በዚያም ወራት ሄሮድስ የቤተ ክርስቲያንን ሹሞች ያዛቸው፤ መከራም አጸናባቸው። የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው። አይሁድንም ደስ እንዳላቸው አይቶ ጴጥሮስን ደግሞ ያዘው፤ ያንጊዜም የፋሲካ በዓል ነበር። ይዞም ወኅኒ ቤት አስገባው፤ ለሚጠብቁት ለዐሥራ ስድስቱ ወታደሮችም አሳልፎ ሰጠው፤ ከፋሲካም በኋላ ወደ ሕዝብ ሊያቀርበው ወድዶ ነበር። ጴጥሮስንም በወኅኒ ቤት ይጠብቁት ነበር፤ በቤተ ክርስቲያንም ዘወትር ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር። ሄሮድስም ማለዳ ያቀርበው ዘንድ በወደደባት በዚያች ሌሊት ጴጥሮስ ሁለቱን እጆቹን በሰንሰለት ታስሮ በሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባቂዎችም የወኅኒ ቤቱን በር ይጠብቁ ነበር። የእግዚአብሔርም መልአክ ወርዶ በአጠገቡ ቆመ፤ በቤትም ውስጥ ብርሃን ሆነ፤ ጴጥሮስንም ጎኑን ነክቶ ቀሰቀሰውና፥ “ፈጥነህ ተነሥ” አለው፥ ሰንሰለቶቹም ከእጆቹ ወልቀው ወደቁ። መልአኩም፥ “ወገብህን ታጠቅ፥ ጫማህንም ተጫማ” አለው፤ እንደ አዘዘውም አደረገ፤ “ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ” አለው። ተከትሎትም ወጣ፤ ጴጥሮስ ግን ራእይ የሚያይ ይመስለው ነበረ እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም ነበር። መጀመሪያውንና ሁለተኛውን ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደምትወስደው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ፤ ያንጊዜም መዝጊያው ራሱ ተከፈተላቸው፤ ወጥተውም በአንድ ስላች መንገድ ሄዱ፤ መልአኩም ጴጥሮስን ትቶት ሄደ። ያንጊዜም የጴጥሮስ ልቡና ተመለሰለትና፥ “እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ በእውነት አሁን ዐወቅሁ” አለ።
የሐዋርያት ሥራ 12 ያንብቡ
ያዳምጡ የሐዋርያት ሥራ 12
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሐዋርያት ሥራ 12:1-11
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos