የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 16:16-24

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 16:16-24 አማ2000

ለጸ​ሎት ስን​ሄ​ድም የም​ዋ​ር​ተ​ኛ​ነት መን​ፈስ ያደ​ረ​ባት አን​ዲት ልጅ አገ​ኘ​ችን፤ በጥ​ን​ቈ​ላም የም​ታ​ገ​ኘ​ውን ብዙ እጅ መንሻ ለጌ​ቶ​ችዋ ታገባ ነበር። ከዚ​ህም በኋላ ጳው​ሎ​ስ​ንና እኛን እየ​ተ​ከ​ተ​ለች፥ “እነ​ዚህ ሰዎች የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸው፤ የሕ​ይ​ወ​ት​ንም መን​ገድ ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ች​ኋል” እያ​ለች ትጮኽ ነበር። ብዙ ቀንም እን​ዲሁ ታደ​ርግ ነበር፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አሳ​ዘ​ነ​ችው፤ መለስ ብሎም፥ “መን​ፈስ ርኩስ፥ ከእ​ር​ስዋ እን​ድ​ት​ወጣ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም አዝ​ዤ​ሃ​ለሁ” አለው፤ ወዲ​ያ​ው​ኑም ተዋት። ጌቶ​ች​ዋም የም​ታ​ገ​ባ​ላ​ቸው የጥ​ቅ​ማ​ቸው ተስፋ እንደ ቀረ ባዩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስ​ንና ሲላ​ስን ይዘው በገ​በያ እየ​ጐ​ተቱ ወደ ገዢ​ዎች ወሰ​ዱ​አ​ቸው። ወደ ገዢ​ዎ​ችም አቅ​ር​በው፥ “እነ​ዚህ ሰዎች ከተ​ማ​ች​ንን ያሸ​ብ​ሩ​ብ​ናል፤ እነ​ር​ሱም አይ​ሁድ ናቸው። እኛ የሮሜ ሰዎች ስን​ሆ​ንም ልና​ደ​ር​ገው የማ​ይ​ገ​ባ​ንን ሕግ ይና​ገ​ራሉ” አሉ። ሕዝ​ቡም ተነ​ሡ​ባ​ቸው፤ ገዢ​ዎ​ቹም ልብ​ሳ​ቸ​ውን ገፍ​ፈው በበ​ትር ይመ​ቱ​አ​ቸው ዘንድ አዘዙ። በብ​ዙም ደብ​ድ​በው አሰ​ሩ​አ​ቸው፤ የወ​ህኒ ቤቱን ዘበ​ኛም አጽ​ንቶ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቃ​ቸው አዘ​ዙት። እር​ሱም ትእ​ዛ​ዙን ተቀ​ብሎ ወደ ውስ​ጠ​ኛው ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባ​ቸው፤ እግ​ራ​ቸ​ው​ንም በግ​ንድ አጣ​ብቆ ጠረ​ቃ​ቸው።