የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 4

4
ኢያ​ቡ​ስቴ እንደ ተገ​ደለ
1የሳ​ኦ​ልም ልጅ ኢያ​ቡ​ስቴ አበ​ኔር በኬ​ብ​ሮን እንደ ሞተ ሰማ፤ እጆ​ቹም ደከሙ፤ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ሁሉ ደነ​ገጡ። 2ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለኢ​ያ​ቡ​ስቴ የጭ​ፍራ አለ​ቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበ​ሩት፤ የአ​ን​ደ​ኛው ስም በዓና፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም ሬካብ ነበረ፤ ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች የቤ​ሮ​ታ​ዊው የሬ​ሞን ልጆች ነበሩ፤ ቤሮ​ትም ለብ​ን​ያም ተቈ​ጥራ ነበር። 3ቤሮ​ታ​ው​ያ​ንም ወደ ጌቴም ሸሽ​ተው ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ተጠ​ግ​ተው ነበር።
4ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለዮ​ና​ታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበ​ረው። የሳ​ኦ​ልና የዮ​ና​ታን ወሬ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል በመጣ ጊዜ የአ​ም​ስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግ​ዚ​ቱም አዝ​ላው ሸሸች፤ ልት​ሸ​ሽም ስት​ሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ነበረ።
5የቤ​ሮ​ታ​ዊ​ውም የሬ​ሞን ልጆች ሬካ​ብና በዓና ቀኑ ሲሞቅ ወደ ኢያ​ቡ​ስቴ ቤት መጡ፤ እር​ሱም በቀ​ትር ጊዜ በአ​ል​ጋው ላይ ተኝቶ ነበር። 6በረ​ኛ​ዪ​ቱም ስንዴ ታበ​ጥር ነበር፤ አን​ቀ​ላ​ፍ​ታም ተኝታ ነበር፤ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾቹ ሬካ​ብና በዓ​ናም በቀ​ስታ ወደ ቤት ገቡ። 7ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ኢያ​ቡ​ስቴ በእ​ል​ፍኙ በም​ን​ጣፉ ላይ ተኝቶ ሳለ መቱት፥ ገደ​ሉ​ትም፤ ራሱ​ንም ቈር​ጠው ወሰ​ዱት፥ በዓ​ረ​ባም መን​ገድ ሌሊ​ቱን ሁሉ ሄዱ። 8የኢ​ያ​ቡ​ስ​ቴ​ንም ራስ ይዘው ወደ ዳዊት ወደ ኬብ​ሮን መጡ፤ ንጉ​ሡ​ንም፥ “ነፍ​ስ​ህን ይሻ የነ​በ​ረው የጠ​ላ​ትህ የሳ​ኦል ልጅ የኢ​ያ​ቡ​ስቴ ራስ እነሆ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዛሬ ከጠ​ላ​ትህ ከሳ​ኦ​ልና ከዘሩ ለጌ​ታ​ችን ለን​ጉሥ በቀ​ሉን መለ​ሰ​ለት” አሉት። 9ዳዊ​ትም ለቤ​ሮ​ታ​ዊው ለሬ​ሞን ልጆች ለሬ​ካ​ብና ለወ​ን​ድሙ ለበ​ዓና እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው፥ “ነፍ​ሴን ከመ​ከራ ሁሉ ያዳነ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! 10መል​ካም ወሬ የያዘ መስ​ሎት እነሆ፥ ሳኦል ሞተ ብሎ የነ​ገ​ረ​ኝን የም​ስ​ራቹ ዋጋ እን​ዲ​ሆን ይዤ በሴ​ቄ​ላቅ ገደ​ል​ሁት። 11አሁ​ንም እና​ንተ ክፉ​ዎች ሰዎች በቤቱ ውስጥ በአ​ል​ጋው ላይ ጻድ​ቁን ሰው ገደ​ላ​ች​ሁት፤ እነሆ፥ ደሙን ከእ​ጃ​ችሁ እሻ​ለሁ፤ ከም​ድ​ርም አጠ​ፋ​ች​ኋ​ለሁ።” 12ዳዊ​ትም ጐል​ማ​ሶ​ቹን አዘዘ፤ ገደ​ሉ​አ​ቸ​ውም፤ እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ቈር​ጠው በኬ​ብ​ሮን በውኃ መቆ​ሚያ አጠ​ገብ አን​ጠ​ለ​ጠ​ሉ​አ​ቸው። የኢ​ያ​ቡ​ስ​ቴን ራስ ግን ወስ​ደው በአ​በ​ኔር መቃ​ብር በኬ​ብ​ሮን#“በኬ​ብ​ሮን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ቀበ​ሩት።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ