የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መቃ​ብ​ያን ሣልስ 9

9
1በሰ​ማ​ይም ያለ ቢሆን፥ በም​ድ​ርም ያለ ቢሆን፥ ረቂ​ቅም ቢሆን፥ ግዙ​ፍም ቢሆን ሁሉም የእ​ርሱ ነው፤ ሁሉም በሥ​ር​ዐቱ ጸንቶ ይኖ​ራል። 2ከዓ​ለሙ ሁሉ ፈጣሪ ሕግና ትእ​ዛዝ የሚ​ተ​ላ​ለፍ የለም፤ በሰ​ማይ የሚ​በር የን​ስር ፍለጋ ቢሆን፥ ወደ ወደ​ደ​በት መሄ​ጃ​ውን እርሱ ያዝ​ዛል። 3የእ​ባ​ብ​ንም ጎዳና በዓ​ለት ውስጥ እርሱ ወደ ወደ​ደ​በት ያዝ​ዛል፤ የመ​ር​ከ​ብ​ንም ጎዳና በባ​ሕር ውስጥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ በቀር ጎዳ​ና​ውን የሚ​ያ​ው​ቀው የለም። 4የጻ​ድ​ቅም ነፍስ፥ የኃ​ጥ​እም ነፍስ ብት​ሆን፥ ከሥ​ጋዋ ከተ​ለ​የች በኋላ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ በቀር ነፍስ የም​ት​ሄ​ድ​በ​ትን ጎዳና የሚ​ያ​ውቅ የለም። 5በም​ድረ በዳ ወይም በተ​ራ​ራም ትዞር እንደ ሆነ የም​ት​ዞ​ር​በ​ትን ማን ያው​ቃል? እንደ ወፍም ትበር እንደ ሆነ፥ በተ​ራ​ራ​ውም ንቃ​ቃት ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ አር​ሞ​ን​ኤም ጠል ትሆን እንደ ሆነ፥ 6እንደ ጥቅል ነፋ​ስም ትሆን እንደ ሆነ፥ ጎዳ​ና​ውን እን​ደ​ሚ​ያ​ቀና መብ​ረ​ቅም ትሆን እንደ ሆነ፥ 7በጥ​ልቁ ላይም እን​ደ​ሚ​ያ​በሩ ከዋ​ክ​ብት ትሆን እንደ ሆነ፥ በጥ​ልቁ መካ​ከል እን​ደ​ሚ​ከ​መር እንደ ባሕር ዳር አሸ​ዋም ትሆን እንደ ሆነ፥ 8በባ​ሕ​ሩም ጥልቅ ዳርቻ እንደ ጸና እንደ አድ​ማስ ድን​ጋ​ይም ትሆን እንደ ሆነ፥ በውኃ መፍ​ሰሻ እንደ በቀ​ለች፥ የአ​ማረ ፍሬ​ዋ​ንም እን​ደ​ም​ት​ሰጥ ዛፍ ትሆን እንደ ሆነ፥ 9ዋዕየ ፀሐይ እን​ደ​ሚ​ያ​ቃ​ጥ​ለው፥ ነፋ​ስም አን​ሥቶ ወደ አል​በ​ቀ​ለ​በት ወደ ሌላ ቦታ እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው፥ ፍለ​ጋ​ውም እን​ደ​ማ​ይ​ገኝ እንደ መቃ ትሆን እንደ ሆነ፥ ፍለ​ጋው እን​ደ​ማ​ይ​ገኝ እንደ ጉም ሽን​ትም ትሆን እንደ ሆነ ማን ያው​ቃል?
10የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ መን​ገድ ማን ያው​ቃል? መካ​ሮ​ቹስ እነ​ማን ናቸው? ከማ​ንስ ጋር መከረ? 11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳቡ ከሰው የተ​ሰ​ወረ ነውና ፍለ​ጋ​ውን ማን ይከ​ተ​ላል? 12የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክ​ሩ​ንና ጥበ​ቡን መመ​ር​መር የሚ​ችል ማን ነው? እርሱ ምድ​ርን በውኃ ላይ መሥ​ር​ት​ዋ​ታ​ልና፥ ያለ​ካ​ስ​ማም አጽ​ን​ት​ዋ​ታ​ልና፥ በፍ​ጹም ጥበ​ቡም ሰማ​ይን በነ​ፋስ አጸ​ናው፤ ተባ​ዕ​ታ​ዊ​ው​ንም ውኃ እንደ ድን​ኳን ዘረ​ጋው። 13ደመ​ና​ት​ንም በም​ድር ላይ ዝና​ምን ያዘ​ንሙ ዘንድ አዘ​ዛ​ቸው፤ ሣር​ንም ያበ​ቅ​ላል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ን​ድ​ነት ደስ ይለን ዘንድ ለሰው ምግብ ሊሆኑ ቍጥር የሌ​ላ​ቸው ፍሬ​ዎ​ችን ያበ​ቅ​ላል። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ልጆች በረ​ከ​ቱን ሁሉ፥ ደስ​ታ​ው​ንና ጥጋ​ቡ​ንም ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል ይኸ​ውም ጠግ​በው ከም​ድር ፍሬ የሰ​ጣ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑት ዘንድ ነው። 15የአ​ማረ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ንም ያለ​በ​ሳ​ቸ​ውን፥ የሚ​ፈ​ለ​ገ​ው​ንም በረ​ከት ሁሉ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ ለሚ​ፈ​ጽሙ ሰዎች የተ​ሰጠ ደስ​ታ​ው​ንና ተድ​ላ​ው​ንም ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል። 16የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትእ​ዛዝ ለሚ​ጠ​ብቁ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው በአ​ዘ​ጋ​ጀው ማደ​ሪያ በሰ​ማ​ያት ክብ​ር​ንና መወ​ደ​ድን ደስ​ታ​ንም ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል። 17በአ​ም​ል​ኮ​ቱና በፍ​ርዱ ለኖሩ፥ ሕጉን ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ይሹ ዘንድ ለጠ​በ​ቃ​ቸ​ውና ለመ​ገ​ባ​ቸው፥ ለአ​ሳ​ደ​ጋ​ቸ​ውና ለአ​ከ​በ​ራ​ቸው፥ ከእ​ር​ሱም ትእ​ዛዝ ላል​ወጡ ክብ​ር​ንና ሞገ​ስን ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል፤ እኔም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን በማ​ድ​ከም፥ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም በመ​ጠ​በቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ዓለም ለወ​ዳ​ጆቹ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን አየሁ። 18ሁሉ​ንም እንደ ለመ​ኑት ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል፥ ፈቃ​ዳ​ቸ​ው​ንም ይፈ​ጽ​ም​ላ​ቸ​ዋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ አት​ውጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ፈቃድ ፈጽሙ። 19እን​ዳ​ይ​ቈ​ጣ​ባ​ችሁ፥ በአ​ንድ ጊዜም እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ችሁ፥ በቍ​ጣ​ውም እን​ዳ​ይ​ገ​ር​ፋ​ችሁ፥ ቀድሞ ከነ​በ​ራ​ች​ሁ​በት ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ርስ​ትም እን​ዳ​ት​ወጡ፥ ማደ​ሪ​ያ​ች​ሁም እስከ ዘለ​ዓ​ለሙ ድረስ መውጫ በሌ​ለ​በት በገ​ሃ​ነም እን​ዳ​ይ​ሆን ከት​እ​ዛ​ዙና ከሕጉ አት​ውጡ።
20በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በቆ​ማ​ችሁ ጊዜ ሥራ​ችሁ በጎ ይሆን ዘንድ ነፍ​ሳ​ችሁ ከሥ​ጋ​ችሁ ሳት​ለይ የፈ​ጣ​ሪ​ያ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ ጠብቁ። 21የሰ​ማ​ይና የም​ድር መን​ግ​ሥት ለእ​ርሱ ብቻ ነውና፤ ከሃ​ሊ​ነ​ትም፥ መን​ግ​ሥ​ትም ለእ​ርሱ ነውና፤ መራ​ራ​ትና ይቅር ማለ​ትም ለእ​ርሱ ብቻ ነው። 22እርሱ ባለ​ጸጋ ያደ​ር​ጋ​ልና፤ ያደ​ኸ​ያ​ል​ምና፥ ያዋ​ር​ዳ​ልና፥ ያከ​ብ​ራ​ል​ምና።
23ዳዊ​ትም ስለ እርሱ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፥ “ሰው ከን​ቱን ይመ​ስ​ላል፤ ዘመ​ኑም እንደ ጥላ ያል​ፋል። 24አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትኖ​ራ​ለህ፤ ስም አጠ​ራ​ር​ህም ለልጅ ልጅ ነው።” 25ዳግ​መ​ኛም እን​ዲህ አለ፥ “መን​ግ​ሥ​ትህ የዘ​ለ​ዓ​ለም መን​ግ​ሥት ነው፤ አገ​ዛ​ዝ​ህም ለልጅ ልጅ ነው፥” አንተ መን​ግ​ሥ​ትን ከሳ​ኦል ወስ​ደህ ለዳ​ዊት ሰጠህ። 26አን​ተን ግን የሚ​ሾ​ምህ የለም፤ አን​ተ​ንም መሻር የሚ​ችል የለም፤ አን​ተን ማየት የሚ​ችል የለም፤ አንተ ግን ሁሉን ታያ​ለህ። 27መን​ግ​ሥ​ት​ህም ለልጅ ልጅ ዘመ​ንና ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ሻ​ርም፤ እር​ሱን የሚ​ገ​ዛው የለም፤ እርሱ ግን ሁሉን ይገ​ዛል፤ ሁሉ​ንም ያያል። 28ያመ​ሰ​ግ​ኑት ዘንድ ያለ ጥር​ጥ​ርም በቀና ልቡና አም​ል​ኮ​ቱን ያውቁ ዘንድ፥ ከፈ​ጠ​ራ​ቸ​ውና ከመ​ገ​ባ​ቸው፥ ከአ​ከ​በ​ራ​ቸ​ውና ከአ​ሳ​ደ​ጋ​ቸው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብቻ በቀር ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት የሚ​ሰ​ግዱ እን​ዳ​ይ​ሆኑ እርሱ ሰውን በመ​ል​ኩና በም​ሳ​ሌው ፈጥ​ሮ​ታ​ልና ልብ​ንና ኵላ​ሊ​ትን ይመ​ረ​ም​ራል። 29እነ​ርሱ ግን የፈ​ጠ​ራ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማም​ለ​ክን እንቢ አሉ፤ ለድ​ን​ጋ​ይና ለእ​ን​ጨት፥ የሰው እጅም ለሠ​ራ​ቸው ለብ​ርና ለወ​ርቅ ይሰ​ግ​ዳሉ። 30በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይቆም ዘንድ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው ጢስ ወደ ሰማይ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ ይሠ​ዉ​ላ​ቸ​ዋል፤ ጣዖ​ታ​ቸ​ው​ንም በማ​ም​ለክ ሰለ ሠሩት ኀጢ​አ​ታ​ቸው ሁሉ ይከ​ስ​ሳ​ቸ​ዋል። 31የተ​ማ​ሩ​ት​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ አል​ጠ​በ​ቁም። ነገር ግን ለጣ​ዖት መስ​ገ​ድን፥ የሚ​ገባ ያይ​ደለ የጐ​ደፈ ሥራ​ንም ሁሉ፥ በኮ​ከብ ማሟ​ረ​ትን፥ ጥን​ቆ​ላ​ንና ጣዖት ማም​ለ​ክን፥ ክፉ ፈቃ​ድ​ንና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የማ​ይ​ወ​ድ​ደ​ው​ንም ሥራ ሁሉ ተማሩ። 32በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በመ​ላ​እ​ክቱ ፊት እን​ዲ​መ​ሰ​ገኑ ከኀ​ጢ​አ​ትና ከበ​ደል ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ያድኑ ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማመ​ስ​ገ​ንን አል​ወ​ደ​ዱ​ምና በጎ ሥራ በማ​ጣት ይኸን ሁሉ ይሠ​ራሉ። 33ከተ​ቀ​በ​ሩ​በ​ትና አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸው ከረ​ገ​ፉ​በት ከመ​ቃ​ብር ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት በተ​ነሡ ጊዜ፥ ነፍ​ሳ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕራ​ቁ​ት​ዋን ትቆ​ማ​ለች፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም ለደ​ጋ​ጎች ሰዎች በተ​ዘ​ጋጁ በብ​ር​ሃን ቤቶች ትኖ​ራ​ለች። 34የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች ነፍስ ግን በጨ​ለማ ትኖ​ራ​ለች፤ መቃ​ብ​ራ​ትም በተ​ከ​ፈቱ ጊዜ ሥጋ​ዎች ይነ​ሣሉ፤ ነፍ​ሳ​ትም ቀድሞ ወደ ተለ​ዩ​አ​ቸው ሥጋ​ዎች ይመ​ለ​ሳሉ። 35ዕራ​ቁ​ታ​ቸ​ውን እንደ ተወ​ለዱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕራ​ቁ​ታ​ቸ​ውን ይቆ​ማሉ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ታ​ቸው ጀምሮ እስ​ከ​ዚያ ጊዜ የሠ​ሩት ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይገ​ለ​ጣል። 36ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን በጫ​ን​ቃ​ቸው ይሸ​ከ​ማሉ፤ ጥቂ​ትም ቢሆን፥ ብዙም ቢሆን፥ ኀጢ​አት ቢሠሩ እንደ ሠሩት ሥራ​ቸው ይቀ​በ​ላሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ