የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 5

5
ዳዊት በይ​ሁ​ዳና በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እንደ ነገሠ
(1ዜ.መ. 11፥1-914፥1-7)
1የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ወደ ኬብ​ሮን ወደ ዳዊት መጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እኛ የአ​ጥ​ን​ትህ ፍላጭ የሥ​ጋህ ቍራጭ ነን። 2አስ​ቀ​ድሞ ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ታ​ወ​ጣና የም​ታ​ገባ አንተ ነበ​ርህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አንተ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ትጠ​ብ​ቃ​ለህ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ አለቃ ትሆ​ና​ለህ ብሎህ” ነበር። 3የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብ​ሮን መጡ፤ ንጉሡ ዳዊ​ትም በኬ​ብ​ሮን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን ቀቡት። 4ዳዊ​ትም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ አርባ ዓመ​ትም ነገሠ፤ 5በኬ​ብ​ሮን በይ​ሁዳ ላይ ሰባት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር ነገሠ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉና በይ​ሁዳ ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።
6ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በሀ​ገሩ ውስጥ ወደ​ሚ​ኖ​ሩት ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄዱ፤ እነ​ር​ሱም ዳዊ​ትን፥ “ወደ​ዚህ አት​ገ​ባም” አሉት። ዕው​ሮ​ችና አን​ካ​ሶ​ችም ወደ​ዚህ አት​ገ​ባም ብለው ተቃ​ወ​ሙት። 7ነገር ግን ዳዊት አን​ባ​ዪ​ቱን ጽዮ​ንን ያዘ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ናት። 8በዚ​ያም ቀን ዳዊት፥ “ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን የሚ​መታ ሁሉ፥ ዕው​ሮ​ች​ንና አን​ካ​ሶ​ችን፥ የዳ​ዊ​ት​ንም ነፍስ የሚ​ጠ​ሉ​ትን ሁሉ በሳ​ንጃ ይው​ጋ​ቸው” አለ። ስለ​ዚ​ህም፥ “ዕው​ርና አን​ካሳ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግቡ” ተባለ። 9ዳዊ​ትም በአ​ን​ባ​ዪቱ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ተባ​ለች። ከተ​ማ​ዋ​ንም ዙሪ​ያ​ዋን እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ ቀጠ​ራት፤ ቤቱ​ንም ሠራ። 10ዳዊ​ትም እየ​በ​ረታ፥ ከፍ እያ​ለም ሄደ፤ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ።
11የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን፥ የዝ​ግባ እን​ጨ​ት​ንም፥ አና​ጢ​ዎ​ች​ንም፥ ድን​ጋይ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንም ላከ፤ ለዳ​ዊ​ትም ቤት ሠሩ​ለት። 12ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ አድ​ርጎ እን​ዳ​ዘ​ጋ​ጀው፥ ስለ ሕዝቡ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም መን​ግ​ሥ​ቱን ከፍ እን​ዳ​ደ​ረገ ዐወቀ።
13ዳዊ​ትም ከኬ​ብ​ሮን ከመጣ በኋላ እንደ ገና ቁባ​ቶ​ቹ​ንና ሚስ​ቶ​ቹን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰደ፤ ለዳ​ዊ​ትም ደግሞ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት። 14በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት ስማ​ቸው ይህ ነው፤ ሳሚስ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎ​ሞን፥ 15ኢያ​ቢ​ሖር፥ ኤሊ​ሱስ፥ ናፌቅ፥ ያፍያ፥ 16ኤሊ​ሳማ፥ ኤሊ​ዳሂ፥ ኤሊ​ፋ​ላት፥#“ኤሊ​ፋ​ላት” ከሚ​ለው ስም በኋላ ያሉ​ትን ስሞች ዕብ. አይ​ጽ​ፍም። ሶሜኤ፥ ኢያ​ሴ​ቦት፥ ናታን፥ ጋላ​ማ​ሄን፥ የበ​አር፥ ትሄ​ሱስ፥ ኤል​ፋ​ላት፥ ናጌድ፥ ናሬት፥ ያናታ፥ ሊሳ​ሚስ፥ በአ​ሊ​ማት፥ ኤል​ፋ​ላድ።
ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ድል እንደ አደ​ረገ
(1ዜ.መ. 14፥8-17)
17ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዳዊት በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደ ተቀባ ሰሙ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ዳዊ​ትን ሊፈ​ልጉ ወጡ፤ ዳዊ​ትም በሰማ ጊዜ ወደ ምሽጉ ወረደ። 18ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መጥ​ተው በረ​ዓ​ይት ሸለቆ ተበ​ት​ነው ሰፈሩ። 19ዳዊ​ትም፥ “ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ልው​ጣን? በእ​ጄስ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ህን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በር​ግጥ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ውጣ” አለው። 20ዳዊ​ትም ከላ​ይ​ኛው መጋ​ደያ መጣ፤ በዚ​ያም መታ​ቸ​ውና፥ “ውኃ እን​ደ​ሚ​ያ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶቼን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በፊቴ አጠ​ፋ​ቸው” አለ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም “የላ​ይ​ኛው መጋ​ደያ” ተብሎ ተጠራ። 21ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወሰ​ዱ​አ​ቸው።
22ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ደግሞ መጡ፤ ወደ ረዓ​ይ​ትም ሸለቆ ወረዱ። 23ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በኋ​ላ​ቸው ዞረህ በሾ​ላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠ​ማ​ቸው እንጂ አት​ውጣ። 24በሾ​ላ​ውም ዛፍ#ግሪክ ሰባ. ሊ. የል​ቅሶ ቦታ ማለ​ትን ያሳ​ያል። ራስ ውስጥ የሽ​ው​ሽ​ውታ ድምፅ ስት​ሰማ፥ በዚያ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ ለመ​ም​ታት በፊ​ትህ ወጥቶ ይሆ​ና​ልና በዚያ ጊዜ ፍጠን” አለው። 25ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም እስከ ጌሴራ ድረስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ