የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 15

15
አቤ​ሴ​ሎም በአ​ባቱ በዳ​ዊት ላይ እንደ ዐመፀ
1ከዚ​ህም በኋላ አቤ​ሴ​ሎም ሰረ​ገ​ላና ፈረ​ሶች፥ በፊ​ቱም የሚ​ሮጡ አምሳ ሰዎች አዘ​ጋጀ። 2አቤ​ሴ​ሎ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ በበሩ ጎዳና ይቆም ነበር፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ከን​ጉሥ ለማ​ስ​ፈ​ረድ ጉዳይ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ወደ እርሱ እየ​ጠራ፥ “አንተ ከወ​ዴት ከተማ ነህ?” ብሎ ይጠ​ይቅ ነበር። እር​ሱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ከአ​ን​ዲቱ ነኝ” ይለው ነበር። 3አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “ነገ​ርህ መል​ካም ነው፤ ቀላ​ልም ነው፤ ነገር ግን ከን​ጉሥ ዘንድ የሚ​ሰ​ማህ የለም” ይለው ነበር። 4አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “ነገ​ርና ክር​ክር ያለው ሁሉ ወደ እኔ ይመጣ ዘንድ፥ ቅንም ፍርድ እፈ​ር​ድ​ለት ዘንድ በሀ​ገር ላይ ፈራጅ አድ​ርጎ ማን በሾ​መኝ?” ይል ነበር። 5ሰውም እጅ ለመ​ን​ሣት ወደ እርሱ በቀ​ረበ ጊዜ እጁን ዘር​ግቶ አቅፎ ይስ​መው ነበር። 6በን​ጉሡ ዘንድ ሊፋ​ረዱ ለሚ​መጡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ አቤ​ሴ​ሎም እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበር፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች ልብ ማረከ።
7እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከአ​ራት ዓመት በኋላ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አርባ ዓመት” ይላል። አቤ​ሴ​ሎም አባ​ቱን፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሳ​ል​ሁ​ትን ስእ​ለት በኬ​ብ​ሮን አደ​ርግ ዘንድ ልሂድ። 8እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በሶ​ርያ ጌድ​ሶር ሳለሁ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቢመ​ል​ሰኝ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ር​ባ​ለሁ ብዬ ስእ​ለት ተስዬ ነበ​ርና” አለው። 9ንጉ​ሡም፥ “በሰ​ላም ሂድ” አለው፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ኬብ​ሮን ሄደ። 10አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “የመ​ለ​ከት ድምፅ በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ፥ አቤ​ሴ​ሎም በኬ​ብ​ሮን ነገሠ” በሉ የሚሉ ጕበ​ኞ​ችን ወደ እስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ላከ። 11የተ​ጠ​ሩ​ትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሄዱ፤ እነ​ር​ሱም በየ​ዋ​ህ​ነት ሄዱ፤ ነገ​ሩ​ንም ሁሉ ከቶ አያ​ው​ቁም ነበር። 12አቤ​ሴ​ሎ​ምም መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሠ​ዋ​በት ጊዜ የዳ​ዊት አማ​ካሪ ወደ ነበ​ረው ጌሎ​ና​ዊው አኪ​ጦ​ፌል ወደ ከተ​ማው ጊሎ ላከ። ሴራ​ውም ጽኑ ሆነ፤ ከአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።
ዳዊት ከአ​ቤ​ሴ​ሎም እንደ ሸሸ
13የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ልብ ወደ አቤ​ሴ​ሎም ተመ​ል​ሶ​አል የሚል መል​እ​ክ​ተኛ ወደ ዳዊት ሄደ። 14ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያሉ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ሁሉ፥ “ተነሡ እን​ሽሽ፤ ከአ​ቤ​ሴ​ሎም እጅ የም​ን​ድ​ን​በት የለ​ን​ምና፤ ፈጥኖ እን​ዳ​ይ​ዘን፥ ክፉም እን​ዳ​ያ​መ​ጣ​ብን፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በሰ​ልፍ ስለት እን​ዳ​ይ​መታ ፈጥ​ና​ችሁ እን​ሂድ” አላ​ቸው። 15የን​ጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖች ንጉ​ሡን፥ “እነሆ፥ ጌታ​ችን ንጉሥ የመ​ረ​ጠ​ውን ሁሉ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉት። 16ንጉ​ሡና ከእ​ር​ሱም በኋላ ቤተ ሰቡ ሁሉ በእ​ግ​ራ​ቸው ወጡ፤ ንጉ​ሡም ቁባ​ቶቹ የነ​በሩ ዐሥ​ሩን ሴቶች ቤቱን ይጠ​ብቁ ዘንድ ተወ። 17ንጉ​ሡና ሕዝቡ ሁሉ በእ​ግር ወጡ፤ በሩ​ቅም ቦታ ቆሙ። 18ብላ​ቴ​ኖ​ቹም ሁሉ ተከ​ተ​ሉት፤ ኬል​ቲ​ያ​ው​ያ​ንና ፌል​ታ​ው​ያ​ንም ሁሉ በም​ድረ በዳ በወ​ይራ ሥር ቆሙ። ሕዝ​ቡም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ይሄዱ ነበር። ከእ​ርሱ ጋር ያሉ ሰዎ​ችም ሁሉ ስድ​ስት መቶ ነበሩ። ከእ​ርሱ ጋር ፌል​ታ​ው​ያ​ንና ኬል​ቲ​ያ​ው​ያን፥ በእ​ግ​ራ​ቸው ከጌት የመጡ ስድ​ስት መቶ ጌታ​ው​ያ​ንም ነበሩ። በን​ጉ​ሡም ፊት ይሄዱ ነበር።
19ንጉ​ሡም ጌታ​ዊ​ውን ኤቲን፥ “ከእኛ ጋር ለምን መጣህ? አንተ ከስ​ፍ​ራህ የመ​ጣህ ስደ​ተ​ኛና እን​ግዳ ነህና ተመ​ለስ፤ ከን​ጉ​ሡም ጋር ተቀ​መጥ፤ 20የመ​ጣ​ኸው ትና​ንት ነው፤ ዛሬ ከእኛ ጋር ላዙ​ር​ህን? እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እሄ​ዳ​ለሁ፤ አንተ ግን ተመ​ለስ፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ህ​ንም ከአ​ንተ ጋር መል​ሳ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምሕ​ረ​ቱ​ንና እው​ነ​ቱን ያድ​ር​ግ​ልህ” አለው። 21ኤቲም ለን​ጉሡ መልሶ፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በጌ​ታ​ዬም በን​ጉሡ ሕይ​ወት እም​ላ​ለሁ! ጌታዬ ባለ​በት ስፍራ ሁሉ፥ በሞ​ትም ቢሆን በሕ​ይ​ወ​ትም፥ በዚያ ደግሞ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ እሆ​ና​ለሁ” አለው። 22ንጉ​ሡም ኤቲን፥ “ና ከእኔ ጋር ተሻ​ገር” አለው፤ ጌታ​ዊው ኤቲና ንጉ​ሡም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝቡ ሁሉ ተሻ​ገሩ። 23ሀገ​ሪ​ቱም ሁላ በታ​ላቅ ድምፅ አለ​ቀ​ሰች። ሕዝ​ቡም ሁሉ በቄ​ድ​ሮን ወንዝ ተሻ​ገሩ፤ ንጉ​ሡም ደግሞ የቄ​ድ​ሮ​ንን ወንዝ ተሻ​ገረ፤ ንጉ​ሡና ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተሻ​ገሩ።
24እነ​ሆም፥ ደግሞ፥ ሳዶ​ቅና ከእ​ር​ሱም ጋር ሌዋ​ው​ያን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት አመጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት አስ​ቀ​መጡ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ፈጽሞ እስ​ኪ​ያ​ልፉ ድረስ አብ​ያ​ታር ወጣ። 25ንጉ​ሡም ሳዶ​ቅን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ ከተማ መልስ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ሞገስ አግ​ኝቼ እንደ ሆንሁ፥ መልሶ እር​ሷ​ንና ክብ​ሯን ያሳ​የ​ኛል፤ 26ነገር ግን አል​ወ​ድ​ድ​ህም ቢለኝ፥ እነ​ሆኝ በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ያድ​ር​ግ​ብኝ” አለው። 27ንጉ​ሡም ደግሞ ካህ​ኑን ሳዶ​ቅን፥ “እነሆ፥ አን​ተና ልጅህ አኪ​ማ​ኦስ፥ የአ​ብ​ያ​ታ​ርም ልጅ ዮና​ታን፥ ሁለቱ ልጆ​ቻ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር በሰ​ላም ወደ ከተማ ተመ​ለሱ። 28እዩ፤ እኔም እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ወሬ እስ​ኪ​መ​ጣ​ልኝ ድረስ በም​ድረ በዳው ውስጥ በሜ​ዳው እቈ​ያ​ለሁ” አለው። 29ሳዶ​ቅና አብ​ያ​ታ​ርም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መለ​ሷት፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።
30ዳዊ​ትም ወደ ደብረ ዘይት ዐቀ​በት ወጣ፤ ሲወ​ጣም ያለ​ቅስ ነበር፤ ራሱ​ንም ተከ​ና​ንቦ ነበር፤ ያለ​ጫ​ማም ይሄድ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ተከ​ና​ን​በው ነበር፤ እያ​ለ​ቀ​ሱም ይወጡ ነበር። 31አኪ​ጦ​ፌል ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ዳዊ​ትም፥ “አቤቱ የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር ለውጥ” አለ። 32ዳዊ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ሰገ​ደ​በት ወደ ተራ​ራው ራስ መጣ፤ ወዳጁ ኵሲም ልብ​ሱን ቀደደ፤ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ ሊገ​ና​ኘው መጣ። 33ዳዊ​ትም አለው፥ “ከእኔ ጋር ብት​ሻ​ገር ሸክም ትሆ​ን​ብ​ኛ​ለህ፤ 34ወደ ከተማ ግን ተመ​ል​ሰህ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም፦ ወን​ድ​ሞ​ችህ፥ ንጉ​ሡም መጡ። እነሆ፥ በኋ​ላዬ ናቸው። ንጉሥ ሆይ፥ አገ​ል​ጋ​ይህ ነኝ፤ አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ባ​ትህ አገ​ል​ጋይ ነበ​ርሁ፥ እን​ዲሁ አሁ​ንም ለአ​ንተ አገ​ል​ጋይ ነኝ፥ ተወኝ ልኑር#“ተወኝ ልኑር” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ብት​ለው የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር ትለ​ው​ጥ​ል​ኛ​ለህ። 35እነሆ፥ ካህ​ናቱ ሳዶ​ቅና አብ​ያ​ታ​ርም በዚያ ከአ​ንተ ጋር ናቸው። ከን​ጉሡ ቤትም የም​ት​ሰ​ማ​ውን ነገር ሁሉ ለካ​ህ​ናቱ ለሳ​ዶ​ቅና ለአ​ብ​ያ​ታር ንገ​ራ​ቸው። 36እነሆ፥ የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ኦ​ስና የአ​ብ​ያ​ታር ልጅ ዮና​ታን፥ ልጆ​ቻ​ቸው በዚያ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አሉ፤ የም​ት​ሰ​ሙ​ትን ሁሉ በእ​ነ​ርሱ እጅ ላኩ​ልኝ።” 37የዳ​ዊ​ትም ወዳጅ ኩሲ ወደ ከተማ መጣ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ደግሞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ገባ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ