የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 16

16
ዳዊ​ትና ሲባ
1ዳዊ​ትም ከተ​ራ​ራው ራስ ጥቂት እልፍ አለ። እነ​ሆም፥ የሜ​ም​ፌ​ቡ​ስቴ አገ​ል​ጋይ ሲባ ሁለት መቶ እን​ጀራ፥ አንድ መቶም ዘለላ ዘቢብ፥ አንድ መቶም ተምር፥ አንድ አቁ​ማ​ዳም ወይን ጠጅ የተ​ጫኑ ሁለት አህ​ዮች እየ​ነዳ ተገ​ና​ኘው። 2ንጉ​ሡም ሲባን፥ “ይህ ለአ​ንተ ምን​ድን ነው?” አለው። ሲባም፥ “አህ​ዮቹ የን​ጉሥ ቤተ ሰቦች ይቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው ዘንድ፥ እን​ጀ​ራ​ውና ተም​ሩም ብላ​ቴ​ኖቹ ይበ​ሉት ዘንድ፥ የወ​ይን ጠጁም በበ​ረሃ የሚ​ደ​ክ​ሙት ይጠ​ጡት ዘንድ ነው” አለ። 3ንጉ​ሡም፥ “የጌ​ታህ ልጅ ወዴት ነው?” አለ። ሲባም ንጉ​ሡን፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ዛሬ የአ​ባ​ቴን መን​ግ​ሥት ይመ​ል​ስ​ል​ኛል ብሎ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​ም​ጦ​አል” አለው። 4ንጉ​ሡም ሲባን፥ “እነሆ፥ ለሜ​ም​ፌ​ቡ​ስቴ የነ​በ​ረው ሁሉ ለአ​ንተ ይሁን” አለው። ሲባም ሰግዶ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊ​ትህ ሞገ​ስን ላግኝ” አለ።
ሳሚ ዳዊ​ትን እንደ ሰደ​በው
5ንጉሡ ዳዊ​ትም ወደ በው​ሪም መጣ፤ እነ​ሆም፥ ሳሚ የሚ​ባል የጌራ ልጅ ከሳ​ኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየ​ሄ​ደም ይረ​ግ​መው ነበር። 6ወደ ዳዊ​ትና ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ድን​ጋይ ይወ​ረ​ውር ነበር፤ በን​ጉ​ሡም ቀኝና ግራ ሕዝቡ ሁሉና ኀያ​ላኑ ሁሉ ነበሩ። 7ሳሚም ሲረ​ግ​መው እን​ዲህ ይል ነበር፥ “ውጣ! አንተ የደም ሰውና ዐመ​ፀኛ ሰው ሂድ! ሂድ! 8በፋ​ን​ታው ነግ​ሠ​ሃ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሳ​ኦ​ልን ቤት ደም ሁሉ መለ​ሰ​ብህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥ​ት​ህን ለል​ጅህ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም እጅ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ታል፤ እነ​ሆም፥ አንተ የደም ሰው ነህና በመ​ከራ ተይ​ዘ​ሃል።”
9የሶ​ር​ህያ ልጅ አቢ​ሳም ንጉ​ሡን አለው፥ “ይህ የሞተ ውሻ ጌታ​ዬን ንጉ​ሡን ስለ​ምን ይረ​ግ​ማል? ልሻ​ገ​ርና ራሱን ልቍ​ረ​ጠው፤” 10ንጉ​ሡም፥ “እና​ንተ የሶ​ር​ህያ ልጆች! በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምን አለኝ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዳዊ​ትን ርገ​መው ብሎ አዝ​ዞ​ታ​ልና ይር​ገ​መኝ፤ ለም​ንስ እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ? የሚ​ለው ማን ነው?” አለ። 11ዳዊ​ትም አቢ​ሳ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ሁሉ፥ “እነሆ፥ ከወ​ገቤ የወ​ጣው ልጄ ነፍ​ሴን ይሻል፤ ይል​ቁ​ንስ ይህ የኢ​ያ​ሚን#ዕብ. “ብን​ያም” ይላል። ልጅ እን​ዴት ነዋ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዝ​ዞ​ታ​ልና ተዉት፥ ይር​ገ​መኝ። 12ምና​ል​ባት መከ​ራ​ዬን አይቶ ስለ ርግ​ማኑ በዚህ ቀን መል​ካም ይመ​ል​ስ​ል​ኛል” አላ​ቸው። 13ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በመ​ን​ገድ ይሄዱ ነበር፤ ሳሚም በተ​ራ​ራው አጠ​ገብ በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያው ይሄድ ነበር፤ ሲሄ​ድም ይረ​ግ​መው፥ ድን​ጋ​ይም ይወ​ረ​ው​ር​በት ነበር፤ ትቢ​ያም ይበ​ት​ን​በት ነበር። 14ንጉ​ሡና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ረው ሕዝብ ሁሉ ደረሱ፤ ደክ​መ​ውም ነበር፤ በዚ​ያም ዐረፉ።
የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልና የኩሲ ምክር
15አቤ​ሴ​ሎ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ሁሉ፥ አኪ​ጦ​ፌ​ልም ከእ​ርሱ ጋር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጡ። 16የዳ​ዊ​ትም ወዳጅ ኩሲ ወደ አቤ​ሴ​ሎም በመጣ ጊዜ ኩሲ አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “ንጉሥ ሆይ! ሽህ ዓመት ያን​ግ​ሥህ” አለው። 17አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኩሲን፥ “ስለ ወዳ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ቸር​ነት ይህ ነውን? ከወ​ዳ​ጅህ ጋር ያል​ሄ​ድህ ስለ ምን​ድን ነው?” አለው። 18ኩሲም አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ይህም ሕዝብ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ለመ​ረ​ጡት ለእ​ርሱ እሆ​ና​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር እኖ​ራ​ለሁ” አለው። 19“ዳግ​ምም የማ​ገ​ለ​ግል ለማን ነው? በን​ጉሥ ልጅ ፊት አይ​ደ​ለ​ምን? በአ​ባ​ትህ ፊት እን​ዳ​ገ​ለ​ገ​ልሁ እን​ዲሁ በአ​ንተ ፊት እሆ​ና​ለሁ” አለው።
20አቤ​ሴ​ሎ​ምም አኪ​ጦ​ፌ​ልን፦ ምን እን​ደ​ም​ና​ደ​ርግ ምከሩ አለው። 21አኪ​ጦ​ፌ​ልም አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “ቤት ሊጠ​ብቁ ወደ ተዋ​ቸው ወደ አባ​ትህ ቁባ​ቶች ግባ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አባ​ት​ህን እን​ዳ​ሳ​ፈ​ር​ኸው ይሰ​ማሉ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ያሉት ሁሉ እጃ​ቸው ይበ​ረ​ታል” አለው። 22ለአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም በሰ​ገ​ነት ላይ ድን​ኳን ተከ​ሉ​ለት፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት ወደ አባቱ ቁባ​ቶች ገባ። 23በእ​ነ​ዚያ በመ​ጀ​መ​ሪያ ወራት የመ​ከ​ራት የአ​ኪ​ጦ​ፌል ምክር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እንደ መጠ​የቅ ነበ​ረች፤ የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልም ምክር ሁሉ ከዳ​ዊ​ትና ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር እን​ዲሁ ነበ​ረች።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ