የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 12:6-16

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 12:6-16 አማ2000

ሄሮ​ድ​ስም ማለዳ ያቀ​ር​በው ዘንድ በወ​ደ​ደ​ባት በዚ​ያች ሌሊት ጴጥ​ሮስ ሁለ​ቱን እጆ​ቹን በሰ​ን​ሰ​ለት ታስሮ በሁ​ለት ወታ​ደ​ሮች መካ​ከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ችም የወ​ኅኒ ቤቱን በር ይጠ​ብቁ ነበር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወርዶ በአ​ጠ​ገቡ ቆመ፤ በቤ​ትም ውስጥ ብር​ሃን ሆነ፤ ጴጥ​ሮ​ስ​ንም ጎኑን ነክቶ ቀሰ​ቀ​ሰ​ውና፥ “ፈጥ​ነህ ተነሥ” አለው፥ ሰን​ሰ​ለ​ቶ​ቹም ከእ​ጆቹ ወል​ቀው ወደቁ። መል​አ​ኩም፥ “ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፥ ጫማ​ህ​ንም ተጫማ” አለው፤ እንደ አዘ​ዘ​ውም አደ​ረገ፤ “ልብ​ስ​ህ​ንም ልበ​ስና ተከ​ተ​ለኝ” አለው። ተከ​ት​ሎ​ትም ወጣ፤ ጴጥ​ሮስ ግን ራእይ የሚ​ያይ ይመ​ስ​ለው ነበረ እንጂ በመ​ል​አኩ የሚ​ደ​ረ​ገው ነገር እው​ነት እንደ ሆነ አላ​ወ​ቀም ነበር። መጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንና ሁለ​ተ​ኛ​ውን ዘብ አል​ፈው ወደ ከተማ ወደ​ም​ት​ወ​ስ​ደው ወደ ብረቱ መዝ​ጊያ ደረሱ፤ ያን​ጊ​ዜም መዝ​ጊ​ያው ራሱ ተከ​ፈ​ተ​ላ​ቸው፤ ወጥ​ተ​ውም በአ​ንድ ስላች መን​ገድ ሄዱ፤ መል​አ​ኩም ጴጥ​ሮ​ስን ትቶት ሄደ። ያን​ጊ​ዜም የጴ​ጥ​ሮስ ልቡና ተመ​ለ​ሰ​ለ​ትና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ልኮ ከሄ​ሮ​ድስ እጅና የአ​ይ​ሁድ ሕዝብ ይጠ​ብ​ቁት ከነ​በ​ረው ሁሉ እንደ አዳ​ነኝ በእ​ው​ነት አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ። ከዚ​ህም በኋላ በአ​ስ​ተ​ዋለ ጊዜ ብዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች ተሰ​ብ​ስ​በው ይጸ​ል​ዩ​በት ወደ ነበ​ረው ማር​ቆስ ወደ​ተ​ባ​ለው ወደ ዮሐ​ንስ እናት ወደ ማር​ያም ቤት ሄደ። ጴጥ​ሮ​ስም በሩን አን​ኳኳ፤ ሮዴ የም​ት​ባል ብላ​ቴ​ናም ልት​ከ​ፍ​ት​ለት መጣች። የጴ​ጥ​ሮ​ስም ድምፅ መሆ​ኑን ዐውቃ ከደ​ስታ የተ​ነሣ አል​ከ​ፈ​ተ​ች​ለ​ትም፤ ነገር ግን ጴጥ​ሮስ በበር ቆሞ ሳለ ሮጣ ነገ​ረ​ቻ​ቸው። እነ​ር​ሱም “አብ​ደ​ሻ​ልን? አንድ ጊዜ ታገሺ” አሉ​አት፤ እር​ስዋ ግን እርሱ እንደ ሆነ ታረ​ጋ​ግጥ ነበር። እነ​ር​ሱም፥ “ምና​ል​ባት መል​አኩ ይሆ​ናል” አሉ። ጴጥ​ሮስ ግን በሩን ማን​ኳ​ኳ​ቱን ቀጠለ፤ ከፍ​ተ​ውም ባዩት ጊዜ ተደ​ነቁ።