥም፤ ድሃአደጉም በአንተ ዘንድ ይቅርታን ያገኛልና ከእንግዲህ ወዲህ የእጆቻችንን ሥራ አምላኮቻችን ናችሁ አንላቸውም።”
5ቍጣዬ ከእርሱ ዘንድ ተመልሶአልና ሀገራቸውን አድናለሁ፤ በእውነትም እወድዳቸዋለሁ። 6ለእስራኤልም እንደ ጠል እሆነዋለሁ፤ እንደ አበባም ያብባል፥ እንደ ሊባኖስም ሥሩን ይሰድዳል። 7ቅርንጫፎቹም ይዘረጋሉ፤ ውበቱም እንደ ወይራ፥ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ይሆናል። 8ተመልሰውም ከጥላው ሥር ይቀመጣሉ፤ በሕይወትም ይኖራሉ፤ ከእህሉም የተነሣ ይጠግባሉ፤ እንደ ወይንም አረግ ያብባሉ ፤ መታሰቢያውም እንደ ሊባኖስ ወይን ይሆናል። 9ከእንግዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤፍሬም ምንድን ነው? እኔ አደከምሁት፤ አጸናሁትም፤ እኔ እንደ ተወደደ አበባ አፈራዋለሁ፤ ፍሬህም በእኔ ዘንድ ይገኛል።
10ይህን ነገር የሚያስተውል ጠቢብ፤ የሚያውቃትም አስተዋይ ማን ነው? የእግዚአብሔር መንገዶች ቀናዎች ናቸው፥ ጻድቃንም ይሄዱባቸዋል፤ ኃጥአን ግን ይወድቁባቸዋል።
Currently Selected:
ትንቢተ ሆሴዕ 14: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ