የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 21:27-40

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 21:27-40 አማ2000

በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከእ​ስያ የመጡ አይ​ሁድ ጳው​ሎ​ስን በመ​ቅ​ደስ አዩት፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ በእ​ርሱ ላይ አነ​ሳ​ሥ​ተው ያዙት። እየ​ጮ​ሁም እን​ዲህ አሉ፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ ርዱን፤ በየ​ስ​ፍ​ራው ሕዝ​ባ​ች​ንን፥ ኦሪ​ት​ንም፥ ይህ​ንም ስፍራ የሚ​ቃ​ወም ትም​ህ​ርት ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር እነሆ፥ ይህ ሰው ነው፤ አሁ​ንም አረ​ማ​ው​ያ​ንን ወደ መቅ​ደስ አስ​ገባ፤ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም አረ​ከሰ። የኤ​ፌ​ሶን ሀገር ሰው የሆነ ጥሮ​ፊ​ሞ​ስን ከጳ​ው​ሎስ ጋር በከ​ተማ አይ​ተ​ውት ነበ​ርና፤ ጳው​ሎ​ስም ወደ ቤተ መቅ​ደስ ያስ​ገ​ባው መስ​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና። ከተ​ማ​ውም ሁሉ ታወከ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እየ​ሮጡ ሄደው ጳው​ሎ​ስን ጐት​ተው ከቤተ መቅ​ደስ አወ​ጡት፤ በሩ​ንም ሁሉ ዘጉ። ሊገ​ድ​ሉ​ትም ፈል​ገው ብዙ ደበ​ደ​ቡት፤ ወዲ​ያ​ውም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመ​ላዋ እንደ ታወ​ከች የሚ​ገ​ልጥ መል​እ​ክት ወደ ሻለ​ቃው ደረ​ሰ​ለት። በዚያ ጊዜም ጭፍ​ሮ​ቹን ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው ጋር ይዞ ወደ እነ​ርሱ ሄደ፤ እነ​ር​ሱም የሻ​ለ​ቃ​ውን ጭፍ​ሮች ባዩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስን መም​ታ​ታ​ቸ​ውን ተዉ። የሻ​ለ​ቃ​ውም ቀረብ ብሎ ያዘው፤ በሁ​ለት ሰን​ሰ​ለ​ትም እን​ዲ​ታ​ሰር አዘዘ፤ “ምን​ድ​ነው? ምንስ አደ​ረገ?” ብሎም ጠየቀ። ሕዝ​ቡም እኩ​ሌ​ቶቹ እን​ዲህ ነው፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም እን​ዲህ አይ​ደ​ለም እያሉ ይጮሁ ነበር፤ ሻለ​ቃ​ውም ሕዝቡ የሚ​ታ​ወ​ክ​በ​ትን ርግ​ጡን ማወቅ ተሣ​ነው፤ ወደ ወታ​ደ​ሮ​ቹም ሰፈር እን​ዲ​ወ​ስ​ዱት አዘዘ። ደረ​ጃ​ው​ንም በሚ​ወ​ጣ​በት ጊዜ ወታ​ደ​ሮች ተሸ​ክ​መው አወ​ጡት፤ ሰው ይጋፋ ነበ​ርና። ብዙ​ዎ​ችም ይከ​ተ​ሉት ነበር፤ ሕዝ​ቡም፥ “አስ​ወ​ግ​ዱት” እያሉ ይጮሁ ነበር። ወደ ሰፈ​ርም በደ​ረሰ ጊዜ ጳው​ሎስ ሻለ​ቃ​ውን፥ “ላነ​ጋ​ግ​ርህ ትፈ​ቅ​ድ​ል​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ሻለ​ቃ​ውም፥ “የጽ​ርዕ ቋንቋ ታው​ቃ​ለ​ህን?” አለው። “ምና​ል​ባት ከዚህ በፊት ወን​ጀል የሠ​ራ​ህና ከነ​ፍሰ ገዳ​ዮች አራት ሺህ ሰዎ​ችን ይዘህ ወደ ምድረ በዳ የወ​ጣህ ያ ግብ​ፃዊ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?” አለው። ጳው​ሎ​ስም፥ “እኔስ አይ​ሁ​ዳዊ ሰው ነኝ፤ የተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባ​ትም ሀገር ጠር​ሴስ የታ​ወ​ቀች የቂ​ል​ቅያ ከተማ ናት፤ ለሕ​ዝ​ቡም እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ቸው ትፈ​ቅ​ድ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው። በፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም ጊዜ ጳው​ሎስ በደ​ረ​ጃው ላይ ቆሞ እጁን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ እጅ​ግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ ጳው​ሎስ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ ተና​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ።